የእውቀት ታላቅነት

Author picture
የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም አደም አለይሂ ሰላም ወደዚች አለም ሲመጣ ከአሏህ ዘንድ የነገራቶችን ስምና እውቀት አሏህ ችሮት ነው። ከዚህም አልፎ ለነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻው ወህይ (ቁርአን) ሲገለፅላቸው የመጀመሪያው ቃል «ኢቅራ» አንብብ የሚል ነበር። ይህ ምን ያህል እውቀት
የእውቀት ታላቅነት

የእውቀት ታላቅነት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው። የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ማለትም አደም አለይሂ ሰላም ወደዚች አለም ሲመጣ ከአሏህ ዘንድ የነገራቶችን ስምና እውቀት አሏህ ችሮት ነው።

እንዲሁም ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻው ወህይ (ቁርአን) ሲገለፅላቸው የመጀመሪያው ቃል «ኢቅራ» አንብብ የሚል ነበር። ይህ ምን ያህል እውቀት በኢስላም ቦታ ያለው መሆኑን የሚያመላክት ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ፈትህ 58:11)

“አሏህ ከእናንተ መካከል እነዚያ ያመኑትንና እውቀት የተቸሩትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል።”

እንዲሁም በቡኋሪ በተዘገበው ሐዲስ መሠረት

እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

ቡኻሪ

ኢማሙ ሙሐመድ አልገዛሊ እንዳሉት እውቀት የእያንዳንዱ ተግባር ፣ የስራ ወይም የእምነት መሰረት ነው። ካለ እውቀት መልካምነትና ደግነት በዚህም ሆነ በመጭው አለም ሊገኝ አይችልም።

ስለዚህ እንደተባለው ከእውቀት በላይ ወደ አሏህ የሚያደርስ (የሚያመራ) መንገድ የለም በእውቀት ቢሆን እንጂ። የሰው ልጅ ጌታውን በብቸኝነት እንዳይገዛ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ የሰው ልጅ ልብ በድንቁርና ፅልመት መሸፈኑ ነው።

እውቀት የህይወት መሠረት ነው። በእውነቱ እውቀት በራሱ ህይወት ነው። እንዲሁም ድንቁርና የሞት መሠረት ሲሆን ድንቁርና በራሱ ደግሞ ሞት ነው።

ከእውቀት ባሻገር ከሁሉም ነገር በላይ ከአሏህ ዘንድ የተወደደ ነገር ቢኖር ኖሮ ለአደም (ዐ.ሰ) ይሰጠው ነበር። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢምራን 3:18)

“አሏህ በማስተካከል የቆመ አስተናባሪ ሲሆን ከእሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ መሆኑን መሠከረ። መላዕክቶችና የእውቀት ባለቤቶችም እንዲሁ መሠከሩ። ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። አሏህ አሸናፊና ጥበበኛ ነው።”

ከዚህ መገንዘብ እንደሚቻለው አሏህ (ሱ.ወ.ተ) ራሱን በመጥቀስ ይጀምርና በሁለተኛ ደረጃ መላዕክቶችን ያወሳል። ከዚያም በሶስተኛ ደረጃ የእውቀት ባለቤቶች ሲል ይጠቅሳል።  

በሌላ አያ ደግሞ አሏህ የራሱን እና የኡለማዎች ምስክርነት በቂ እንደሆነ ያመላክታል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ረዕድ 13:43)

“በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአሏህና እርሱ ዘንድ የመፅሐፉ እውቀት ባላቸው በቃ በላቸው።”

በሌላ የቁርአን አያህ አሏህ እንዲህ ይላል:- «በእርግጥ አሏህን ፈሪ አገልጋዮች ሊቃውንቶች ናቸው።»

ለዚህ ምክኒያቱ ግልፅ ነው። በእርግጥ አንድ ሰው ካለ እውቀት የአሏህ ፍራቻ ሊኖረው አይችልም። እንዲሁም የአሏህን ቁጣ ፣ የጀሃነምን ቅጣት ፣ የቂያማን መከራ ካለ እውቀት ሊረዳ የሚችል የለምና ነው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) “አሏህ ከሁሉ በላይ ቸር ነው። እኔ ከእናንተ መካከል በጣም ለጋስ ነኝ እናም ከእኔ ብኋላ ከእናንተ መካከል በጣም ለጋስ የሆነው እውቀትን የሚሽትና የሚያስፋፋ ነው” ብለዋል።

ኢማሙ ዘሃቢይ እንደዘገበው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

“በፍርዱ ቀን የኡለማዎች (የሊቃውንት) የቀለም ማሰሮ እና የሰማእታት ደም ወደ ፊት ይመጣል። የኡለማዎች ቀለም ከሰማእታት ደም በላይ ይሆናል” ብለዋል።

በሐዲስ ሸሪፍ እንደተዘገበው አንድ ሰው እውቀትን በመሻት ላይ እያለ የሞተ አሏህን በዚያው ሁኔታ ላይ ይገናኛል።

በሙአሊመቱ ተንዚል እንደተዘገበው ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

«አንድ ሰው እውቀትን ለመሻት ሲጓዝ መላኢካዎች ክንፎቻቸውን ከእግሩ ስር ያደርጉለታል ፤ ሰማያትና ምድር እንዲሁም የውቅያኖስ አሳዎች ዱአ ያደርጉለታል።» ብለዋል።

የእውቀትን ታላቅነት ለመረዳት እውቀት ከአሏህ ባህሪያት መካከል አንዱ መሆኑን መገንዘብ በራሱ በቂ ነው። በዚህም ሆነ በመጭው አለም የህይወታችን መድህን የብልፅግናችን መሠረቱ እውቀት ነው።

እውነታውን ስንመለከት እውቀት የሌለው ሰው እንሰሳ ነው። የሰው ልጅ ልዩና ታላቅ የሚያደርገው ነገር እውቀቱና ንግግሩ ነው። ይህ ለኛ ጠቃሚ ከሆነ የእውቀትን ሃብት ለማግኘት ሁሌም መጣር ይጠበቅብናል።

እውቀትን በመፈለግ ላይ ሊገጥሙን የሚችሉ መሠናክሎች

እውቀትን በመሻት መንገድ ላይ ሆነን የሚገጥሙን መሰናክሎች የሚከተሉት ናቸው፦

የሸይጧን ፈተና

ከተረገመው ሸይጧን ዘንድ በጣም የተጠላና በጣም አደገኛ ነገር ቢኖር እውቀትን መሻት ነው። ይህን ጣልቃ ገብነት ፣ መሰናክል ለመዋጋት በጣም ቀላሉ ዘዴ የቁርአን አያቶችን እና ሐዲሶችን ማስታዎስ ሲሆን እንዲሁም ለሸይጧንም ጉትጎታና ማዘናጊያ ትኩረት አለመስጠት ነው።

ነፍስያ

መከራን ስትጠላ መዝናናትን እና መንፈስን ማርካታ ትወዳለች። በእርግጥ አንድ ሰው የዱንያን ጊዜያዊነትና የአሂራን ዘላለማዊ መኖሪያነት ሲረዳ እውቀትን የመሻት መከራ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ይሆንና ደስታውና ጥቅሞቹ እልቆቢስ ይሆኑለታል።

  • የጓደኛ ተፅእኖ
  • አለማዊ ጥቅምን መፈለግ
  • የሃብት ስስት

የዚህ ብልጭልጭ አለም ሃብት ጠፊና ከእውቀት ጋር ሊነፃፀር የማይችል ነው። አንድ ሰው ሲሞት ሃብቱ አይከተለውም ይልቁንስ ወደ መቃብሩ የሚከተለውና ጀነት እስኪገባ ድረስ የሚረዳው ነገር ቢኖር እውቀት ነው።

  • ቅን የሆነ አስተማሪ ማጣት
  • የእለት ተእለት ኑሯችንን ማሰብ

ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ከገባንበት የድንቁርና አሮንቃ እንውጣ። በዚች ጊዜያዊ መኖሪያ አብዛሃኛዎን ጊዜያችነን ለምን በማይረባ ፍሬ ቢስ በሆነ ነገር እናባክነዋለን።

ስለዲናችን እውቀትን የምንሻበት ሰአት ይኑረን! በዚህም ሆነ በመጭው አለም እውቀት ጠቃሚ ነው። ከእፍረትና ከውርደት እንድናለን።

ይህን ትልቅ ሃብት ለመከሰብ ጊዜያችንንና ገንዘባችነን በእውቀት ላይ ኢንቨስት እናድርግ። አዲስ ነገርን ለማውቅ ከፍተኛ ጉጉት ይኑረን።

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share