የኮሮና ወረርሽኝ የማንቂያ ጥሪ!

ስለዚህ ነገር የምናስበው ምንድን ነው? ቀርአን ምንይላል? ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ምን ብለዋል? አስታውሱ! ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ ልክ እንደ ኮሮና ያለ በሽታ በተከሰተ ጊዜ ማለት ነው እንደ ሙስሊም ምን ማድረግ እንዳለብን መክረውናል፡ “ወረርሽኑ በተከሰተበት ከተማ ፣ መንደር ፣ ቦታ ያለ ሰው አካባቢውን ለቆ አይውጣ፡፡ ወደ ተከሰተበት ቦታም አትሂዱ ብለዋል፡፡” እንደ ሙስሊምነታችን ልናደርግ የሚገባው የመጀመሪያው ነገር ይህ ነው፡፡

ልክ እንደ ኮሮና ቫይረስ ያለ ወረርሽኝ በአለም ላይ እንዲከሰት የሚያደርገው አሏህ ነው፡፡ አንድም የአሏህ ቅጣት ፣ አንድም የአሏህ እዝነት ነው፡፡ የሰው ልጅ የቆሸሸች ነፍሱን የሚያጠራበት ነው፡፡ አሏሁ አክበር! አሏህን ለሚታዘዙ ሰዎች የኢማናቸው መፈተኛ እና ነፍሳቸውን የሚያጠሩበት በረካ ነው፡፡ አሏህን ለማይታዘዙ ፣ በትእዛዛቱ ላይ አመፀኞች ለሆኑ ደግሞ መቀጣጫ ነው፡፡ የማንቂያ ጥሪ ታውቃላችሁ አይደል፡፡ ሰው ከተኛበት የምትቀሰቅስ! በተዘዋዋሪ ይህ የአሏህ እዝነት ነው፡፡ አሂራን ማስታወሻ ነው፡፡

አሁን ቆም ብለን የምናስብበት ፣ የምናሰላስልበት ፣ እራሳችነን የምናደምጥበት እና የምንጠይቅበት ጊዜ ነው፡፡ ሰዎችን ስንሰርቅ ፣ ስናታልል ፣ ስናማ ፣ አሏህን ስናምፅ ፣ ብዙ ሐራም ነገሮችን ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ለአሏህ ታዛዥ የሆነ ሰው የኢማኑ መፈተኛ ነው፡፡ አሏህን እያመፅን የኖርን ግን መቀጫችን ሊሆን ይችላል፡፡

ይሁን እንጅ አሁንም በተውበት ወደ አሏህ ለመመለስ እድሉ አለን፡፡ ይህ የማስጠንቀቂያ ጥሪ ነውና ወደ አሏህ በተውበት መመለስ እና በጎ ስራ መስራት አለብን፡፡

እንደምናውቀው ቻይና በግልፅ እስልምናን ማስተማር እና መተግበር ከማይቻልባቸው ሐገሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡ ባንዳንድ ቦታዎች ቁርአንን አቃጥለዋል ፣ መስጅዶችን አፍርሰዋል ፣ መስሊሞችን አሰቃይተዋል ፣ የኮሚኒስት ፓርቲ በሚፈልገው መልኩ ቁርአንን ለመከለስ እቅድ ነበረው፡፡ በእነሱ ላይ ምን ሆነ? አለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ምንድነው? አሜሪካ እንኳ ስኬቷን አድንቃለች፡፡ ምጣኔ ሃብታቸው በጣም አድጓል፡፡ ነገርግን አሏህ ሲሻ በስንት አመት ልፋት ያካበተችውን በሰከንድ ውስጥ እንድታጣው ያደርጋል፡፡ ውድ እህት ወንድሞቼ እኛ ከእዚህ ምን እንማራለን!

ዝምብሎ መቀመጥና ፎክስ ኒውስ ፣ ቢቢሲ ፣ ሲኤኔን ፣ ኢቢሲ ፣ ፋና ዜና ማድመጥ አይደለም፡፡ ከዚህ የአሏህ የማስጠንቀቂያ ጥሪ መማር አለብን፡፡ ሁሉንም ወደ እራሳችን ህይወት መልሰን እራሳችነን እንፈትሽ፡፡ ምን እውቀት ፣ ገንዘብ ፣ ሃብት ፣ ጉልበት ፣ ጤና ቢኖረን አሏህ ሁሉንም በሰከንድ ውስጥ እንዳልነበር ያደርገዋል፡፡ ሁላችነም የእሱ ነን፡፡

አሁን ላይ ኮሮና በብዙ ሐገራት እየተስፋፋና እየተሰራጨ ነው፡፡ አሏህ ይህ እንዲሆን ከሻ አለም ላይ የትኛውም አካል ወይም ሃይል መመከት አይችልም፡፡ አሜሪካና ቻይና እንኳ እራሳቸውን መከላከል አልቻሉም፡፡

ውድ እህት ወንድሞቼ ስለቻይና ተውትና በቤታችን ፣ በንግዳችን ፣ በስራ ቦታችን ፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ትንሻን ቻይና የሆን ሰዎች ከዚህ ማስጠንቀቂያ መማርና ወደ አሏህ መመለስ አለብን፡፡

መልዕክቱን ከወደዱት ቢያንስ ለሶስት ሰው ሼር አድርጉት| Share

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top