የቁርአን ትንተና እና በቁረአን ማስተንተን

Author picture
የቁርአን ትንተና እና በቁረአን ማስተንተን ሁለት ትልቅ ተጋባራቶች ናቸው። ይህም  ሃያሉ አሏህ አንድን ሙስሊም ሰው ከቃሉ የፈለገውን ነገር እንዲያውቅ እና በእሱም እንዲሰራበት ያስችለዋል።
የቁርአን ትንተና እና ማስተንተን

የቅዱስ ቁርአን ትርጉም ትንተና እና ማስተንተን ሁለት ትልቅ ተጋባራቶች ናቸው። ይህም  ሃያሉ አሏህ አንድን ሙስሊም ሰው ከቃሉ የፈለገውን ነገር እንዲያውቅ እና በእሱም እንዲሰራበት ያስችለዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ማስተንተን ምን ማለት እንደሆነ ፣ ስለ ተፍሲር (ትንተና) ምንነት እና ጠቀሜታ ትማራላችሁ።

የጽሁፉ አላማ

  1. የቁርአን ትርጉም ትንተና እና በቁርአን ማስተንተን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ
  2. የቁርአን ማብራሪያ እና በእሱ ማስተንተን ያለው ደረጃ እና አስፈላጊነቱን ታውቃላችሁ
  3. የቅዱስ ቁርአን ትርጉም የሚብራሩበትን መንገዶች ታውቃላችሁ
  4. አስፈላጊ የሆኑ እና የታወቁ የቁርአን ትንተና መጽሐፍትን ታውቃላችሁ

የቅዱስ ቁርአን ትንተና እና በቁርአን ማስተንተን

ተፍሲር የሚለው የአረብኛ ቃል ‹ገለፃ ወይም ትንተና› የሚል ትርጉም አለው። በጥቅሉ ተፍሲር ማለት የቅዱስ ቁርአን ሃተታ ሲሆን የማብራራት ጥበብ ፣ ትርጉሙን የመግለፅ እና ህጎቹን የማውጣት ሂደት የሚገልፅ ነው።

ቁርአንን ተፍሲር የሚያደርግ ሰው ሙፈሲር ይባላል። ብዙ ቁጥርን ለመግለፅ ሙፈሲሩን የሚለውን ቃል እንጠቀማለን።

ሁሉም ሙስሊም ሰው ቁርአንን በትክክል ማንበብ ፣ በእሱ ማስተንተን ፣ ስለ ትርጉሞቹ ፣ ስለ ትዕዛዛቱ እና ስለ ክልከላዎቹ ማሰብ ፣ ማብራሪያውን እና ህግጋቱን መማር አለባቸው። የዚችን አለም እና የመጭውን አለም ደስታ ለማግኘት በእሱ መስራት አለባቸው።

የተድቢር (የማስተንተን) ትርጉም

ማስተንተን፡ ከቁርአን አንቀፆች ጋር መቆም ፣ በእነሱ ላይ ማስተንተን እና ጥቅም ላይ ለማዋል ከእነሱ ጋር ቁርኝት መፍጠር ነው።

ኢብን ተይሚያ አሉ፡ ቁርአንን ለመረዳት የመጀመሪያው ማድረግ ያለባችሁ ነገር እራሱ ቁርአንን መመልከት ነው። ምክኒያቱም ቁርአን ብዙ ጊዜ የሆነን ነገር አንድ ቦታ ላይ ያነሳል፤ ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ በዝርዝር ይገልፀዋልና ነው።

ሁለተኛው ማድረግ ያለባችሁ ነገር የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ገለፃ መመልከት ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የቁርአንን ቃላት ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ትርጉማቸውንም አብራርተዋል። ሶስተኛው መደረግ ያለበት ነገር የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃባዎች ትንተናን መመልከት ነው።

ምክኒያቱም ከማንም በላይ ቁርአንን ተረድተውታል ፣ ራዕዩን መገለጥ ተመልክተዋል ፣ የተገለጠበትን መንገድ ያውቃሉ ፣ ትርጉሞቹን በቀጥታ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተምረዋልና ነው።

አራተኛው መደረግ ያለበት ነገር ከሶሃቦች ቡኋላ ያሉ ሁለት ትውልዶች ፣ ታቢኢዩን እና ተበአተ ታቢኢይን የሰጡትን ማብራሪያ መመልከት ነው። ምክኒያቱም ትንተናቸው በመጤ ሃሳቦች ያለተበረዘ ነው።

በቅዱስ ቁርአን አንቀፆች ላይ የሚያስተነትን ሰው ማሰላሰሉ (ማስተንተኑ) እና መረዳቱ ትክክል ይሆን ዘንድ አጠቃላይ ትርጉሙን ማወቅ አለበት።

በቁርአን ማስተንተን ያለው ደረጃ

ሁሉም ሙስሊሞች በቁርአን ማስተንተን ፣ አንቀፆቹን እና ትርጉሙን መረዳት ፣ በእነሱም መሰረት መኖር አለባቸው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሷድ 29)

“ወደ አንተ ያወረድነው የተባረከ መጽሐፍ ነው፤ በአንቀፆቹ ላይ እንዲያስተነትኑ እና የአዕምሮ ባለቤቶች እንዲያስታውሱ ነው።”

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሙሐመድ 24)

“በቁርአን አያስተነትኑምን? ወይስ (እሱን ለመረዳት) ልቦቻቸው ተቆለፉ?”

የተፍሲር ትርጉም

ተፍሲር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም ማብራሪያ ነው።

የተፍሲር (የትንተና) ጠቀሜታ እና አስፈላጊነት

የተፍሲር እውቀት (ሳይንስ) በጣም ጠቃሚ ከሆኑ እውቀቶች ውስጥ አንዱ ነው። ምክኒያቱም ከሃያሉ አሏህ መጽሐፍ  ጋር የተያያዘ ነውና። እንዲሁም የአሏህን ቃል ለመረዳት ያስችላል። በተፍሲር እውቀት የቅዱስ ቁርአን ትርጉሞች ይታወቃሉ። ሙስሊም ሰው መልካም ስራ እንዲሰራ ይረዳዋል፤ የአሏህን ውዴታ እና ጀነት ለማግኘት ያስችለዋል። ይህም በቅዱስ ቁርአን የተጠቀሱ ትዕዛዛዘትን በመፈፀም ፣ ክልከላዎቹን በመከልከል ፣ ከታሪኮቹ ትምህርት በመውሰድ ፣ በዜናዎቹ በማመን  ነው። በተፍሲር እውቀት አንድ ሰው እውነትን ከውሸት መለየት ይችላል፡፡ ከአንቀፆቹ ትርጉም እና ከሚያመለክቱት እውነተኛ ነገር ግራ እንዳይጋባም ይረዳዋል።

ሶሃቦች የቁርአን ትርጉም እና ተፍሲር ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለማወቅ የነበራቸው ጉጉት

እነዚያ ብርቅየ ሶሃቦች ከቁርአን ለመረዳት የከበዳቸው ነገር ሲኖር ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይጠይቁ ነበር። ይህ አንቀፅ

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንአም 82)

“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን በበደል ያልሸፈኑ፤”

የሚለው በተገለጠ ጊዜ አብዱሏህ ቢን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦች ይህ ከብዷቸው ነበር። እነሱም፡ ማነው ከእኛ ውስጥ እራሱን ያልበደለ? አሉ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሱረቱ ሉቅማን 13) (ቡኻ 6937 ፣ ሙስሊም 124)

‹‹እንደምታስቡት አይደለም፤ ነገርግን ሉቅማን ለልጁነ እዳለው ነው አሉ። ‹‹ልጄ ሆይ! በአሏህ ላይ አታጋራ (ባላንጣ አታብጅ)፤ በእርግጥ ሽርክ (በአሏህ ላይ ማጋራት) ትልቅ በደል ነውና።››

የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እና ማብራሪያ ማጣቀሻ ዘዴዎች

  1. የቁርአን ተፍሲር በቁርአን (ቁርአንን በቁርአን መተንተን)
  2. ቁርአንን በሱና መተንተን
  3. የሶሃቦች ትንተና
  4. የታቢኦች (ከሶሃች በኋላ የነበሩ ትውልዶች) ትንተና

አንደኛ፡ ቁርአንን በቁርአን መተንተን

ቅዱስ ቁርአን ያወረደው (የገለጠው) ሃያሉ አሏህ በመሆኑ  በእሱ ሊያሳውቀን የፈለገውንም አዋቂ ነው። ለምሳሌ፡ ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ዩኑስ 62-63)

“አዋጅ! የአሏህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ አያዝኑምም። እነሱም እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩት ናቸው።”

በእርግጥ የአሏህ ወዳጆች የሚለው በዚህ አንቀፅ ‹‹እነዚያ ያመኑ እና ይፈሩት የነበሩት›› በሚል ተብራርቷል።

ሁለተኛ፡ የቁርአን ትንተና በነብዩ ሱና

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከአሏህ የተገለጠላቸውን ራዕይ በእሱ ስም ለሰዎች እንዲያስተላልፉ የተመረጡ በመሆናቸው ነው። አሏህ በቃሉ ማለት ስለፈለገው ነገር ከሁሉም ሰው በላይ ያውቃሉና ነው። ለምሳሌ፡ ቀስት በራሱ ጥንካሬ እንደሆነ የተናገሩበት የኡቅባ ቢን አምር (ረ.ዐ) ዘገባ ያሳያል።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 1917)

‹‹ኡቅባ እንዲህ አለ፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሚንበር ላይ ሆነው እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡ ‹‹ከሃይል በእነሱ ላይ የቻላችሁትን ሁሉ አዘጋጁ።›› (ሱረቱል አንፋል 60) ‹‹አዋጅኧ ጥንካሬ ቀስትትን ያካትታል፤ አዋጅ ጥንካሬ ቀስትን ያካትታል፤ አዋጅ ጥንካሬ ቀስትን ያካትታል።››

ሶስተኛ፡ የሶሃቦች ማብራሪያ

በዚህ ጉዳይ ላይ ሶሃቦች የበለጠ እውቀት ያላቸው ነበሩ። ምክኒያቱም ለቁርአን እና ላለፉበት ሁኔታ ምስክሮች በመሆናቸው ነው። እንዲሁም የተሟላ ተረድኦ ፣ ትክክለኛ እውቀት እና የመልካም ስራ ባለቤቶች በመሆናቸው ነው።

ለዚህ ምሳሌ ተከታዩ የአሏህ ንግር ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 43)

“ብትታመሙ ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከእናንተ አንዱ ለተፈጥሮ ጥሪ መልስ ሰጥቶ (ተፅዳድቶ) ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩ”

በጦበሪ ተፍሲር (ማብራሪያ) መሰረት ‹‹ብትነካኩ›› የሚለው የግብረ ስጋ ግኑኝነት እንደሆነ ተገልፃል። (389/8) ኢብን አባስ (ረ.ዐ) ትክክል ነው ብሏል።

አራተኛ፡ የታቢኦች ተፍሲር

ታቢኦች ከሶሃቦች በኋላ የነበሩ በላጭ ህዝቦች በመሆናቸው እና ከፍላጎቶቻቸው የተጠበቁ በመሆናቸው ምክኒያት የሶሃቦችን የቁርአን ትንተና ጠብቀው አቆይተዋል። ታቢኦች ከእነሱ በኋላ ከመጡ ህዝቦች የበለጠ ቁርአንን ለመረዳት የቀረቡ ነበሩ።

የቁርአን ማብራሪያ በተመለከተ የሙስሊም ሰው ግዴታ

ቁርአንን ለመረዳት ፣ ትጉሙን ለማወቅ የሆነ ነገር አሻሚ የሆነበት ሰው የተፍሲር ማጣቀሻ መጽሐፍት እና የቁርአን አንቀፆችን ትርጉም በመግለፅ እና በማብራራት የታወቀ ሊቃውንትን ማብራሪያ መመልከት አለበት።

የቅዱስ ቁርአን ትንተና ለሁሉም ሙስሊም አይደለም። ይልቁንም የትንታኔው እውቀት ላላቸው ሰዎች ነው። ሆኖም እውቀቱ የሌላቸው ሙስሊሞች ያለ እውቀት ወደዚያ መሄድ የለባቸውም። ሙፈሲሩ (ተንታኙ) የሚያብራራው በሃያሉ አሏህ ስም ነው። በቃሉ ማስተላለፍ ለፈለገው ነገር ምስክር ነው። ይህን ምስክርነትም በስራው አጉልቶ ያሳያል። ስለ አሏህ ያለ እውቀት እንዳይነገር እና በከለከለው ነገር ውስጥ እንዳይወድቅ ፣ ለፍርድ በመቆሚያዋ ቀን እንዳይዋረድ በመስጋት ይጠነቀቃል። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አዕራፍ 33)

“ጌታየ እርም ያደረገው መጥፎ ስራዎችን ፣ ከእሷ የተገለፀውን እና የተደበቀውን ሃጢያትንም ፣ ያለ አግባብ መበደልን ፣ በእሱ ማስረጃ ያላወረደበትን በአሏህ ማጋራታችሁን እና በአሏህ ስም መናገራችሁ ብቻ ነው በላቸው።”

ጠቃሚ የቁርአን ተፍሲር መጽሐፍት

የቁርአን ተፍሲር መጽሐፍት

የቁርአን ተፍሲር ማብራሪያ ተብለው የተለዩ ብዙ መጽሐፍት አሉ። ሁሉም በቅቡልነታቸው ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ባለመሆናቸው የትንተና ህግጋትን አጥብቆ የተከተለን ጽሐፊ ማብራሪያ ላይ መደገፍ አለባቸው። ከነዚህ የታወቁ ስራዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

  1. ጃሚዕ አል-በያን የቁርአን ማብራሪያ በኢማም ቢን ጀሪር አጦበሪ
  2. የቅዱስ ቁርአን ማብራሪያ በኢማሙ ኢብን ከሲር አዲመሽቂ
  3. ተፍሲር አል-ከሪም አረህማን በአልመናን ቃል በሼህ አብዱረህማን አሰአዲ
  4. ቀላል ማብራሪያ በእውቅ ሊቃውንቶች፡ አሳታሚ ንጉስ ፋህድ የቁርአን ህትመት፤ መዲና
  5. ተፍሲሩል ቁርአን አል-አዚም በኢማም ኢብን ከሲር
  6. አል-ጃሚ ሊ አህካሚል ቁርአን በኢማም አቡ አብዱሏህ አል-ቁርጡቢ
  7. ተፍሲር ሩሀል..ማዕኒ ፊ ቁርአነል አዚም ….በኢማሙ ሙሐመድ አል-አሉሲ…አል-ሐነፊ
0%
1
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

ጥያቄና መልስ፡ የቅዱስ ቁርአን ተፍሲር

የቅዱስ ቁርአን ተፍሲር (ትንተና) ፈተና 8 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 8

Bookmark question icon

1 እነዚያ ብርቅየ ሶሃቦች (ረ.ዐ) ከቁርአን የከበዳቸውን ነገር ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አይጠይቁም ነበር። ምክኒያቱም ቁርአን ለሁሉም ሰው ግልፅ ሰለነበር።

2 / 8

Bookmark question icon

2 ያለ እውቀት በቁርአን ማብራሪያ ላይ የተናገረ ሰው ሁክሙ (ሸሪአዊ ብያኔው) ምንድን ነው?

3 / 8

Bookmark question icon

3 በቁርአን ማስተንተን ሸሪአዊ ብያኔው ምንድን ነው?

4 / 8

Bookmark question icon

4 የቅዱስ ቁርአን ተፍሲር (ማብራሪያ) መጽሐፍ ጽሐፊ የትኛው ነው?

5 / 8

Bookmark question icon

5 ፅሁፎቹን ከፍ እና ዝቅ በማድረግ የቁርአን የትንተና ዘዴዎችን በቅደም ተከተላቸው አስቀምጡ።

የቁርአን ማብራሪያ በሱና
የታቢኦች ማብራሪያ
የሶሃቦች ማብራሪያ
ቁርአን በቁርአን ማብራሪያ

6 / 8

Bookmark question icon

6 የተፍሲር ትሩፋት እና ጠቀሜታ ከአሏህ መጽሐፍ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው።

7 / 8

Bookmark question icon

7 የቅዱስ ቁርአን ትክክለኛ ማብራሪያ ላይ ለመድረስ የሚፈልግ ሰው

8 / 8

Bookmark question icon

8 ማስተንተን ምነድን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 50%

0%

ቅዱስ ቁርአን ተመልከቱ

Related posts

ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22) ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች

Read More »

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡- ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት

Read More »

ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል አላህ እንዲህ ይላል፡- ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share