ሱፍያኑ ሰውሪ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡ “የእውቀት ታላቅነት የሚታወቀው አንድን ሰው አሏህን እንዲፈራ እና እንዲታዘዝ የሚያደርገው ከሆነ ነው፡፡ ካለበለዚያ ልክ እንደማንኛውም ነገር ነው፡፡ {ኢብን ረጀብ አስተላልፈውታል}
ኢብን መስኡድ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብለዋል፡ “ትክክለኛ እውቀት የሚለየው ምን ያህል እንደሸመደድክ እና ለሰዎች እንደምትተርክ እና እንደምታስረዳ ሳይሆን እውነተኛ እውቀት የቅድስና(አሏህን የመፍራት እና የመታዘዝ) መገለጫ በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም “ባወከው እና ባጠናሃው ነገር ስራበት” ይሉም ነበር፡፡
አሏህ ሆይ እውቀትን ጨምርልን!