ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

Author picture

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል ሙዕሚኑን 23:12-14

“በእርግጥ ሰውን ከጭቃ ንጥር ፈጠርነው። ከዚያም በተጠበቀ ስፍራ ውስጥ ጠብታ ፈሳሽ (የወንድና የሴት የዘር ፈሳሽ ድብልቅ) አደረግነው። ከዚያም የፈሳሹን ጠብታ ወደረጋ ደም ለወጥነው፤ ከዚያም የረጋውን ደም ትንሽ ቁራጭ ሥጋ አደረግነው፤ ከዚያም ከትንሹ ሥጋ ቁራጭ አጥንቶችን ፈጠርን፤ ከዚያም አጥንቶቹን በሥጋ አለበስናቸው፤ ከዚያም ሌላ ፍጥረት አድርገን አወጣነው። ከሰአሊዎች ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ምንኛ የተባረከ ነው! ከዚያ በኋላ በእርግጥ ትሞታላችሁ። ከዚያም [እንደገና] በእርግጥ በትንሳኤ ቀን ትነሳላችሁ።”

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡-

ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት መሆናቸውን ነው።

የሰው ልጅ ከሌሎች ዝርያዎች በዝግመተ ለውጥ አልተፈጠረም።

የተቀላቀለ የዘር ፍሬ፡ በዚህ ደረጃ የወንድና የሴት የዘር ፈሳሽ በማህፀን ውስጥ ይደባለቃል።

በዚህም ምክንያት እንቁላሉ በአላህ ፈቃድ ሊዳብር ወይም ሊሞት ይችላል። እንቁላሉ ከዳበረ የመጀመሪያዎቹ የፍጥረት ደረጃዎች ይጀምራሉ።

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ደህር 76:2

“እኛ ሰውን ከተዋሃደ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፤ እንድንፈትነውም ሰሚና ተመልካች አደረግነው።”

የወንዱ የዘር ፍሬ

የወንዱ የዘር ፍሬ እንቁላሉን ማዳበር ካልቻለ ከማህፀን ይወጣል። ነገርግን እንቁላሉን ካዳበረና ዚጎት (የመጀመሪያ ህዋስ) ከፈጠረ በብላስቱላ (የሴል ክምችት) መልክ በማህፀን ግድግዳ ላይ ይጣበቃል።

አላህ በማህፀን ላይ እንዲጣበቅ ከሻ ወደ አለቃህ ደረጃ (እንደ ሊች የሚመስል ተንጠልጣይ ነገር) ይሸጋገራል።

አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል ሐጅ 22:5

“እናንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ በመጠራጠር ውስጥ እንደ ሆናችሁ (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ)፡፡ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፣ ከዚያም ከረጋ ደም ፣ ከዚያም ከቁራጭ ሥጋ ፣ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፡፡ የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማሕፀን ውስጥ እናረጋዋለን፡፡ ከዚያም ሕፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን፡፡ ከዚያም ሙሉ ጥንካሪያችሁ ላይ ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን)፡፡ ከእናንተም የሚሞት ሰው አለ፡፡ ከእናንተም ከዕውቀት በኋላ ምንንም እንደማያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ፡፡ ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ፡፡ በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ ትላወሳለች፤ ትነፋፋለችም፡፡ ውበት ካለው ጎሳ ሁሉ ታበቅላለችም፡፡”

የረጋ ደም/ተጣባቂ ነገር፡- በዚህ መንገድ የተገለጸው በማህፀን ላይ ስለሚጣበቅ ነው። ልክ እንደ ሊች በሌሎች ፍጡራን ደም እንደሚመገብ ማለት ነው።

የሚጀምረው የወንዱ የዘር ፍሬ የሴቷን ሁለተኛ ደረጃ እንቁላል የፕላዝማ ሽፋን ሲነካ ጀምሮ የእናት እና የአባት ክሮሞዞሞች በዚጎት የመጀመሪያ ሚቶቲክ ክፍፍል ሜታፋዝ ላይ እስከሚዋሃዱበት ጊዜ ድረስ ነው።

ሀ, በበርካታ የወንድ የዘር ፍሬዎች የተከበበ ሁለተኛ ደረጃ እንቁላል ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ኮሮና ራዲያታን ዘልቀዋል።

እንደታኘከ ነገር፡ ፅንሱ በመልክ የታኘከ ነገር ስለሚመስል እንደዚህ ተብሎ ተገልጻል።

ስፐርም

የፅንስ የጎን እይታ (ከ24 እስከ 25 ቀናት)። ለ. በ ‘አላቃህ’ ደረጃ በአንጭላ እና በሰው ልጅ ፅንስ መካከል ያለውን ተመሳሳይነት የሚያሳዩ ስዕሎች። (ከዶ/ር ኪት ሙር፣ ዘ ዴቨሎፒንግ ሂውማን ገጽ 71 – 7ኛ እትም የተወሰደ)

በግምት የ21 ቀን ፅንስ ውስጥ ያለ የመጀመሪያ ደረጃ የልብ እና የደም ሥር ስርዓት ከግራ በኩል ሲታይ የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫ።

ተጣምረው የተመጣጠኑ የደም ሥሮች ጊዜያዊ ደረጃን ይመልከቱ።

(ኪት ሙር) እያንዳንዱ የልብ ቱቦ ከጀርባ በኩል ወደ ኋላ ወደሚያልፈው የጀርባ ወሳጅ ቧንቧ ይቀጥላል።

የፅንሱ እና የከረጢቶቹ ውጫዊ ገጽታ በፅንሱ ውስጥ በአንጻራዊነት ከፍተኛ መጠን ያለው ደም በመኖሩ ምክንያት የረጋ ደም ይመስላል።

• ማዳበሪያ፡ በሰዎች ውስጥ ማዳበሪያ የሚከሰተው የወንድ የዘር ፍሬ (spermatozoon) የጄኔቲክ ቁስ ከእንቁላሉ (ovum) ጋር ሲዋሃድ ነው። በሰዎች ውስጥ ማዳበሪያ የሚከሰተው በማህፀን ቱቦ (የfallopian ቱቦ) ሩቅ ሶስተኛ ክፍል ውስጥ ነው።   

የተተከለ ፅንስ ክፍል (በግምት 21 ቀናት)። በዚህ ሥዕላዊ መግለጫ ላይ ፅንሱ በእናቱ ማህፀን ውስጥ በ”አላቃህ” ደረጃ ላይ ተንጠልጥሎ እናያለን።

”በእርግጥ የሰውን ልጅ እንፈንትነው ዘንድ ከፍትወት ጠብታ፡፡” (አል-ቁርአን 76፡2)  

  • የአጥንቶች አፈጣጠር
  • የአጥንቶች በስጋ መሸፈን
የሰው ሽል የማክሮ ፎቶግራፍ
የደረጃ 13 የሰው ሽል የማክሮ ፎቶግራፍ። (Keith Moore) ትክክለኛ መጠን 4.5 ሚሜ  
ፅንስ

ምስል፡ በአንድ የታኘከ ማስቲካ ቁራጭ እና በእውነተኛ የፅንስ ፎቶ መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ተመልከት።

እንዴት ሊሆን ይችላል አንድ ያልተማረ ሰው ስለ ፅንሱ እንደዚህ ያሉ ግልጽ ዝርዝሮችን ሊሰጥ ይችላል? በእርግጥ ይህ ከአሏህ የሆነ መገለጥ ብቻ ነው!

በዚህ ደረጃ ያለው ፅንስ በመልክ ከታኘከ ነገር ጋር ይመሳሰላል።

ምክንያቱም በፅንሱ ጀርባ ላይ ያሉ ሶማይትስ በተወሰነ መልኩ በተኘከ ንጥረ ነገር ውስጥ ያሉ የጥርስ ምልክቶችን ይመስላሉና።  

  • የፅንሱ ወደ ተለየ ቅርጽ ማደግ፡ በዚህ ውስጥ የሰውነት ክፍሎች ተመጣጣኝ ይሆናሉ፤ እናም ህይወት ይሰጠዋል።

የሰው ልጅ ፅንስ በሶስት የጨለማ ሽፋኖች ውስጥ በርካታ ደረጃዎችን ያልፋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ዙመር 39:6

“ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከግመልና ከከብት ፣ ከፍየል ፣ ከበግ ስምንት ዓይነቶችን (ወንድና ሴት) አወረደ፡፡ በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ (ሙሉ) መፍጠርን ይፈጠራችኋል፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ስልጣኑ የእሱ ብቻ ነው፡፡ ከእሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ?”

ይህ አንቀጽ ፅንሱ በሶስት ሽፋኖች ወይም ንብርብሮች እንደተሸፈነ ይገልጻል።

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ጨለማዎች” ተብለው ተጠቅሰዋል። ውሃ ፣ አየር ፣ ብርሃን እና ሙቀት ወደ እነዚህ ሽፋኖች ዘልቀው ሊገቡ አይችሉም። በዓይን እንኳ አይታዩም።

ዶክተር ሞሪስ ቡካይ 1 እንዲህ ብሏል፡-

ዶክተር ሞሪስ ቡካይ
ዶክተር ሞሪስ ቡካይ

“የዚህ ዘመን የቁርአን ተርጓሚዎች በዚህ አንቀጽ ውስጥ በእርግዝና ወቅት ህፃኑን የሚከላከሉ ሶስት የሰውነት ሽፋኖች እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ እነሱም የሆድ ግድግዳ ፣ የማህፀን አካል እና የፅንሱ አካባቢ (ፕላሴንታ ፣ ሽል ሽፋኖች ፣ የአሞኒቲክ ፈሳሽ) ናቸው።” 2

ፅንሱም ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ላይ ይቀመጣል። አላህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱ ሙርሰላ 77:20-23

“ከደካማ ውሃ አልፈጠርናችሁምን? ከዚያም በተጠበቀ ስፍራ (ማህፀን) ውስጥ አኖርነው። እኛም ለካነው፤ እኛም ምንኛ አሳማሪ ልኬተኞችች ነን!”

ዶ/ር ጌር ሚለር
ዶ/ር ጌር ሚለር

ዶ/ር ጌር ሚለር 3 እንዲህ ይለናል፦ አንድ ጋዜጠኛ ፕሮፌሰር ኪዝ ሙርን 4 እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ ‘ምናልባት አረቦች ስለነዚህ ነገሮች  ማለትም ስለ ሽል (ፅንስ) ገለፃ ፣ ስለ አፈጣጠሩ ፣ እንዴት እንደሚለወጥ እና እንደሚያድግ አውቀው ይሆናል ብለው አያስቡም?

ምናልባት ሳይንቲስቶች አልነበሩም ይሆናል፤ ነገርግን ምናልባት በራሳቸው ጊዜ ያልተራቀቀ ቀዶ ጥገና በማድረግ  ሰዎችን በመሰንጠቅ እነዚህን ነገሮች መርምረው ሊሆን አይችልም?

ፕሮፌሰር ኪዝ ሙር
ፕሮፌሰር ኪዝ ሙር

ፕሮፌሰሩም ወዲያውኑ ጋዜጠኛው እጅግ በጣም ወሳኝ የሆነ ነጥብ እንደሳተ አመላከቱት። በፊልሙ ላይ የታዩትና የቀረቡት ሁሉም የሽል (ፅንስ) ስላይዶች በአጉሊ መነጽር (ማይክሮስኮፕ) አማካኝነት ከተነሱ ምስሎች የተገኙ ነበሩ።

እሳቸውም አሉ፦ ‘ከአስራ አራት መቶ ክፍለ ዘመናት በፊት ማንም ሰው የስነ-ፅንስን ጥናት (embryology) ለማወቅ ቢሞክር በፍጹም ሊያየው አይችልም ነበር!’” ሲሉ መለሱለት።

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

በቅዱስ ቁርአን ውስጥ ስለ ሽሉ (ፅንስ) ገጽታ (አፈጣጠር) የተሰጡት ገለፃዎች በሙሉ ፍጡሩ ገና በዓይን ለማየት በማይቻልበት ደረጃ ላይ እያለ ያለውን ሁኔታ የሚመለከቱ ናቸው።

ስለዚህ ይህንን ለማየት አንድ ሰው አጉሊ መነጽር (ማይክሮስኮፕ) ያስፈልገዋል።

እንዲህ አይነቱ መሳሪያ ደግሞ መኖር ከጀመረ ከሁለት መቶ አመታት በላይ እንኳ አልሆነውም።

ዶ/ር ሙር በማሾፍ (ወይም ‘በጥያቄ መልክ’) እንዲህ አሉ፦

“ምናልባት ከአስራ አራት መቶ ክፍለ ዘመናት በፊት አንድ ሰው በድብቅ አጉሊ መነጽር ኖሮት ይህንን ምርምር ምንም አይነት ስህተት ሳይሰራ አካሂዶ ይሆናል።

ከዚያም በሆነ መንገድ መሐመድን አስተምሮት ይህንን መረጃ በመጽሐፉ (በቁርአን) ውስጥ እንዲያስገባ አሳምኖት ይሆናል።

ከዚያም መሳሪያውን አጥፍቶ ይህንን ነገር ለዘላለም ሚስጥር አድርጎት ይሆናል። ይህንን ታምናላችሁ?

እንዲህ አይነቱ እጅግ አስቂኝ የሆነ መላምት (ቲዎሪ) ስለሆነ ማስረጃ ካልመጣላችሁ በስተቀር በፍጹም ልታምኑ አይገባም።” እሳቸው “ይህን በቁርአን ውስጥ የሚገኘው መረጃ እንዴት ያብራሩታል?” ተብለው ሲጠየቁ፣

የዶ/ር ሙር መልስ “ይህ ሊሆን የሚችለው በአምላካዊ መገለጥ (ወህይ) ብቻ ነው!” የሚል ነበር።

ዶ/ር ጀራልድ ሲ. ጎሪንገር
ዶ/ር ጀራልድ ሲ. ጎሪንገር

ዶ/ር ጀራልድ ሲ. ጎሪንገር 5 እንዲህ ብለዋል፦ “ይህ ገለጻ በባህላዊ የሳይንስ መዛግብት ውስጥ የተመዘገቡት የተለያዩ የሰው ልጅ የሽል እና የፅንስ እድገት ደረጃዎች ነው፡፡ከመመዝገባቸው ከብዙ መቶ ክፍለ ዘመናት በፊት የቀደመ ነው።”

የግርጌ ማስታወሻ

  1. ሞሪስ ቡካይ በፓሪስ ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ጥገና ክሊኒክ ኃላፊ ነበሩ። ↩︎
  2. (2) ቡካይ፣ ሞሪስ። The Bible, the Qur’an and Science: The Holy Scriptures Examined in the Light of Modern Science. 2010. Archive.org. ድረ ገጽ። 5 መስከረም 2017። https://archive.org ↩︎
  3. አብዱል-አሃድ ዑመር ካናዳዊ ሙስሊም ነው። ወደ እስልምና ከመግባታቸው በፊት የክርስትና የሃይማኖት ምሁር እና ፓስተር በመሆናቸው ይታወቃሉ። ↩︎
  4. ኪት ሙር በዓለም የታወቀ የፅንስ ጥናት ባለሙያ ናቸው። የካናዳ የሰውነት ተመራማሪዎች ማኅበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ነበሩ፣ ↩︎
  5. ዶ/ር ጀራልድ ሲ. ጎሪንገር በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ አሜሪካ በሚገኘው የሕክምና ትምህርት ቤት የሴል ባዮሎጂ ክፍል የሕክምና ስነ-ፅንስ (Medical Embryology) ኮርስ ዳይሬክተር እና ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ↩︎

Related posts

ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22) ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች

Read More »

ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል አላህ እንዲህ ይላል፡- ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ

Read More »

ቁርአን ስለ አጽናፈ ዓለም መስፋፋት

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- እነዚህ አንቀጾች የምንኖርበት አጽናፈ ዓለም በህዋ ውስጥ ያለማቋረጥ እየሰፋ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ አጠቃላይ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share