መርየም (ዐ.ሰ) ከእስራኤል ልጆች መካከል ታላቅ እና አሏህን ፈሪ የነበረው የኢምራን ልጅ ናት። የኢምራን ሚስት ማርገዟን ባወቀች ጊዜ ልዩ ፀሎት አደረገች። የምትወልደውንም ልጅ ለአሏህ አገልግሎት ለማዋል ወሰነች።

እራሱን ለአሏህ የሰጠ ፣ እንደ ቀደምት ቤተሰቦቹ ተአምረኛ የሆነ ወንድ ልጅን ጠበቀች።
ነገርግን አሏህ ሴት ልጅ ሰጣት፤ መርየም ስትልም ጠራቻት። እሷን እና ዘሯን አሏህ ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲጠብቃቸው ተማፀነች።
ዘከሪያ የመርየም አጎት ነው። ተንከባክቦ ፣ ጠብቆ ያሳደጋት እሱ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሊያያት ወደ ፀሎት ክፍሏ ይሄድ ነበር።
አንድ ቀን ምግብ እየበላች አገኛት። አሁን በቅርቡ ምግብ ማን አመጣላት? ማን ሊሆን ይችላል? እያለ እራሱን እየሞገተ፤ ከየት አገኘሽው? ሲል ጠየቃት። መርየም (ዐ.ሰ) እንዲህ ስትል መለሰች፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢምራን 3፡37)
ከአሏህ ዘንድ፤ በእርግጥ አሏህ ለሻው ሰው ያለ ሂሳብ (ያለድካም) ሲሳይን ይሰጣል አለችው።

መርየም የኢሳ (የእየሱስ) እናት ናት። ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) የወለደችው ወንድ ወደ እሷ ሳይደርስ ድንግል ሆና ነው። አንድ ወቅት መርየም (ዐ.ሰ) ከፀሎት ክፍሏ ሆና እያለ መልአክ ሰው ተመስሎ ተገለጠ።
በፍርሃት ተውጣ ወደ እኔ እንዳትቀርብ አለች። መልአኩም የንፁህ ልጅ ብስራት ልሰጥሽ የመጣሁ የአሏህ መልዕክተኛ ነኝ አላት።

ሳላገባ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል አለችው። ይህ የአሏህ ውሳኔ ነው አላት። ባረገዘችም ጊዜ ወደ አንድ ገጠር ቦታ ሄደች። እዚያም ወለደች።
ጥንካሬዋና ብርታቷ በተመለሰላት ጊዜ ልጇን በእጆቿ አቅፋ ወደ ከተማው ተጓዘች። ከብዙ ወራቶች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስላይዋት ሰዎች በዙሪያዋ ተሰባሰቡ።
ያለ ባል እንዴት ልጅ ሊኖራት ይችላል ሲሉ አሰቡ። በመጥፎ ነገርም ጠረጠሯት። ልጁን እንዴት እንዳገኘሽው?
ሲሉ ጠየቋት። አንዲትን ቃል ሳትተነፍስ ወደ ልጁ ጠቆመች። ተሳለቁና በእናቱ እቅፍ ውስጥ ያለ ህፃን ልጅ እንዴት ማወራት ይችላል አሏት።
በዚህ ወሳኝ ጊዜ ኢሳ (ዐ.ሰ) ተአምራዊ በሆነ ሁኔታ እንዲህ ሲል ተናገረ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱ መርየም 19፡30-33)
በእርግጥ እኔ የአሏህ ባሪያ ነኝ። መጽሐፉን ሰጥቶኛል፤ ነብይም አድርጎኛል አለ። በየትኛውም ቦታ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል። በህይወት እስካለሁ ድረስ በእኔ ላይ ሶላትን እና ዘካን አዟል። ለእናቴ ታዛዥ እንጅ ትዕቢተኛ ፣ እብሪተኛ አላደረገኝም። በተወለድኩበት ቀን ፣ በምሞትበት ቀን እና ህያው ሆኜ በምቀሰቀስበት ቀን ሁሉ ሰላም በእኔ ላይ ነው።
አቡ-ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
”አንድም ልጅ አይወለድም ሲወለድ ሸይጧን የነካው ቢሆን እንጅ። ሆኖም በሸይጧን በመነካቱ ምክኒያት ጮሆ ማልቀስ ይጀምራል። ከመርየም እና ከልጇ ኢሳ በቀር።
አቡ-ኹረይራ (ረ.ዐ) አክለው እንዲህ አሉ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢምራን 3፡36)
ለእሷና ለዝርያዋ ከተረገመው ሸይጧን የአንተን ከለላ እሻለሁ።
ከፈለጋችሁ ይህን አያ አንብቡ ብሏል። (ቡኻሪ)
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ”ብዙ ወንዶች ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ነገርግን እንዲህ ያለ ደረጃ ላይ የደረሰች ሴት የለችም የኢምራን ልጅ መርየም እና የፊርአውን ሚስት አሲያ ሲቀሩ።”
ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) ፣ ሶላት እና ዘካ



Share