ከባኢር ትልቅ ሃጢያት

Author picture
ከባኢር ማለት በፍርዱ ቀን የአሏህን ከባድ እና አሳማሚ ቅጣት የሚያስከትል አሏህ የከለከለው ትልቅ ሃጢያት ነው። ይህን ወንጀል መፈፀም ጀሐነም ያስገባል፤ ጀነት ከመግባት ያስከለክላል ፣ የአሏህን እርግማን እና በዚህ አለም ህይወት የእሱን ቅጣት ያስከትላ።
ከባኢር

ከባኢር ማለት በፍርዱ ቀን የአሏህን (ሱ.ወ.ተ) ከባድ እና አሳማሚ ቅጣት የሚያስከትል አሏህ የከለከለው ትልቅ ሃጢያት ነው። ይህን ወንጀል መፈፀም ጀሐነም ያስገባል፤ ጀነት ከመግባት ያስከለክላል ፣ የአሏህን እርግማን እና በዚህ አለም ህይወት የእሱን ቅጣት ያስከትላ።

ሐድ (ብዛት ገላጭ፡ ሁዱድ) ለተወሰኑ ልክ እንደ ስርቆት ፣ ዝሙት ፣ በውሸት ሰውን በዝሙት መወንጀል ፣ ክህደት ወ.ዘ.ተ ያሉ ወንጀሎች በቁርአን እና በሱና የተቀመጠ ልዩ ቅጣት ነው።

ትልቅ ሃጢያት የፈፀመና በዚህ አለም ህይወት የተቀጣ ሰው የሚገባውን አግኝቷል። ካልተቀጣ መቶበት አለበት። በፍርዱ ቀን አሏህ ማረውም ቀጣውም ፍርዱ የእሱ ነው።

ከትላልቅ ወንጀሎች የሚያስጠነቅቁ ብዙ የቁርአን እና የሱና አስተምህሮቶች አሉ። ከትልቅ ወንጀሎች ለራቁ ሰዎች የአድን (የአትክልት ቦታ) ጀነት አሏህ እንደሚሰጣቸው አረጋግጧል፤ ቃልገብቷል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡31)

ከከለከልናችሁ ትልቅ ወንጀሎችን ከራቃችሁ፤ ትንንሽ ወንጀሎቻችሁን እናብስላችኋለን። ታላቅ መግባትን እናስገባችኋለን።

ነፍስ መግደል

ከእነዚህ ሃጢያቶች መካከል አንዳንዶቹን ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሲጠቅሱ እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

“ሰባቱ አጥፊ ሃጢያቶችን ራቁ (አስወግዱ)። ሰዎቹም ‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እነማን ናቸው? ሲሉ ጠየቋቸው። እሳቸውም ‹በአምልኮ ከአሏህ ጋር ማሻረክ ፣ ድግምት መስራትና ማሰራት ፣ በፍትህ ካልሆነ በቀር አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል ፤ አራጣ መብላት ፣ የሙት ልጆችን ገንዘብ ማጥፋት ፣ ከጦር ቦታ መሸሽ (ማፈግፈግ) እና ንፁህ እና ጨዋ አማኝ ሴቶችን ማማት ናቸው ሲሉ መለሱላቸው።”

አራጣ መብላት

አንዳንድ ትልቅ ሃጢያቶች ከሌሎቹ የበለጠ የከፉ ናቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሽርክን (በአምልኮተ አሏህ ላይ ባላነንጣ ማበጀት) ከእነሱ መካከል እንደሆነ ገልፀዋል። በቁርአን ውስጥ እንደተገለፀው ሽርክ የፈፀመን ሰው አሏህ አይምርም። ዘላለም በጀሐነም እሳት ውስጥ ይኖራል። አሏህ እንዲህ ይላል፡

ሽርክ

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡48)

በእርግጥ አሏህ በእሱ ላይ ማሻረክን ፈፅሞ አይምርም። ከዛውጭ ያለን ለሻው ሰው ይምራል።

አንድ ቀን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ከትልቅ ወንጀሎች ሁሉ ትልቅ የሆነውን ወንጀል አላሳውቃችሁምን? አሉ። አሳውቁን የአሏህ መልዕክተኛ አሉ። እሳቸውም በአሏህ ላይ ማሻረክ ፣ ወላጆችን አለመታዘዝ ነው አሉ።” ጋደም ካሉበት ቀጥ ብለው በመቀመጥ ‹የውሸት ምስክርነት ነው› አሉ። ሶሃባዎች ዝም ይላል ብለው እስኪመኙ ድረስ ደጋግመው አሉት።” (ቡኻሪ)

የውሸት ምስክርነት

ከባኢር (ትልቅ) ወንጀሎችን የምናርምበት ብቸኛው መንገድ ከልብ በመቶበት እና ወንጀሉን ከመስራት ሙሉ በሙሉ መራቅ ነው።

ሽርክ እና ሪባ ተመልከቱ

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share