የንባብ ክህሎት በትምህትም ሆነ በእለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችል መሰረታዊ ክህሎት ነው። የንባብ ክህሎት እውቀት የሚጨምር ብቻ ሳይሆን እልቆቢስ የሆኑ የድል በሮችን የሚከፍት ነው።
የንባብ ክህሎት

የንባብ ክህሎት በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ ሊኖረው የሚገባ መሠረታዊ ክህሎት ነው። በተሰማራንበት ነገር ሁሉ ስኬታማ ለመሆን ፣ በእምነታችን ጠንካራ ለመሆን እና እምነታችነን ሙሉ ለማድረግ እንዲሁም ደስተኛ እና የተረጋጋ ህይወት ለመምራት እራሳችነን በእውቀትና በጥበብ ልንክን ይገባል።

የንባብ ክህሎት በትምህትም ሆነ በእለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችል መሰረታዊ ክህሎት ነው። የንባብ ክህሎት እውቀት የሚጨምር ብቻ ሳይሆን እልቆቢስ የሆኑ የድል በሮችን የሚከፍት ነው። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የንባብ ክህሎት ምንነት ፣ ጠቀሜታ እና የንባብ ክህሎት የምናሳድግበትን ስልት እንዳስሳለን።

እነዚህን እና ሌሎች ጥቅሞችን ለማግኘት የንባብ ክህሎታችን ማሳደግ ይጠበቅብናል። ወጣቶች አብዛሃኛውን ጊዜ የምናሳልፈው በትምህርት በመሆኑ በትምህርታችን ጐበዝ ለመሆን እና በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን ለመውጣት የንባብ ክህሎታችንን ከወዲሁ ልናነሻሽል ይገባል።

የንባብ ክህሎት ምንነት

የንባብ ክህሎት ማለት የተፃፈ ፅሁፍ የመረዳት ፣ ትርጉም የማግኘት እና ከፅሁፉ የተረዱትን የማብራራት ክህሎት ነው። ይህን ክህሎት በተለያየ መንገድ መክፈል ይቻላል።

1. ርቱዕነት፡ በቀላል መንገድ እና በፍጥነት ከትክክለኛ አገላለፅ ጋር የማንበብ ችሎታ ነው።

2. መገበ ቃላት፡ አንድ ሰው የሚረዳቸውን እና የሚጠቀማቸውን ቃላት ብዛት ያጠቃልላል።

3. ተረድኦ፡  የሚያነቡትን ነገር የመረዳት እና የማብራራት ችሎታ ነው።

በተለያዩ ሁኔታዎች የምንጠቀማቸው ሶስት የንባብ ዘዴዎች አሉ። እነሱም:-

  • የቅኝት/የአሰሳ ንባብ፡ ከአንድ ፅሁፍ ውስጥ የምንፈልገውን ነገር ብቻ ለይተን ለማውጣት የምንገለገለው የንባብ አይነት ነው።
  • ግርፍ ንባብ፡ የፅሁፉን ፍሬ (ዝርዝር) ነገሮች ለማግኘት የምንጠቀመው የንባብ ዘዴ ነው።
  • የዝግታ ንባብ፡ ሙሉ ፅሁፉን በጥልቅ ለመረዳት የምንጠቀመው የንባብ ዘዴ ነው።

የንባብ ክህሎት ጠቀሜታ

ጠንካራ የንባብ ክህሎት ማዳበር ለተለያዩ ምክኒያቶች ወሳኝ ነው።

  1. ለትምህርት ስኬት ጥሩ የንባብ ክህሎት በሁሉም የትምህርት ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን አስፈላጊ ነው። በደንብ ማንበብ እና መረዳት የሚችሉ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ።
  2. ማሰብ እና ማሰላሰል ንባብ ማሰብ ማሰላሰል እና የማብራራት የመተንተን ችሎታዎችን ያበረታታል። አንባቢዎች ከፅሁፉ ጋር መረጃን የማመዛዘን ፣ የመተንተን እና ሃሳብ ማፍለቅ ይማራሉ።
  3. የመረዳት ችሎታን ማሳደግ ንባብ አዕምሯዊ ሂደቶችን ያነቃቃል ፣ የማስታወስ እና የመረዳት ችሎታ ይጨምራል። ማስተዋልን እና ትኩረትን ይጨምራል።
  4. የመግባባ ክህሎት ንባብ መዝገበ ቃላትን እና የቋንቋ ክህሎት ይጨምራል። ይህ ደግሞ በፅሁፍም ሆነ በቃል በበቂ ሁኔታ ለመግባባት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የንባብ ክህሎት የማሳደጊያ ስልቶች

የንባብ ክህሎትህን ለማሻሻል ይህን ፅሁፍ የምታነብ መምህርም ፣ ወላጅ ወይም ግለሰብ ይህን አላማ ለማሳካት የሚረዱህ የተለያዩ ስልቶች አሉ።

1 ዘወትር ማንበብ

ከንባብ ክህሎት ጋር በተያየዘ ንባብን ማዘውተር ይህን ክህሎት የማሳደጊያ ቁልፍ ነው። ዘወትር ቀን በቀን የማንበብ ልምድ ይኑርህ። ዘወትር በእያንዳንዱ ቀን ለማንበብ የምታነብበትን ጊዜ አስቀምጥ።

2 ትክክለኛ የንባብ ቁሳቁሶችን ምረጥ

ከእድሜህ እና ከፍላጎትህ ጋር አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ወይም የሚጣጣሙ የንባብ ቁሳቁሶችን ምረጥ። ቀለል ያሉ መጽሐፍት ወይም ፅሁፎችን በመምረጥ ጀምርና ከዚያም በሂደት የመረዳት ችሎታህን እያየህ ውስብስብ የሆኑ መጽሐፍትን እና ፅሁፎችን በማንበብ እራስክን ፈትን።

3 መዝገበ ቃላትህን ስፋት እና ጥልቀት አሳድግ

አውዳዊ ፍችን በመጠቀም አዳዲስ ቃላት ተማር። ለየት ያሉ ቃላቶች በሚገጥሙህ ጊዜ የመዝገበ ቃላት መጽሐፍ ውስጥ በመፈለግ እና በአረፍተነገር ውስጥ እየተለማመድክ ተጠቀምባቸው። ይህን ለማድረግ ፍላሽ ካርዶች ወይም ለዚሁ አላማ የተዘጋጁ አፕልኬሽን ሊረዱህ ይችላል እና ተጠቀምባቸው።

4 የመረዳት ችሎታህን አሳድግ

አንድን ፅሁፍ ከማንበብህ በፊት ፣ ስታነብ ወይም ካነበብክ ቡኋላ ስለ ፅሁፉ ምንነት እና በርዕሱላ ያለህን እውቀት እና ግንዛቤ እራስህን ጠይቅ። ስላነበብከው ነገር ሰዎች ጋር ተወያይ ፣ ማጠቃለያ ስጥ እንዲሁም የራስክን ሃሳብ እና ምልከታ አስቀምጥ።

5 ቴክኖሎጅን መጠቀም

ኦንላይን ላይ የሚገኙ ኢቡክ መጽሐፍት እና የድምፅ መጽሐፍት ማንበብ። አሁን አሁን የወረቀት ስራ እየቀረ ሁሉም ነገር ዲጅታል እየሆነ በመምጣቱ ከዲጅታሉ አለም የምናገኘውን ጥቅም በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል። የወጣቱ ተልዕኮ መጽሐፍት የመሰሉ በርካታ ድህረገፆች ለንባብ የሚሆኑ መጽሐፍትን እና መጣጥፎችን በይነመረብ ላይ ይለቃሉ እንጠቀምባቸው።

የንባብ ክህሎታችነን የምናሻሽልባቸው መንገዶች

የቅኝት / የአሰሳ ንባብ

  • የንባብ ዘዴ
  • የአትኩሮት ንባብ
  • መዝገበ ቃላት

የቅኝት ንባብ ማለት አንድ የምንፈልገው ነገር ካለ ያን ለማግኘት ስንል አይናችነን ከፅሁፉ ላይ በማድረግ ፅሁፉን በፍጥነት ማንበብ ነው።

ይህን የንባብ ዘዴ የምንጠቀመው አትኩሮታችን አንድ የምንፈልገው ነገር ላይ ብቻ ስናደርግ ነው። ለምሳሌ አንድ አረፍተ ነገር ፣ ሀረግ ፣ ቃል ወይም ቁጥርን ቶሎ ብለን ለማግኘት ስናስብ ዝርዝር ነገሮችን ወደ ጎን በማድረግ አትኩሮታችነን በምንፈልገው ነገር ላይ በማድረግ ቶሎ ብለን ማንበብ ነው።

አንድን ፅሁፍ ምን ያህል ለኛ ጠቃሚ መሆኑን ለመገምገም ካሰብን የፅሁፉን የተወሰኑ ክፍሎቹን ብቻ እንቃኛ።

  • የመጽሐፉን መቅድምና መግቢያ
  • የምዕራፉን የመጀመሪያና የመጨረሻ አንቀፆችን
  • የመጽሐፉን መደምደሚያ/ማጠቃለያ
  • ሠንጠረዥ ፣ ግራፍ ፣ ካርታ ወ.ዘ.ተ

የግርፍ ንባብ

የግርፍ ንባብ ማለት የአንድን ፅሁፍ ዋና ነጥቦች ለማግኘት ፅሁፉን በፍጥነትና ዝርዝር ነገሮችን እየዘለሉ ማንበብ ነው። ለምሳሌ መፅሄት ፣ ጋዜጣ ፣ በራሪ ወረቀቶችን ስናነብ እንዲሁም በላይብረሪ ያለ ወይም ልንገዛው ያሰብነው መጽሐፍ ካለ ምን ያህል መጽሐፉ ለኛ ጠቃሚ መሆን ለማወቅ ስንል የምንጠቀመው የንባብ አይነት ነው።

አንድን ፅሁፍ ወይም መጽሐፍ በዝርዝር ከማንበባችን በፊት አስቀድመን የሚከተሉትን ነገር እንመልከት:-

  • ርዕሱን
  • መቅድም
  • መግቢያ
  • ማጠቃለያ
  • ሃይለቃሉን
  • የተዘረዘሩ ነገሮችን
  • ታላቅ ስራ የሰሩ ሰዎችን ማንነት

የዝግታ ንባብ

የዝግታ ንባብ ማለት መጽሐፍት ወይም የጽሁፍ መልዕክት በጥልቅ ለመረዳት ቀስና ረጋ ብሎ እያንዳንዷን ቃል ፣ ሀረግ ፣ አረፍተነገርና አንቀፆችን ቀስና ረጋ ብሎ በደምብ ምበብ ነው።

የአትኩሮት ንባብ

አብዛሃኛዎቻችን በትምህርት ቤት የተሰጡን መጽሐፍት አንብበናል ግን ከመጽሐፎቹ በቂና ተፈላጊውን እውቀት ይዘን የወጣነው ጥቂቶች ነን። ለዚህም ትልቁ ምክኒያት ለምናነበው ነገር ትኩረት አለመስጠታችን ነው።

  • እያሰመሩ ወይም ጠቃሚ ነጥቦችን በማስታዎሻ ደብተር ላይ እያወጡ ማንበብ
  • እማናውቃቸውን ቃለት ለቅመን በማውጣት መሸምደድ
  • በአትኩሮት ከማንበባችን በፊት የጽሁፉን ርዕስ ተመልክተን ምን ያህል ስለ ርዕሱ እንደምናውቅ ለመገምገም እራሳችነን የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንጠይቅ። ለምሳሌ የአበባ አይነቶች የሚል ርዕስ ቢኖር ስንት የአበባ አይነቶች አሉ? እነማናቸው? የትና እንዴት ይበቅላሉ? ብለን እራሳችነን እንጠይቅ።

መዝገበ ቃላት

መጽሐፍት ስናነብ ፣ የተለያዩ የመረጃ አውታሮችን ስንከታተል አዲስ ቃላት ከዚህ በፊት የማናውቃቸው ቃላት ሊገጥሙን እንደሚችል እሙን ነው።

ታዲያ ይህ ችግር ለመቅረፍ ማለትም የምናነበውንና የምናዳምጠውን ነገር በትክክልና ሙሉ በሙሉ ለመረዳት አዲስ ቃላቶችን ማወቅ ይጠበቅብናል።

ለዚህም መፍትሄው የመዝገበ ቃላት መጽሐፍ ከጐናችን እንዳይለየን ማድረግና ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን ቃላት በማስታወሻ መዝግበን በመያዝ መሸምደድ ይጠበቅብናል።

በንባብ ጊዜ የሚገጥሙን ፈተናዎች

ከንባብ ጥቅም ባሻገር ብዙ ሰዎች መሻሻላቸውን የሚያደናቅፍ ፈተና ይገጥማቸዋል። የተለመዱት መሰናክሎች የሚከተሉት ናቸው።

1 ጊዜ አለመኖር

በዚህ በተጨናነቀ ህይወት ውስጥ ለንባብ ጊዜ መፈለግ በራሱ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ይህን ችግር ለመቅረፍ ንባብን ከዕለት ተዕለት ልማዶች ውስጥ አንዱ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ከመተኛት በፊት ወይም ከእንቅልፍ በነቃህ ጊዜ ወይም ደግሞ ባለህ ትርፍ ጊዜ ሊሆን ይችላል።

2 ጊዜ ማሳለፊያ

የዲጅታል ጊዜ ማሳለፊያ በሞላበት አለም ውስጥ ንባብ ላይ ትኩረት ማድረግ ሊከብድ ይችላል። ይሁን እንጅ ለሁሉም ነገር ልክና ሚዛን አበጅተን ለንባባ የተወሰነች ጊዜ ብንሰጥ ጥሩ ነው።

3 አካል ጉዳተኞች

አካል ጉዳተኞች ልዩ የሆኑ ስትራቴጂ እና መሳሪያዎችን በመተቀም የንባብ ክህሎታቸውን ሊያሳድጉ ይችላሉ። ለምሳሌ በድምፅ የተቀረፁ መጽሐፍት ፣ ስልክ ላይ ከፅሁፍ ወደ ድምፅ በመቀየር ፣ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ወ.ዘ.ተ ናቸው።

መደምደሚያ

የንባብ ክህሎት እስከ ህይወት ፍፃሜ ለሚዘልቅ ስኬት የሚያገለግል ጠቃሚ ክህሎት ነው። የትምህርት ስኬት ጨምሮ ፣ አስተውሎትን ፣ የእውቀት አድማስ የማስፋት ጥቅችን ይሰጣል። ጥሩ የንባብ ስልቶችን እና ምቹ  የንባብ ከባቢን በመፍጠር የንባብ ክህሎት ማዳበር ይቻላል።

ለበለጠ ንባብ በአካባቢያችሁ ያሉ ቤተ-መጽሐፍት ይጎብኙ። ኦንላይን የመጽሐፍት ጦማሮችን ያስሱ።

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share