እውነትም ያልገባው

Author picture

ፍጥረታት በሙሉ ከጥንት ጀምሮ፤
መላዕክቶች ሳይቀሩ ኢብሊስን ጨምሮ፤

የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአዳም ጀምሮ፤
እንዲኖር ነበር ትዕዛዙን አክብሮ፤
የአሏህን ሃያልነት ባንድነት መስክሮ፤

አሏህ አልፈጠረም አንዳች ነገር፤
እንዲኖር እንጂ በሱ ትዕዛዝ ስር፤

ከፍጥረታት በሙሉ፤
ከአድማስ እስከ አድማስ ያሉ፤
እፅዋት አራዊቶች ዛፍና ቅጠሉ፤

አላማ አላቸው የመፈጠራቸው፤
የአሏህን አንድነት መስካሪዎች ናቸው፤

የተፈጠረበትን አላማ ዘንግቶ፤
የአሏህን ራህመት ቀና መንገድ ትቶ፤

ነፍሱን ተከተለ እሮጠ ነጎደ፤
በጥፋት ጎዳና ራሱን አዋረደ፤

እሩጦ መጨረሻውን ሲያጣ፤
የአሏህን ትዕዛዝ በቅጡ ሳይወጣ፤

ጭንቀት ሲፈጥርበት የምድር አለሙ፤
አልገባኝም ይላል የኑሮ ትርጉሙ፤
እራሱን ያጠፋል እስከ ዘላለሙ፤

እውነትም ያልገባው የዚች አለም ኑሮ፤
ሁልጊዜ ይኖራል በጭንቀቱ ታስሮ፤

Related posts

ሂጃብ ወይስ ፋሽን

ሂጃብ ወይስ ፋሽን

ሂጃቧን ጠቅልላሙሰስሊም ነሽ ተብላበስም ተሸንግላ ኡፍፍ እንዴት ይሞቃልሂጃብ ያስወልቃልውስጥን ያስጨንቃል ኡሽ ምን አለ ቢቀርፀሃዩ ሲከርፊትን ሲያጠቁርወደዚያ ነው መወርወር የምን መጨናነቅወንዶች መጡ መሰቅቅበዝግታ መሣቅእራስን መደበቅ ኧረገኝ

Read More »
ድፈርና ኢማናችን ይሙላ

ድፈርና ኢማናችን ይሙላ

የናትህን ማህፀን ያኔ ባልጋራህ፤ በኖርክበት ቀዬ ባልኖር ካንተ ጋራ፤ እንደ ዕድል ሆኖ ባይወልደኝ አባትህ፤ ድክ ድክ ብዬ ባላድግ ከቤትህ፤ ምንም ባልፈጠር ከመሃከላችሁ፤ በዘርም በቋንቋ ባልገናኛችሁ፤

Read More »

አማር እና አሞራዎቹ

ፈገግታው ጨረቃ ጅስሙ የሚያሳሳ፤
ድክ ድክ የሚል እንደጨቅላ እንቦሳ፤
በአማር ቁንጅና በልጃቸው ሀሴት፤
ኡሙን ሲያስለቅሳት ልቧን ፍቅር ሞልቶት፤
አቢው ይቦርቃል የልጅ

Read More »
ከሙዕሚን ባህሪ

ከሙዕሚን ባህሪ

ታላቁን አክባሪ
ለታናሹ ራሪ

ፈርዱን ቸል ያላለ
ከሱናውም ያለ

ንግግሩ ተግባር
ህይወቱ ቁምነገር

Read More »

Share