ሪባ (ወለድ ፣ አራጣ) ማለት አበዳሪው ከተበዳሪው ሰው ከአበደረው ገንዘብ በላይ አስበልጦ የሚቀበለው ገንዘብ ነው። ሪባ መቀበል በእስልምና ትልቅ ወንጀል ነው።
ሪባ

ሪባ (ወለድ ፣ አራጣ) ማለት አበዳሪው ከተበዳሪው ሰው ከአበደረው ገንዘብ በላይ አስበልጦ የሚቀበለው ገንዘብ ነው። ሪባ መቀበል በእስልምና ትልቅ ወንጀል ነው። ሙስሊሞች ይህን ተግባር እንዲተው አሏህ አዟል

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 2፡278-279)

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ። አማኞች እንደሆናችሁ ከአራጣ የተቀረውን ተው። (ይህን) ብትሰሩ ከአሏህና ከመልዕክተኛው የሆነችን ጦር ተጠንቀቁ።

ሪባ ወለድ አይነቶች

ሁለት ሪባ አይነቶች

  1. ሪባ አነሲአህ (የብድር ወለድ)

ይህ የሪባ አይነት የተለያየ ቅርፅ አለው።

ሀ) አበዳሪ ለተበዳሪው በጊዜ ገደብ ወስኖ ገንዘብ በመስጠት ጊዜው ሲያልፍ እና ተበዳሪው እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር ተጨማሪ ጊዜና ተጨማሪ ገንዘብ ጨምሮ እንዲከፍል የሚያደርግበት የአራጣ ብድር ነው።

ወለድ የመክፈያ ጊዜ

ለ) ተበዳሪው ለአበዳሪው በየወሩ ቁርጥ ያለ የወለድ መጠን እየከፈለ ብድሩ የሚመመለስበት ጊዜ ሲደርስ ተበዳሪው ለአበዳሪው የወሰደውን ዋናውን ገንዘብ የሚመልስበት የአራጣ ብድር ነው።

ሐ) በተወሰነ ቀን እና ቁርጥ ባለ የወለድ መጠን ቀኑ ሲደርስ ተበዳሪ ለአበዳሪ ጠቅልሎ የሚከፍልበት የአራጣ ብድር አይነት ነው።

  1. ሪባ አል-ፈድል (የንግድ ወለድ) ይህ አይነቱ አራጣ ተበዳሪው ለአበዳሪው የሚከፍለው ተመሳሳይ የሆነ ተጨማሪ ክፍያ ሲሆን ሸቀጥ የተለዋወጡ ከሆነ ሸቀጥ ፣ ገንዘብ ከሆነ ገንዘብ ፣ ዱቄት ከሆነ ዱቄት ፣ ሩዝ ከሆ ሩዝ ጨምሮ የሚከፍሉበት የአራጣ አይነት ነው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“ወርቅ የሚከፈለው በወርቅ ፣ ብር የሚከፈለው በብር ፣ ስንዴ በስንዴ ፣ ገብስ በገብስ ፣ ተምር በተምር እና ጨው በጨው ፣ ተመሳሳይ በተመሳሳይ ነው። ክፍያ የሚፈፀመውም ወዲያውኑ ነው። ጨምሮ የሰጠ ሰው ወይም አብልጦ የጠየቀ ሰው ግብይታቸው በአራጣ ላይ ነው። ተቀባዩም ሰጭውም እኩል ጥፋተኛ (ወንጀለኛ) ናቸው።”

ሙስሊሞች የሪባ ንግድ አይነቶች ሁሉ መተውና መራቅ አለባቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“አሏህ ሪባ የተቀበለውን እና የሚከፈለውን ሰው ረግሟል። ሁለቱም ለእሷ ምስክር እና አንዱ መዝጋቢዋ ናቸው ብለዋል።” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሁሉም ወንጀለኛ መሆናቸውን ገልፅ አድርገውታል። ሆኖም “ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው” አሉ።

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የገንዘብ ግብይቶች

ጥያቄና መልስ፡ አራጣ ወይም ወለድ

‹‹አራጣ ወይም ወለድ›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 ጃቢር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) _____ ረግመዋል።

2 / 6

Bookmark question icon

2 ትክክለኛ መልሶችን ምረጥ፡ ከአራጣ መቶበት ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ ከሚከተሉት ውስጥ መሟላት ያለበት የትኛው ነው?

3 / 6

Bookmark question icon

3 በቋንቋ ደረጃ አራጣ እንደ ____ ይገለፃል።

4 / 6

Bookmark question icon

4 በሸሪአ የአራጣ ብያኔ (ሁክም) ምንድን ነው?

5 / 6

Bookmark question icon

5 ትክክለኛ መልሶችን ምረጥ፡ በአራጣ ክልከላ ላይ ካሉ ድንጋጌዎች በመካከል

6 / 6

Bookmark question icon

6 ተመሳሳይ በሆነ ነገር ላይ የአራጣ ገንዘብን በአራጣ ገንዘብ በመገበያየት ትርፍ የሚገኝበት የአራጣ አይነት የሆነው የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ሙስሊሞች የሪባ ንግድ አይነቶች ሁሉ መተውና መራቅ አለባቸው።

ከባኢር ትልቅ ሃጢያት ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share