ሴቶች እና እስልምና

Author picture
በእስልምና ወንዶች እና ሴቶች የተለያየ ባህሪ ያላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ሚና አላቸው። በእስልምና ሴቶችን ማክበር መልካም እና ምስጉን ባህሪ እንዲሁም ያልተበረዘ ተፈጥሮ ምልክት ነው።
ሴቶች እና እስልምና

በእስልምና ወንዶች እና ሴቶች የተለያየ ባህሪ ያላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ሚና አላቸው።

በእስልምና ሴቶችን ማክበር መልካም እና ምስጉን ባህሪ እንዲሁም ያልተበረዘ ተፈጥሮ ምልክት ነው።

የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቲርሚዚ)

“ከእናንተ መካከል በላጩ ለሚስቶቹ ጥሩ የሆነው ነው።”

ሴት ልጅ አንድ ወንድ በመልካም ነገር ሊቀርባት ፣ ዝምድናን ሊጠብቅላት እና መልካም ነገር ሊያደርግላት የሚገባው የመጀመሪያ ሰው ናት።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይበልጥ ላገለግለው የሚገባ ማን ነው? ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ እንዲህ ብለው መለሱለት፡- “እናትህ።” ሰውየውም “ከዚያስ ማነው?” ሲላቸው “እናትህ” አሉት። “ከዚያስ ማነው?” ሲላቸው “እናትህ” አሉት። “ከዚያስ ማነው?” ሲላቸው “አባትህ” አሉት።

የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡ ዳውድ)

“ሴቶች የወንዶች ግማሽ አካል ናቸው (ተጓዳኝ ክፍሎች ናቸው)።”

  • ሴቶች በሰብአዊነታቸው ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው። እነሱ የኃጢአት ምንጭ አይደሉም። ነብዩ አደም ከጀነት (ከገነት አትክልቶች) የወጣበት ምክንያት እነሱ አይደሉም።
ሴቶች
  • ሴቶች በግል ማንነታቸው ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው። ትዳር ሲመሠርቱም ስማቸውን ወይም የቤተሰባቸውን ስም አያጡም። አይደበዝዙም ወይም የወንዶችን ማንነት አይወርሱም።
ሴት እና ወንድ እኩል የመማር እና ተገቢውን አስተዳደግ የማግኘት መብት አላቸው።
  • እስልምና ክብራቸውን እና ንጽሕናቸውን ለመጠበቅና በሚፈልጉበት ሁኔታ ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው።
  • ሴቶች የመውረስ መብት ያላቸው በመሆኑ ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው።
  • ሴቶች የገዛ ንብረታቸው በፈለጉት መንገድ የመጠቀም ሙሉ መብት ያላቸው በመሆኑ ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው።
  • ሴቶች ማህበራዊ ሃላፊነትን በመሸከም ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል ናቸው።
  • ሴት እና ወንድ እኩል የመማር እና ተገቢውን አስተዳደግ የማግኘት መብት አላቸው።

አንዲት ሴት ከባሏ ለሚያስፈልጓት ነገሮች ሁሉ እና ከዚያ በላይ ድጋፍ የማግኘት መብት አላት።

ያላገባች ከሆነ ከአባቷ ፣ እርሱ ከሌለ ደግሞ ከወንድሟ (ወንድሞቿ) ድጋፍ የማግኘት መብት አላት።

ወንድሞች ከሌሏት ደግሞ ለእርሷ በጣም ቅርብ የሆነ ዘመድ ይደግፋታል። በቀላል አነጋገር አንዲት ሙስሊም ሴት እንክብካቤ ያስፈልጋታል።

  • አንዲት ሴት የራሷን ገንዘብ በሙሉ የማቆየት መብት አላት። ቤተሰቡን በገንዘብ የመደገፍ ኃላፊነት የለባትም። ለቤተሰቡ የምታበረክተው ማንኛውም የገንዘብ መጠን የሚደረገው በራሷ ፍቃድ ብቻ ሲሆን እንደ ምጽዋት ይቆጠራል።
  • አንዲት ሴት ከባሏ ጾታዊ እርካታ የማግኘት መብት አላት።
  • አንዲት ሴት በፍቺ ጊዜ ከልጆች የገንዘብ ድጋፍ ጋር ልጆቿን የማሳደግ መብት አላት። ልጆቹን ለማሳደግ የሚያስችል በቂ ምክንያት (የጤና እክል ወዘተ) ከሌላት በስተቀር ማለት ነው።
  • ሴቶች ከተፋቱ ወይም ባሎቻቸው ከሞቱ በኋላ እንደገና የማግባት መብት አላቸው።

ነብይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አሕመድ እና ሌሎችም)

“ሦስት ሴት ልጆች ወይም ሦስት እህቶች ያሉት፣ በእነሱም ላይ (በአሳዳጊነቱ) አላህን የሚፈራ ፣ እኔና እርሱ በጀነት ውስጥ እንደዚህ እንሆናለን።” ይህንንም አመልካች ጣታቸውን እና የመሃል ጣታቸውን በማቀራረብ አሳዩ።

0%
14
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ ሴቶች በእስልምና

ሴቶችን በእስልምና ውስጥ ይመርምሩ፦ መብቶቻቸው ፣ ኃላፊነቶቻቸው እና ከጥንት የሙስሊም ታሪክ የተገኙ ምሳሌዎች፤ እንዲሁም እምነት እንዴት ስብዕናን ፣ እውቀትን ፣ የቤተሰብ እንክብካቤን እና የማኅበረሰብ አገልግሎትን እንደሚያጎላ (ይመልከቱ)።

ርዕሱን ይመርምሩ →

እነዚህ ጥያቄና መልስ  ላይ በመሞከር እራስዎን ይፈትኑ፡፡

1 / 10

Bookmark question icon

1 . ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሴት ልጆችን ስለማሳደግ ምን ጠቅሰዋል?

2 / 10

Bookmark question icon

2 . እስልምና ሰው (አዳም) ከገነት በመውደቁ (በመባረሩ) ሴቶችን ይወቅሳል?

3 / 10

Bookmark question icon

3 . ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ እናት ደረጃ ምን ጠቅሰዋል?

4 / 10

Bookmark question icon

4 . በእስልምና ሴቶች እንዴት መያዝ (መታየት) አለባቸው?

5 / 10

Bookmark question icon

5 . በእስልምና ሴቶች ከፍቺ ወይም ከባል ሞት በኋላ እንደገና እንዲያገቡ ተፈቅዶላቸዋል?

6 / 10

Bookmark question icon

6 . እስልምና ሴቶች ከወላጆቻቸው ንብረት እንዲወርሱ ወይም የንብረት ድርሻ እንዲያገኙ ይፈቅዳል?

7 / 10

Bookmark question icon

7 . በእስልምና ሴቶች በመንግሥታት ወይም በፖለቲካ ውስጥ ትልቅ (ቁልፍ) ቦታዎችን መያዝ ይችላሉ?

8 / 10

Bookmark question icon

8 . ሙስሊም ሴቶች የጋብቻ ጥያቄዎችን የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብት አላቸው?

9 / 10

Bookmark question icon

9 . በቁርአን ውስጥ ስለ ወንዶች እና ሴቶች እኩልነት ምን ተጠቅሷል?

10 / 10

Bookmark question icon

10 . እስልምና ስለ ሴቶች የመማር መብት ያስተምራል?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 22%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share