አማኝ ሴት እንቁ ናት

Author picture
አንደኛዉና ዋነኛዉ አማኝ ሴትን ልዩ የሚያደርጋት ባህሪ በአላህ ያላት የፀና እምነት ነው። በዚህ አለም የተከሰተዉ ቢከሰት መጥፎ አጋጣሚወች ቢፈጠሩ በአላህ ፍቃድ ነዉ የምትል የሆነች ናት

አንደኛዉና ዋነኛዉ አማኝ ሴትን ልዩ የሚያደርጋት ባህሪ በአላህ ያላት የፀና እምነት ነው። በዚህ አለም የተከሰተዉ ቢከሰት መጥፎ አጋጣሚወች ቢፈጠሩ በአላህ ፍቃድ ነዉ የምትል የሆነች ናት።

የትክክለኛ ሙስሊም ሴት እምነቷ ወይም አቂዳዋ ንፁህ እና ግልፅ ሲሆን በድንቁርና እድፍ ፣ በተሳሳተ አመለካከት እና ጥንቆላ ያልተበከለ ወይም ያልተመረዘ የሆነ ነዉ።

እምነቷ ያአላህን እምነት መሠረት ያደረገ ፣ አንድነቱን ፣ አምልኮ የሚገባው እሱ ብቻ መሆኑን እና ከሁሉ በላይ መሆኑን ፣ ዘላለማዊነቱን ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል መሆኑን ፣ ሙሉ አለምን ተቆጣጣሪ እና ሁሉም ነገር ወደርሱ ተመላሾች መሆናቸውን በማመን ነዉ።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ጃሲያ 45፡26)

ህያው የሚያደርጋቹህ። ከዚያም ሞትን የሚሰጣችሁ አሏህ ነው። ጥርጥር ወደ ሌላት የትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል። ግን አብዘሃኛዎቹ ሰዎች አያስቁም።

ትክክለኛ ሙስሊም ሴት ጌታዋን በትጋት ታመልካለች። እንዲሁም እስላማዊ ግዴታዋን ያለምንም ቸልተኝነት ትወጣለች።

አዘዉትራ በቀን አምስት ጊዜ ትሠግዳለች

ሶላትዋን በተደነገጉት የሶላት ሰአቶች ትሰግዳለች። የቤት ዉሰጥ ስራ ወይም እንደ ሚስትነት እና እንደ እናትነት ያለባት ግዴታ ይህን ከማድረግ አያግዳትም።

ሶላት በአላህ እና በባሪያዉ መካከል ያለች መገናኛ ናት። ሶላት የጥንካሬ ፣ የፅናት ፣ የምህረት ፣ የደስታ እና የሀጢያት እድፍን ማስወገጃ መሳሪያ ናት።

ስለዚህ ዉድ ሙስሊም እህት ወንድሞቸ ጊዜዉ ሳይጨልምብን የሞትን ቅጣት ከመቅመሳችን በፊት አሁኑኑ ወደ አላህ እንመለስ።

Related posts

Share