የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 5

Author picture

Table of Contents

ክፍል አምስት

የኡመር ኢብን አል-ኽጧብ (ረ.ዐ) ኢስላምን መቀበል

ኡመር (ረ.ዐ) ኢስላምን የተቀበለው ሐምዛ (ረ.ዐ) ኢስላምን ከተቀበለ ከሶስት ቀን መሳሪያ ታጥቆ በከረረ መልኩ ስራውን ከቤቱ ጀመረ።

እህቱ ፋጢማ ቢንት ኸጧብ እና ሰኢድ ኢስላምን ተቀብለው ስለ ነበር ወደ ቤታቸው ሄደና ኸባብ ከቁርአን ያስተማራችሁ የት አለ አለና ሁለታቸውንም መታቸው። ግንባራቸውም መድማት ጀመረ፤ እህቱም በመገረም እስልምናን ተቀብለናል የፈለከውን ነገር ልታደርግ ትችላለህ አለችው።

የኡመር ኢብን አል-ኽጧብ (ረ.ዐ) በእምነታቸው ቅን ሁነው ስላገኛቸው ከተማሩት ነገር እንዲቀሩለት ፈለገ፤ ፋጢማም ሱራ ሐዲድ ስትቀራለት ይህን ቂርአት በመስማቱ ተደሞ ማልቀስ ጀመረ።

በመቀጠል ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በመሄድ ሸሃዳ ብሎ ኢስላምን ተቀበለ። ኡመር (ረ.ዐ) በጣም ጠንካራና ሃይለኛ የነበረ ሲሆን የእሱ ኢስላምን መቀበል ለሙስሊሞች የበለጠ ጥንካሬ ፈጠረላቸው።

ኡመር (ረ.ዐ) ጀግንነቱን ይዞ ወደ ኢስላም መግባቱና የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ቅን አጋር መሆኑ የአረመኔዎችን ልብ አራደው። ኢስላምን መቀበሉን ካወጀም ቡሏላ ካዕባ ውስጥ ሶላት ሰገደ። ይህን ተከትሎ የመካ አረመኔዎች የበለጠ አዘኑ።

የአቡጧሊብ እና የኸድጃ (ረ.ዐ) ህልፈተ ህይወት

በአስረኛው አመተ ሂጅራ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አጎት የሆኑት አቡጧሊብ ሞቱ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያደጉት በአጎታቸው አቡጧሊብ እንክብካቤና ድጋፍ የነበር ሲሆን የመካ ህዝቦች በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ላደረሱባቸው የከፋ ጥላቻና በደል አጎታቸው አቡጧሊብ ትልቅ የፍቅርና የእርዳታ (የድጋፍ) ሃይል ነበሩ።

ኪዚያ ብኋላ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስት ኸድጀቱል ኩብራ (ረ.ዐ) አረፈች፤ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በጣም አዘኑ። ከማንም በፊት በመጀመሪያው ቀን ነበር ኢስላምን የተቀበለችው። ሁሉም የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጉዳይ ከሷ ጋር ነበር። በቅንነት የሚወዷት ታላቅ ሴት ስትሆን በሞቷ በጣም አዘኑ። ያ አመት የሃዘን አመት ተብሎ ተሰየመ።

ነብዩ ሙሐመድ በጧኢፍ የሰጡት ትመህርት

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ውጭ ለነዛ ውስጣቸው በጥላቻ ለተሞላ ህዝቦች ኢስላምን ማስተማር ጀመሩ። የጧኢፍ ህዝቦች እንደሚከተሏቸው አስበው የነበረ ቢሆንም ውጤቱ ግን ከዚህ በተቃራኒ ነበር።

በዚህ ጉዞ ወቅት የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አገልጋይ ዘይድ ቢን ኸሪሳ (ረ.ዐ) ከሳቸው ጋር ነበር። በመካና በጧኢፍ መንገድ መካከል ከሁሉም ጐሳዎች የሚመጡ ሰዎችን ሁሉ አስተማሩ።

ነገርግን በሚያሳዝን ሁኔታ በጣም ደብድበውና ጐድተው ከጧኢፍ አስወጧቸው። ይህ ድብደባ የበፊቶቹ ነብያቶች ከደረሰባቸው ግፍ በላይ አሳማሚ ነበር።

ሆኖም ትንሽ እረፍ ካሉ ቡኋላ የመላዕኮች አለቃ የሆነው ጅብሪል (ዐ.ሰ) በነሱ ላይ ዱአ አድርግና በተራራዎች መሃል ድምጥማጣቸውን ላጥፋቸው አላቸው።

ነገርግን ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን አላደረጉም። ይልቁንስ እጃቸውን አነሱና እነዚህ ሰዎች የሚሰሩትን አያውቁምና መጭ ትውልዳቸውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ምራቸው አሉ።

አጅብ ለአለም እዝነት ተደርገው የተላኩ ድንቅ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ)!!! ቡኋላ ላይም የጧኢፍ ህዝቦች ከሁሉ በላይ የሆኑ ሙስሊሞች ሆኑ።

ኢስላም በመዲና

የመዲና ህዝቦች አብዛሃኛውን ጊዜ ሐጅ ለማድረግ ወደ መካ ይመጣሉ፤ በሐጅ ስብሰባው ላይ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሰዎችን ይሰብኩ ነበር። በ9ኛው ነበውይ ሰዋኢድ ቢን ሳሚት ስብሰባ ላይ የመዲና ታላቅ ገጣሚ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም በመደመሙ ኢስላምን መውደድ ጀመረ።

ለመዲና ወጣቶችም የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) እውነተኛነት አሳወቃቸው። እናም በ10ኛው ነበውይ ስድስት ተሰጥኦ ያላቸው የመዲና ሰዎች በሐጅ ወቅት ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ተገናኙ፤ እነሱም ጋር ኢስላምን ሊቀበሉ ከመዲና የመጡ 12 ሰዎች ነበሩ።

እናም የመዲና የአውስ ጐሳ መሪ ኢስላምን ተቀበለ። በ12ኛው ነበውይ 72 ሰዎች ከመዲና ለሐጅ ወደ መካ በመጡ ጊዜ ኢስላምን ተቀበሉ። ይህን ተከትሎ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የመካ ሙስሊሞች ወደ መዲና ከተማ ይሰደዱ ዘንድ ፈቀዱላቸው።

በመዲና ጐሳዎች ውስጥ ከሚገኙ ጎሳዎች መካከል የኸዝረጅ ጎሳ አባል የሆኑ ሰዎች በሌላኛው መዲና ላይ በሚገኘው በአውስ ጎሳ ላይ ጠላት ሁነው ተነሱባቸው፤ እርስበርሳቸውም ባላንጣዎች ሆኑ።

እነዚህ የኸዝረጅ ህዝቦች ከቁረይሾች ጋር ሊመሳጠሩ ፈለጉ። ነገርግን ሃያሉ አሏህ ባሮቹን ባስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እያለ እንግዳ በሆነ ነገር ረዳቸው።

በዚህ ከተማ ሰዎች ስለ ኢስላም ይጠይቁና ይመራመሩ ጀመር። ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ባገኙ ጊዜ ኢስላም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ጠየቋቸው። ስለ ምንድ ነው የሚቆመው? ይህ ሐይማኖት ለሰው ልጅ አዳኝ እርግጠኛ (ትክክለኛ) መለኮታዊ እውነታ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉም ጠየቋቸው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በጣም በትጋት ሰበኴቸው።

ለጥያቄያቸውም ማስረጃ የሚሆኑ አያቶችን ቀሩላቸው። ቢን ማዝ ይህንን በመስማት ተደመመ። እናም እንዲህ አለ:- ጎሳየ ሆይ እዚህ ከመጣችሁበት አላማ ይልቅ አሁኑ ኢስላምን ብትቀበሉ ለናንተ የተሻለ ነው አላቸው። እነዚህ የመዲና ቡድኖችም የታወቁ ሙስሊሞች ሆኑ

ሚእራጅ

አሏህ (ሱ.ወ) ለነብያቶች ከሰጣቸው ተአምር በላይ የሰጣቸው ተዓምር እና ትልቁ ስጦታ ከመሬት ወደ ሰማያት ያደረጉት መለኮታዊ ጉዞ ነው።

በመጀመሪያ ከመስጅደል ሐራም (መካ) ሄዱ። በማስቀጠልም ወደ መስጅደል አቅሷ ሄዱ። እናም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የነብያቶች ሁሉ መሪ ሆኑ። አሏህ የአለም እዝነት አድርጐ የላካቸው ሲሆን ከፍተኛ ውዴታውንም አገኙ።

ወደ ሰማይ ጉዞ ባደረጉበት ወቅት ጀነትን ፣ ጀሃነምን እና በፍርዱ ቀን የሚቀመጡበትን አይተዋል። ይህ ሃሳብ ሊያረጋግጠው የማይችልና የሰው ልጅ ሊያስበው ከሚችለው በላይ የሆነ ሲሆን ከአሏህ ታአምራቶች አንዱ ነው። ሃያሉ አሏህ ወዳለበትም ገብተዋል። ይህ አሏህ የቸራቸው ታአምር ነው።

ሙስሊሞች ከኡመር (ረ.ዐ) ጋር ያደረጉት ስደት

ኡመር (ረ.ዐ) ጀግና ታዋቂ መኪይ ነበርና ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መዲና ውስጥ ቦታ ሊያዘጋጅላቸው ተሰደደ። ኡመር (ረ.ዐ) በጀግንነት እና በድፍረት መሰደዳቸው ሙስሊሞች መካን ለቀው ወደ መዲና እንዲገቡ ብርታት ሆናችው።

ጉዞውንም ከ20 ፈረሰኞች ጋር የጀመሩ ሲሆን ጉዟቸውንም የጀመሩት ሁሉም ቁረይሾች በነበሩበት በቀን ብርሃን ነው።

ይቀጥላል…..

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top