በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

  • የዱአ ትርጉም
  • የዱአ አይነቶች
  • የዱአ ታላቅነትና ጥቅሞች
  • የዱአ ቅድመ ሁኔታዎች
  • የዱአ ስነ-ምግባር
  • ዱአ ተቀባይነትን ሊያገኝባቸው የሚችሉ አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች

የዱአ ትርጉም

ዱአ አሏህን ለዚህም ሆነ ለመጭው አለም እርዳታን የምንጠይቅበት ታላቅ መንፈሳዊ ኢባዳ ነው። በቃንቇ ደረጃ ዱአ ማለት የእርዳታ ጥሪ ማድረግ ወይም መለመን ፣ መጠየቅ ፣ እርዳታን መሻት ማለት ነው። በሸሪአ ፍች መሠረት ደግሞ ዱአ ማለት አሏህ(ሱ.ወ.ተ) የሆነ ነገር እንዲሰጠን እንዲያጐናፅፈን እና ከመቅሰፍት ፣ ከመከራከና ከችግር እንዲጠብቀን አሏህን መለመን ነው።

ዱአ ማድረግ በራሱ አሏህን መገዛት ነው። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ብሏል፦ ለኔ ዱአ አድርጉ ምላሽ እሰጣችኋለሁና፤ እነዚያ እኔን ለመገዛት እብሪተኛ የሆኑ የተዋረዱ ሆነው ወደጀሃነም እሳት ይገባሉ።

ዱአ የአንድን ሰው የኢማን ደረጃና ከሱ ጋር ተያያዥ የሆነውን የተውሂድ ማለት በተውሂድ ላይ ያለውን ዝንባሌና ጥንካሬ የሚያመላክት ነው። ከአሏህ ውጭ ያለን ነገር መለመን ሰውም ይሁን እንስሳ ፣ ጣኦትም ይሁን መልእክተኛ ወ.ዘ.ተ መለመን ትልቅ ሽርክ ነው።

የዱአ አይነቶች

ሁለት የዱአ አይነቶች አሉ እነሱም:-

  1. ዱአኡል መሳላህ
  2. ዱአኡል ኢባዳ

ዱአኡል መሰላህ ብሎ ማለት አሏህን የመለመን ዱአ ነው። ለምሳሌ

  • አሏህ ሆይ ማረኝ
  • አሏህ ሆይ መልካም ስራን ስጠኝ
  • አሏህ ሆይ ልጅ ስጠኝ
  • አሏህ ሆይ ባሪያህ አድርገኝ ወ.ዘ.ተ

ሁለተኛው የዱአ አአይነት ዱአኡል ኢባዳ ሲሆን ይህ የዱአ አይነት እያንዳንዱን የአምልኮተ አሏህ ተግባሮችን ያጠቃልላል። ለምሳሌ፦

  • ሶላት
  • ዚክር
  • ቲላወቲል ቁርአን ወ.ዘ.ተ

ትክክለኛና ሙሉ የሆነ ዱአ ማለት ሁለቱን የዱአ አይነቶችን ባንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ ነው። አሏህን በብቸኝነት እየተገገዛን አሏህን ብቻ እንለምናለን!!!

የዱአ ታላቅነትና ጠቀሜታዎቹ

ዱአ ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ዘንድ በጣም ታላቅ ተግባር ነው። ምክኒያቱም ባሪያው እንደባሪያ ይሆናል፤ ቸግሮሃል አሏህን ትለምናለህ(ለማኝነትህን ታረጋግጣለህ) እንዲሁም አሏህን ታልቃለህና ነው።

  • አሏህ እሱን እንድንለምን አዞናል
  • ዱአ ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር ያጠነክራል
  • የአሏህን ውዴታ ያስገኛል
  • ከመጥፎ ነገሮች መጠበቂ ይሆናል
  • ከጀሃነም እሳት ይጠብቃል
  • ቀድርን (ቀዷ ወል ቀድርን) ይቀይራል
  • ስኬትን ያጐናፅፋል
  • ችግሮችን ያቀላል
  • ለጭቁኖች መሳሪያ ነው
  • ማሃርታን ያስገኛል
  • ኢማን ያበረታል
የዱአ ቅድመ ሁኔታዎች
  • ለዱአችን ምላሽ ሰጭው አሏህ ብቻ መሆኑን ማመን
  • ኢህላስ(ቅንነት) ያለው መሆን
  • ቀጣይነትና ሶብር ያለው መሆን
  • ለምላሹ ችኩል አለመሆን
  • ሃላል የሆነን ነገር መለመን
  • ለምንጠይቀው ነገር ሃላል የሆነ ኒያ ማድረግ
  • ምግባችን ልብሳችን ገቢያችን ወ.ዘ.ተ በሃላላ የተገኙ መሆን
  • ኢኽላስ ያላትና ሶብር የምታደርግ ልብ ያለው መሆን የዱአ ስነ-ምግባርBዱአ ስናደርግ ምን ማድረግ አለብን?
  • ምንም ነገር ከመለመናችን በፊት አሏህን ማመስገን/አሏህን ማወደስ
  • የአሏህን ስሞችና ባህሪያት መጠቀም ለምሳሌ:- ምህረትን ስንጠይቅ ያረህማን በማለት መጀመር ገንዘብን ስንጠይቅ ያረዛቅ በማለት መጀመር
  • በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ
  • ሁለቱንም መዳፎች መዘርጋት
  • ዱአ ሲያደርጉ ወደ ቂብላ መዞር
  • ዱአ ከማድረግ በፊት ውዱእ ማድረግ ወይም በውዱእ ላይ መሆን
  • ዱአ ያደረጉ ማልቀስ

– አሏህ ለዱአችን ምላሽ እንደሚሰጠን እርግጠኛ መሆንና ከአላህ ተስፋ ማድረግ
– አሏህን ብቻ መለመን
– ዱአውን በሚስጥር(ድምፅን) ሳያሰሙ ማድረግ
– ከሃጢያት መፀፀት
– ቆራጥ መሆን ለምሳሌ:- አሏህ ሆይ አንተ ካሻህ ማረኝ ማለት ሳይሆን አሏህ ሆይ አንተ ሁሉን ማሃሪነህና ማረኝ ማለት ይኖርብናል።
– ለሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ዱአ ማድረግ
– ሲጨርሱ አሚን በማለት መጨረስ
– አዘውትሮ ዱአ ማድረግ

በዱአ ውስጥ የተጠሉ ወይም የተከለከሉ ነገሮች

  • ግጥም
  • ሃራም የሆነን ነገር መለመን
  • አሏህ አስቀድሞ የደነገገውን ነገር መለመን
  • ምድራዊ የሆኑ ነገሮችን ብቻ መለመን
  • የአሏህን ስሞችና ባህሪያት ያላግባብ መጠቀም
  • መጥፎ የሆነን ነገር ለራሳችነም ይሁን ለሌሎች መለመን
  • ዱአ ያደረጉ መራገም
  • ሞትን መለመን
  • ይህን ስጠኝ እንጂ ሌላ አልጠይቅህም ማለት
  • ጩኸው ዱአ ማድረግ

ከሌሎች ጊዚያ የበለጠ ዱአችን ተቀባይ የሚሆኑባቸው ግዜያቶች

  • እኩለለሊት
  • አዛን ሲደረግ
  • በአዛንና በኢቃም መካከል ባለችው ጊዜ
  • በሶላት ወቅት
  • በሱጁድ ወቅት
  • በጁም አቀን
  • በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር
  • ውዱእ ካደረጉ ቡኋላ
  • የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት
  • በሐጅ ወቅት በተለይ በአረፋ ቀን
  • ዝናብ ሲጥል ዱአ ተቀባይነትን ሊያገኝባቸው የሚችሉ አጋጣሚዎችና ሁኔታዎች
  • በችግር ውስጥ የሆነ ሰው
  • መንገደኛ
  • የቤተሰብ ዱአ
  • የሚፆም ሰው
  • ቁርአን ከቀሩ ቡኋላ
  • ዚክር ከማድረግና ቁርአን ከመቅራት የማይቦዝን ሰው
  • ሙስሊም ወንድሞቹና እህቶቹ በሌሉበት ለኑሱ የሚደረግ ዱአ
Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top