የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 2

Author picture
የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ

የነብዩ ሙሐመድ ታሪክ 2 ክፍል ሁለት

የአያታቸው ሞት

አያታቸው አብዱል ሙጦሊብ ሲሆኑ የሞቱት ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የስምንት አመት ልጅ እያሉ ነው። አያታቸው በጣም የተከበሩ የመካ መሪ እና የካዕባ ጠንካራ ጠባቂዎች ናቸው።

እሳቸውም የሞቱት በ84 አመታቸው ሲሆን አያታቸው ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም ተወዳጅና ብቸኛው የአብዱሏህና የአሚና ልጅ መልከ መልካም የሙት ልጅ ስለነበሩ በጣም ጥልቅ ፍቅር ነበራቸው።

የአቡጧሊብ ደጋፊነት

አቡጧሊብ በጣም ተወዳጅ የሆኑት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አጐት ናቸው። የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አያት ከመሞታቸው በፊት ለአቡጧሊብ ተንከባክቦ እንዲያሳድጋቸው በአደራ መልክ ሰጧቸው።

አቡጧሊብ አሁን ሃላፊነቱ ተቀብለው ተንከባክበውና ማህበራዊ አድርገው በጥልቅ ፍቅርና ውዴታ አሳደጓቸው። በዚህ ጊዜ ነበር ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የንግድን ጥበብ የተማሩት።

የነብዩ ሙሐመድ ሥራ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወጣት ሲሆኑ በቤተሰብ ስራ ላይ አዘነበሉ። ነገር ግን ምንም ገንዘብ አልነበራቸውም።

ታላቋ ሴት ኸድጃ በጣም ሃብታም ነጋዴ ስትሆን ለተወሰነ ጊዜ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የንግድ ሸቀጦችን በአደራ መልክና በተቆጣጣሪነት በአጐታቸው በኩል የተሰጡ ሲሆን ኸድጃም በታማኝነታቸው ፣ ባማረ ስብዕናቸው ፣ በኑሮ ዘዴያቸው ፣ በግብይት ስርአታቸውና ከሰው ጋር ባለቸው ቅርርብ ትደመም ነበር።

እናም እሷ እራሷ ለንግድ ሸቀጦቿን ይዘውላት እንዲሄዱ ጠየቀቻቸው። አብዛኛውን ስራዎቿን ለሳቸው ሰጠች።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከዚህ ብኋላ ታማኝና ታላቅ የንግድ ሰው ሆኑ። በንግዳቸውም ብዙ ማትረፍ ጀመሩ። ኸድጃም በታላቅነታቸው ፣ በታማኝነታቸው ፣ በግብይት ስርአታቸው መደመሟን ቀጥላለች።

ከኸድጃ ጋር ያደረጉት ጋብቻ

የኸድጃ (ረ.ዐ) አገልጋይ የነበረው መይስራህ በግብይት ወቅት ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ይሆን ነበርና ሁልጊዜም ለኸድጃ የረሱልን ታላቅ ባህሪ ፣ ለጋስነትና ጨዋነት ይተርክላት ነበር።

ይህን ድንቅ ያማረና ታላቅ ስብዕናና ቅድስና በመስማት ኸድጃ (ረ.ዐ) ረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ለጋብቻ ጠየቀች።

በጋብቻው ወቅት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የ25 አመት መልከ መልካም ወጣት የነበሩ ሲሆን ኸድጃ (ረ.ዐ) ደግሞ 40 አመቷ ነበር።

ከነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ከተጋባች ለ25 አመት ያህል ኑራለች። ይህን ተከትሎም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የጠቅላላ ስራዎቿ ተቆጣጣሪ ሆኑ። ሁሉንም ጊዜያቸውን ኃያሉ አሏህን በመገዛትም ያሳልፉ ነበር።

ነብዩ ሙሐመድ በሂራ ዋሻ ውስጥ ያደርጉት አምለኮተ አሏህ

የመካ ሙሽሪኮች እምነተ ቢሶች ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተስፋ ለማስቆረጥ ያልጣሩትና ያላደረጉት ነገር የለም።

ይሁን እንጂ በሂራ ዋሻ ጧት ማታ እዛው በመሆንና ምግብና ውሃ ይዘው በመሄድ የአምልኮት ተግባራቸውን ጀመሩ።

የሂራ ዋሻ ከመካ በስተቀኝ አቅጣጫ በኩል ከሚገኘው የኑር ተራራ ላይ ያለ ሲሆን እዚህ ዋሻ ውስጥ ነበር ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያለማቋረጥ አሏህን ይገዙና ይለምኑ የነበረው። ምግብና ውሃቸው ካለላለቀ በቀር ወደ ከተማይቱ አይመለሱም።

0%
5
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ 2

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሕይወት ታሪክ 2 ፈተና 7 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 7

Bookmark question icon

1 የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የሞቱት በረቢኡል አወል ወር ሰኞ ቀን _____ አመት ነው።

2 / 7

Bookmark question icon

2 በሒጅራ በሶስተኛው አመት ላይ የተካሄደው ጦርነት የትኛው ነው?

3 / 7

Bookmark question icon

3 በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ መሰረት የሚከተሉትን ክስተቶች ከሩቁ ወደ ቅርቡ ሰድረህ አስቀምጥ?
የአቀባ ቃልኪዳን
ይፋዊ ጥሪ
ወደ አቢሲንያ (ኢትዮጲያ) የተደረገው ስደት
ኢስራዕ እና ሚዕራጅ
ሚስጥራዊ ጥሪ (ዳዕዋ)

4 / 7

Bookmark question icon

4 የሚከተሉትን ጦርነቶች በቅደም ተከተላቸው ከሩቁ ወደ ቅርቡ ክስተት ሰድረህ (አስተካክለህ) አስቀምጥ?
የአህዛብ ጦርነት
የበኒ ነዲር ጦርነት
የኡሁድ ጦርነት
የኸይበር ጦርነት
ታላቁ የበድር ጦርነት

5 / 7

Bookmark question icon

5 የኢስራዕ እና ሚዕራጅ ክስተት የተፈፀመው

6 / 7

Bookmark question icon

6 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት በስንት አመታቸው ነው?

7 / 7

Bookmark question icon

7 ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና የተሰደደው ማን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 15%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ነብዩ ሙሐመድ

ነብዩ ሙሐመድ

ሙስሊም ሰው ከነብዩ ሙሐመድ ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ

Read More »
የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

አሏህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት እና ስብዕናዎች ከሁሉ የተለዩ አድርጓቸዋል። ይህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት ልቦች በፍቅራቸው እና በውዳሴያቸው እንዲነጉዱ ያደርጋል። በዚህ ጽሁፉ ውስጥ ከእነዚህ ባህሪያት የተወሰኑትን

Read More »

የነብዩ ሙሐመድ መልዕክት

ሃያሉ አሏህ መልዕክተኞችን ከላቀ ጥበብ ጋር የላካቸው ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ ከሁሉም በላይ አልቆ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ (ማብቂያ) አድርጓቸዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህንም ጥበቦች እና ነብዩ

Read More »

Share