የሙስሊሙ ኡማ አንድነት እና የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፊትና

ዛሬ ዛሬ ፈትዋ የሚሰጠው በዝቷል። ወንድ ፣ ሴት ፣ ወጣት ፣ አዛውንት ሳሩ ቅጠሉ ሁሉም ፈትዋ ሰጭ ሆኗል። ለ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኡማ ትልቁ ፈተና ፈትዋ ለመስጠት መቻኮል ነው።

ይህን ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር አራቱ የመዝሐብ ባለቤቶች የኔ ፈትዋ ከቁርአን እና ከሱና ጋር ካልገጠም ተውት ሲሉ ዛሬ ላይ ግን የኔ ፈትዋ ትክክል ነው ብለው የሚሞግቱ አይጠፉም።

የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱ አሊም ነኘ ዱአት ነኝ ያሉ በኡማው ክፍፍል ላይ ጧት ማታ ይሠራሉ። የዲን ላይ ነጋዴዎች በኡማው መካከል መበታተንን እና መከፋፈልን ፈጥረዋል።

ከዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ): “የኔ ኡመት በ73 ቡድን ይከፋፈላል ከነዚህም መካከል አንዷ ብቻ ናት የጀነት”ብለው የለ የሚል ነው።

አዎ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ብለዋል እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ነገር ቢኖር ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ይከፋፈላሉ እንጂ ተከፋፈሉ የሚል አንድም ቦታ ላይ በሐዲሳቸው የለም። እንዲሁም ሙስሊሞች ተከፋፈሉ የሚል አንድም የቁርአን አያ የለም።

ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ ፈትዋ ለመስጠት አንቻኮል፤ እራሳችነንም ለክፍፍል ምቹ አናድርግ (ምቹ ሁኔታ አንፍጠር)፤ ሂወታችንን በቁርአን እና በሐዲስ ብቻ እንምራ! ማንም ሰው ሶፊያ ፣ ወሐቢያ ፣ ሰለፊይ ፣ ኸዋሪጅ ከነዚህ መካከል የትኛው ነህ? ብሎ ቢጠይቅህ መልስህ “እኔ ሙስሊም ነኝ” ብቻ ይሁን!!!

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top