የሰው ልጅ ስሜቱን ከላዩ ሲያነግስ፤
ለአሄራ መስራቱን ትቶ ለጀሃነም ሲደግስ፤
ሃራምን በመስራት ምድርን ሲያድበሰብስ፤
ያሻውን ሲጠጣ ያሻውን ሲበላ፤
ያማረውን ሲወድ ሲፈልግ ሲጠላ፤
ሃራምን በመሥራት መልካምን ሲያጥላላ፤
እንዲህ ከሆነ ኑሮው ማነለ ከሱ በላይ ተላላ፤
እሱ ዘመናዊ ሆኖ የሸይጧን ተከታይ፤
ሰዎችን ለማጥመድ ይላል ከላይ ከታይ፤
ማየቱን ሳይገድብ እስኪበቃው አይቶ፤
የስሜት መረቡን እስከ ጫፍ ዘርግቶ፤
ሰው ላየው ለሰማው ሁሉ ከማለለ፤
እራሱን የአሏህ ባሪያ ማድረግ ካልቻለ፤
በቃ ስሜት ብቻ እንጂ ኢባዳ የት አለ?
ከራሱ ጋር ተጣልቶ እንደዋለለ የሚኖር ሰው ጉዞው አልጣመኝም፤
መሳቅ ወይስ ማልቀስ ህይወቱ አልገባኝም፤