ኒፋቅ ማለት እንደማታለያ እምነትን በምላስ መመስከር እና ክህደትን በልብ ውስጥ መደበቅ ነው። የዚህ አይነቱ ኒፋቅ ኒፋቁል አክበር (ትልቁ ንፍቅና) ተብሎ ይጠራል። ይህ አይነቱ ኒፋቅ በነብዩ ጊዜ እንኳ የተለመደ ነበር።
ኒፋቅ
ኒፋቅ

ኒፋቅ ማለት እንደማታለያ እምነትን በምላስ መመስከር እና ክህደትን በልብ ውስጥ መደበቅ ነው። በእርግጥ የዚህ አይነቱ ኒፋቅ ኒፋቁል አክበር (ትልቁ ንፍቅና) ተብሎ ይጠራል።

ይህ አይነቱ ኒፋቅ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ እንኳ የተለመደ ነበር። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎችን የሚኮንን የተወሰኑ የቁርአን አንቀፆች ወርደዋል።

በመጭው አለም ህይወት የሚኖራቸውን ቦታ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡145)

በእርግጥ መናፍቃን በታችኛው ጥልቅ የጀሐነም እሳት ውስጥ ይሆናሉ።

ይህ አይነቱ ንፍቅና ከእምነት ቀኖና ወይም አቂዳ ጋር የተያያዘ ነው።

ሌላኛው የኒፋቅ አይነት ከተግባር ጋር የተያያዘ ሲሆን ኒፋቁል አስገር (ትንሹ ንፍቅና) ተብሎ ይጠራል። ይህ አይነቱ ንፍቅና ሙስሊሞች ሊርቁት ይገባል።

በዚህ ንፍቅና ውስጥ ያለ ሰው አማኝ ነው ነገርግን ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ንፍቅና የቆጠሩትን ተግባር መፈፀም ነው። ሆኖም አንድ ሰው ይህን በማድረጉ ከእስልምና ባይወጣም በመጭው አለም ህይወት ግን ቅጣት ይጠብቀዋል።

ይሁን እንጅ የጀሐነም እሳት ውስጥ ለዘላለም አይቆይም። ትንንሾቹ ንፍቅና ወደ ትልቁ ንፍወቅና ያመራሉ። ይህን ንፍቅና እንድናውቀው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተወሰኑ ግልፅ የንፍቅና ምልክቶችን እንደሚከተለው ጠቅሰውልናል።

የጀሐነም እሳት

እነዚህ ባህሪያቶች በአንድ ሰው ተግባር ላይ ከተስተዋሉ ግልፅ መናፍቅ ይሆናል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“እነዚህ አራት ባህሪያቶች ያሉት ሰው ግልፅ መናፍቅ ይሆናል። ከእነሱ መካከል አንድ ባህሪ ያለው ሰው እስካልተወው ድረስ አንድ የንፍቅና ባህሪ አለው። ሲያምኑት ይክዳል ፣ ሲናገር ይዋሻል ፣ የገባውን ቃልኪዳን ያጥፋል ፣ ሲጨቃጨቅ (ሲከራከር) ፀያፍ ቃል ይጠቀማል።ˮ

ሙናፊቅ (መናፍቅ) ማለት የንፍቅና ተግባር የሚፈፅም እና ከላይ የተጠቀሱት ባህሪያት ያሉት ሰው ነው። ሴት መናፍቅ ሙናፊቃ ተብላ ትጠራለች። የዚህ ብዙ ቁጥር አመልካች ደግሞ ሙናፊቃት ነው።

ኩፍርን ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share