ጥሩ ጓደኛ ለመምረጥ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

✍ በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

 

 

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ጓደኛህ ማን እንደሆነ ከነገርከኝ ማንነትህን እነግርሃለሁ!!!

  • መከራ ፣ ችግር አጋጥሞህ ጭንቀትህን ልታካፍለው አስበህ የነበረ ሰው የለም?
  • በጣም የሚወድህ ፣ ስትጨነቅ የሚጨነቅ ፣ ደስታህን ደስታው ያደረገ ጥብቅ ጓደኛስ ኖሮህ ያውቃል?
  • ተስፋ የሚያስቆርጥ ፣ እንድትጨነቅና እንድትተክዝ የሚያደርግህ ጓደኛስ አጋጥሞህ ያውቃል?

እኛ የሰው ልጆች ማህበራዊ ፍጡሮች እንደመሆናችን ጓደኞች እንዲኖሩን እንፈልጋለን። አብዛሃኛዎቻኛው የሂወታችን ክፍል ከሰዎች ጋር በመቀላቀል ወይም ማህበራዊ ትስስር ከመፍጠር ጋር የተያያዘ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደሚታወቀው ማህበራዊ ኑሮ በራሱ የጤናማ አኗኗር እና የችግር መፍትሄ ዋነኛ መሳሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሂወት ውጣ ውረድ የበዛበት የችግር ፣ የተስፋቢስነትና የውድቀት መንስኤም ነው።

ታዲያ ይህ ማህበረሰብ አባት ፣ እናት ፣ ልጅ ፣ እህት ፣ ወንድም ፣ አክስት ፣ አጐት ፣ ጓደኛ ፣ ጐረቤት እያለ የሚፈጠር ማህበራዊ ትስስር ሲሆን ይህ ትስስር ከጊዜ አንፃር እና እንደ የሰው ባህሪ እየተወሳሰበ ሂወት በፈተና የተሞላች ሆና መጥፎ ነገሮችን እንድንጋፈጥ እንሆናለን።

በጥሩም ይሁን በመጥፎ በጓደኞቻችን ተፅእኖ ሥር እንወድቃለን። ይህ ደግሞ ልናስተባብለዉ የማንችል ሀቅ ነዉ። ከመጥፎ ተፅእኖ ራሳችነን ነፃ ለማድረግ ጓደኛ የምንመርጥበትን መስፈርት ልናስተካክል ይገባል።

ከጓደኞቻችን ጋር ወደ ተሻለና መልካም ወደ ሆነ ነገር ለመድረስ ዛሬ ላይ ምን አይነት ጓደኛ መምረጥ እንዳለብን መወሰን ይኖርብናል። አለበለዚያ ግን በጓደኞቻችን እና በእኛ መካከል ያለው ጉዞ የቅፍለቶች ጉዞ ነው የሚሆነው።

ለዚህም ነበር የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ለምንመርጣቸዉ ጓደኞቻችን ትኩረት እንድንሰጥ የመከሩን። ጓደኞቻችን በሙሉ የአሏህን መንገድ እንዳንዘነጋ የሚያስታዉሱን መሆን ይኖርባቸዋል።

የአሏህ መልእክተኛ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) መርጠዋቸዉ የነበሩት ሰሃቦች በጠቅላላ ከርሳቸዉ ጋር እስከ መጨረሻዉ የዘለቁትን እና በተልዕኴቸዉም ተስፋ ያልቆረጡትን ነበር።

  • ምርጥ ጓደኛ ማለት ስንረሳ አስታዋሻችን ፤ ስንጨነቅ ፍቅርን እና ብርታትን ለጋሻችን የሆነ ነዉ።
  • ምርጥ ጓደኛ ለዱንያ ብቻ ሳይሆን በአኼራም ጠቃሚ ነዉ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከገለፁዋቸዉ ዓርሽ ጥላ ስር ከሚቀመጡት ሰባት አይነት ሰዎች አንዱ ለአሏህ ብለዉ የተዋደዱ ሁለት ጓደኛሞች ናቸዉ።

  • ምርጥ ጓደኛ ከራስ ፍላጎት የወንድሙን ፍላጐት ያስቀድማል
  • ምርጥ ጓደኛ ለራሱ የወደደዉን ለወንድሙ ይወዳል

ለዚህ ዉዴታዉ መሠረቱ የነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ንግግርን ነዉ።

ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) በቡኻሪ ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 12 ላይበተዘገበው ሐዲስ “ከናንተ አንዳችሁ ለራሱ የሚወደዉን ነገር ለወንድሙ እስካል ወደደ ድረስ አላመነም” ብለዋል።

  • ምርጥ ጓደኛ ለወንድሙ በሩቅ ዱአ ያረግለታል
  • መጥፎ ጓደኛ ግን ሁሌም ከግል ጥቅሙ ጋር ተንቀሳቃሽ ነዉ።

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በጉዞ አጋሮቻቸዉ ጓደኛ ለመምረጥ ምንድ ነዉ መሥፈርቱ? ተብለዉ ተጠይቀዉ ተወዳጁ የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) “ያን ጓደኛ ምረጥ: ባየኽዉ ወቅት አሏህን የምታስታዉስበት፤ ከእሱ ጋር ባወራህ ወቅት ስለ አሏህ ያለህን እዉቀት የሚጨምርልህ እና ከሞት ቡኋላ ላለዉ ተጠያቂነት አስታዋሽህ የሆነዉን” ብለዋል።

  • የምንመርጠዉ ጓደኛ ለዱንያ ጥቅም ብለን ሳይሆን ለአሏህ ብለን መሆን አለበት።
  • የምንመርጠዉ ጓደኛ የጥሩ ስነ-ምግባር ባለቤት ፤ አሏህ ያዘዘዉን የሚሠራ ፤ አሏህ ከከለከለዉ ነገሮች የራቀ መሆን አለበት።
  • የምንመርጠዉ ጓደኛ በጥሩ መካሪ ከመጥፎ ከልካይ መሆን አለበት።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top