ጊዜና ልጅነት

Author picture

Table of Contents

ቀን ቀንን ሲተካ ሲከንፍ እንደዋዛ፤
ሲመለሱ አይኖርም ያረገፉት ጤዛ፤

እንዲህ ነው ልጅነት በቀን የሚጨልም፤
ካለፈ በኋላ የማይኖሩት አለም፤

የማለዳ ፀሐይ አምሮባት የዋለች፤
ሰአቷን ጠብቃ ማታ ትጠልቃለች፤

ጊዜው እየሮጠ እድሜ እየከነፈ፤
ከቀን ጋር ተዋግቶ የለም ያሸነፈ፤

ልጅነት በጊዜ ጦር እየተመታ፤
የማለዳ ውበት አይገኝም ማታ፤

የሰው ልጅ ሁልጊዜ ልጅነት ቢመኝም፤
ልጅ እንጅ ልጅነት ዳግም አይገኝም፤

ምንጭ_______በአራጋው ሙሐመድ

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top