ነብዩ አዩብ ( ) ለአሏህ ያደረ የታላቅ ስብዕና ባለቤት ናቸው። አሏህ ረጅም እድሜ እና ትልቅ ፀጋን ሰጥቷቸዋል። ብዙ ልጆች ፣ አገልጋዮች ፣ የቀንድ ከብት እና የእርሻ ማሳዎች ነበሯቸው። በጣም ደግና ለጋስ ነበሩ።
ገንዘባቸውን ያወጡት አሏህን በሚያስደስት መንገድ ነው። ድሆችን እና ችግረኞችን አብልተዋል ፣ አልብሰዋል ፣ የሙት ልጆችን እና ጋለሞታዎችን ረድተዋል ፣ ለአሏህ ሲሉ ባሪያዎችን ገዝተው ነፃ አውጥተዋል።
አሏህ በእነሱ ላይ ያደረገውን እልቆቢስ ሲሳይ እና ችሮታ በማስታወስ ህዝቦቹ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ ጥሪ አድርገዋል። አሏህን ሁልጊዜ ያልቃሉ ፣ ያመሰግናሉ። በእርግጥ እሳቸው ለአሏህ ባሮች ትልቅ ምሳሌ ናቸው።
ምንም እንኳ ነብዩ አዩብ ( ) ተከታታይ በሆኑ እጅግ በጣም ከባድ ፈተናዎች አሏህ ቢፈትናቸውም ሁሌም ታጋሽ ነበሩ። ከዚያ ቡኋላ አንኳ የአሏህን ቁጥር ስፍር የሌላቸው
ችሮታዎች ከማስታወስና አሏህን ከማላቅ ቦዝነው አያውቁም። እሳቸውን ለመፈተን አሏህ ( ) ሁሉንም ንብረት ነጥቋቸዋል። መጀመሪያ የቀንድ ከብቶቹን እንዲያጣ ፣ ከዛ አገልጋዮቹን እና የእርሻ ማሳዎቹን እንዲያጣ አደረገው። ከዛ ደግሞ ቤቱንና ልጆቹን እንዲያጣ አደረገው።
ነብዩ አዩብ ( ) ይህ ከአሏህ የሆነ ፈተና እንደሆነ ያውቅ ነበርና ሁሉንም በትዕግስት ቻለው፤ አሏህን ማውሳት (ማስታወስ) ቀጠለ።
ነገርግን ፈተናው በዚህ ብቻ አላበቃም እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆነ በሽታ መላ አካለቱን አጠቃው። አሏህን ከሚያስታውስበት እና ከሚያልቅበት ከምላሱና ከልቡ ውጭ ያለው የአካሉ ክፍል እንዳይሆን ሆነ።
የነብዩ አዩብ አካላዊ ሁኔታቸው እየተበላሸ መጣ። ምንም አይነት የለውጥ ምልክቶች አላሳይ አለ። ሆኖም ዘመዶቹን ፣ የቅርብ ጓደኞቹን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጠላው፤ ተውትም። ከእሱ ጋር የቆየችውና ፍላጎቱን አሟልታ የምትንከባከበው ደጓና ተወዳጇ ሚስቱ ብቻ ነበረች።
በዚህ ጨለማ ጊዜ ነበር ሸይጧን የነብዩ አዩብ ( ) ሁኔታ ተጠቅሞ ከጌታው ተስፋ ሊያስቆርጠው እና ለእሱ ውለታ ቢስ መሆኑን ሉያሳየው ሞከረ።
ነገርግን ታላቅ የአሏህ ባሪያ ነበርና ፈፅሞ ተስፋ የመቁረጥ ምልክት አላሳየም። ይልቁንም እንዲህ ካለ ሊቋቋሙት ከማይችሉት ስቃይ እንዲገላግለው የአሏህን እዝነት ተስፋ አድርጎ ቆይቷል።
በአንድ ወቅት ሚስቱ ባናደደችው ጊዜ ነብዩ አዩብ ( ) ተበሳጨና ጤናየ በተመለሰልኝ እንጅ መቶ ጊዜ እግርፍሽ ነበር ሲል ማለ። አሁን ብቻየን ተይኝ ተነሽ ውጭ አሏት።
አዩብ ( ) ከዚህ ጭንቀት ከዚህ ስቃይ አሏህ እንዲገላግላቸው ከልባቸው ፀለዩ። አሏህም ለጥሪው ምላሽ ሰጠ። “(ምድሩን) በእግርህ ምታው። ይህ የመታጠቢያ (የምንጭ ውሃ) ፣ ቀዝቃዛና የሚያነቃቃ መጠጥም ነው። ቤተሰቦቹን መልሰን ሰጠነው፤ ከእነሱም ጋር ልክ እንደዛው ያሉት ሰጠነው። ከእኛ በሆነ እዝነትን ለሚረዱ ሰዎች ማስታዎሻ ይሆን ዘንድ።” (አል-ቁርአን 38፡42-43)
ወዲያውኑ የነብዩ አዩብ ( ) ጤና ተመለሰላቸው። መሃላውንም እንዴት መፈፀም እንዳለበት ተጨነቀ። ተወዳጅ ሚስቱን መጉዳትም መሃላውን ማጠፍም አልፈለገገም። ቀጫጭን የሳር እቅፍ እንዲይዝና እንደሚለው ሚስቱን እንዲገርፍ በመንገር ከዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ አሏህ አወጣው።
“የቀጭን ሳር እቅፍ በእጅህ ያዝ፤ በእሱም ሚስትህን ምታ። መሃላህንም አታፍርስ።” (አል-ቁርአን 38፡44) አሏህ ነብዩ አዩብ( ) እንዲህ ሲል አመሰገነ፡- “በእርግጥ! ታጋሽ ሆኖ አገኘነው፤ ድንቅ ባሪያ! ወደኛ በተውባ ተመላሽ ነው።” (አል-ቁርአን 38፡44)