በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል አንቀቡጥ አንቀፅ 57 ላይ እንዲህ ይላል፦

              =<({አል-ቁርአን 29:57})>=
{57} ሁሏም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት።

ሞት ምንኛውም ሰው ከሷ ማምለጥ የማይችላት እውነታ ናት። በእያንዳንዷ ቀን ፣ ሰዓት እና ደቂቃ ወደ እሷ ነው የምንቀርበው። በ2007 በወጣው የሲ አይኤ ፍክት ቡክ መረጃ መሰረት በእያንዳንዷ ደቂቃ ሁለት ሰዎች ይሞታሉ። ይህ በአመት ሲሰላ ደግሞ 57.9 ሚልዪን ሰዎች የሞትን እጣፋንታ ይቀምሳሉ።

ከዚህ በፊት የነበሩ ነገስታቶችና ባለሃብቶች የታሉ? ባንድ ወቅት ቆነጃጅት እና ወይዛዝርት ፣ ታዋቂ ፣ ዝነኛ ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበሩ ሰዎች የታሉ? 

ሞት ከዱንያ ወደ አሂራ የሚደረግ ጉዞ እንጅ አደጋ አይደለም። ሆኖም ስለሞት ማስታወሳችን የመፈጠራች አላማ ምን እንደሆነና ከሞት ብኋላ ላለው ህይወት እንድናሰላስልና  እንድናስተነትን ያደርገናል።

=<({አል-ቁርአን 4:78})>=

{78} የትም ስፍራ ብትሆን በጠነከሩ ህንፃዎች ውስጥ ብትሆንም እንኳ ሞት ያገኛችኋል።

አሏሁ አዘወጀል የፈጠረን እሱን በብቸኝነት ከመገዛት አላማ ጋር እንደሆነ በቁርአኑ አሳውቆናል።

=<({አል-ቀርአን 51:56})>=

{56} የሰው ልጅንም ሆነ አጋንትን አልፈጠርኳቸውም እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጅ።

እንዲሁም በሌላ የቁርአን አያ ሞትና ህይወትን የፈጠረበትን አላማ ሲገልፅ እንዱህ አለ፦

               =<({አል-ቁርአን 67:2})>=

{2} ያ የትኛችሁ ስራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ ሞትና ህይወትን የፈጠረ ነው። እሱም አሸናፊ መሐሪ ነው።

አንድ ሰው ለቅሬ ገንዘብ ስለከፈለ ወይም ደግሞ የሚቀበርበትን ቦታ ተናዞ ስለ ተናዘዘ ለሞት ተዘጋጅቷል ማለት አይቻልም። ይልቁንም በህይወት እያለ የሚፈልገውን ነገር አሟልቷል ነው ልንል የምንችለው። አሏህን መገዛት ማለት በትዕዛዙ መሰረት ህይወትን መምራትና መልካም ስራዎችን መስራት ሲሆን ለሞት መዘጋጀት ማለት ደግሞ ለአኺራ የሚሆነንን መልካም ስራ በመስራት ስንቅ መያዝ ማለት ነው።

ኢባዳ ወይም የአምልኮት ተግባር የሚለው ፅንሰ ሃሳብ በኢስላም ሁሉን አቀፍ እንጅ ለሶላት ወይም ለዱአ ብቻ አይደለም። ስለዚህ አሏህን የሚያስደስት ማንኛውም ተግባር እንደ ኢባዳ ወይም እንደ አምልኮት ተግባር ይቆጠራል። በዚህም መልካም ሰሪ አማኞች ይመነዱበታል።

አንድ ምሳሌ እናንሳ ሁለት ሰዎች ወደ ማያውቁት ሃገር ለመጓዝ ትኬት ቢቆርጡና አንደኛው ከመሄዱ በፊት ስለዛ ሐገር ቋንቋ ፣ ባህል ፣ ስርዓት ቢማርና  ሌላኛው ደግሞ እነዚህን ነገሮች ሳይማር ቢቀር ያለምንም ችግር ፣ ያለምንም መጨናነቅና ፍርሃት ብዙም ግራ ሳይጋባ እዛ ሐገር በደስታ የሚኖረው የትኛው ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?  አሏህ እንዲህ አይነቱን ሰው ሲገልፅ ነበር በቁርአኑ እንዲህ ያለው፦

=<({አል-ቁርአን 23:99-100})>=

{99} (ከነሱ መካከል) በአንዳቸው ላይ ሞት በመጣበት ጊዜ ጌታየ ሆይ! መልሰህ ላከኝ ይላል። {100} በተውኩት ነገር በጎን ልሰራ እከጅላለሁና ይላል።

ጀሃነም የገቡ ሰዎች ጀሃነም ምን እንዳስገባቸው በተጠየቁ ጊዜ የሚሰጡትን መልስ አሏህ በቁርአኑ አስቀምጦታል።

           =<({አል-ቁርአን 74:43-47})>=

“ከሰጋጆች አልነበርንም ይላሉ። ሚስኪኖችንም አናበላም ነበር። ከዘባራቂዎች ጋር እንዘባርቅ ነበር። በፍርዱ ቀንም እናስተባብል(እንዋሽ) ነበር። ጥርጣሬ የሌለው(ሞት) እስኪመጣብን ጊዜ ድረስ ይላሉ።”

የመፈጠራችን አላማ 

=<({አል-ቁርአን 23:115})>=

{115} ያለምንም አላማ ለጨዋታ የፈጠርናችሁና ወደ እኛ እንደማትመለሱ ታስባላችሁን?

በዱንያ ህይወት እያንዳንዷ ስራችን ትመዘገባለች አሏህ(ሰ.ወ.ተ) በሱረቱል ካህፍ አንቀጽ 49 ላይ እንዲህ ይላል፦

               =<({አል-ቁርአን 18:49})>=

{49} መጽሐፉ ይሰጣቸዋል፤ ሙጅሪሞችም በውስጡ በተመዘገበው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። ዋ! ጥፋታችን በቁጥር የተመዘገበ ቢሆን እንጅ ትንሽንም ትልቅንም ነገር የማይተው የሆነ ምን አይነት መጽሐፍ ነው ይላሉ። የሰሩትንም ስራ ሁሉ ከፊትለፊታቸው ተቀምጦ ያገኙታል። ጌታህም አንድንም አይበድልም።           

=<({አል-ቁርአን 62:8})>=

{8} ያ ከእሱ የምትሸሹት ሞት እሱ በእርግጥ ያገኛችኋል። ከዚያም ሩቅንና ቅርቡን አዋቂ ወደ ሆነው ጌታ ትመለሳላችሁ በላቸው።

እነዚያ በአሏህ የአመኑና መልካም ስራዎችን አጥርተው ለአሏህ ብለው የሰሩ በጀነት ይመነዳሉ።

            =<({አል-ቁርአን 36:55-57})>=

“በእርግጥ የጀነት ሰዎች ያን ቀን በአስደሳች ነገሮች ይጨናነቃሉ። እነሱና ሚስቶቻቸው ደስ የሚል ጥላ ውስጥ ሆነው በዝፋኖች ላይም ጋድም ይላሉ። በውስጧም ፍራፍሬዎችና የሚጠይቁት ነገር ሁሉ አላቸው።”

የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አሏህ(ሱ.ወ.ተ) አይኖች አይተውት የማያውቁ ጆሮዎች ሰምተውት የማያውቁ የሰው ልጆች ልብ አስቦት የማያውቅ ውብ ነገሮችን ለደጋግ ባሮቼ አዘጋጅቻለሁ ብሏል ብለዋል።

እያንዳንዷ እስትንፋሳችን አየር ወደ ውስጥ ማስገባትና ማስወጣትን የያዘ ሲሆን አንዱ ሌላውን ያለ ማቆም ይከተላል። ይህ ሂደት በተፈጥሮ ያለኛ ቁጥጥር ወይም ንቃተ ህሊና ይፈጠራል። እያንዳንዷ እስትንፋሳችነም በህይወት ለመቆየት ምክኒያት ነው። በእያንዳንዷ እስትንፋሳችነም ህይወታችን ይራዘማል።

ነገርግን ይህ አንድ ቀን ያቆማል። ያኔ የመጨረሻ እስትንፋሳችን ላይ ቀልባችን በምን ሁኔታ ላይ ይሆን? በዚህ መጽሐፍ ኡስማን ኑሪ ቶፕባሽ ለሞት የመዘጋጀትን አስፈላጊነት ይጠቁመናል። እያንዳንዱ ህይወት ያለው ፍጡር በሙሉ ይሞታል። ይሁን እንጅ ሁሉም ህይወት ያላቸው ፍጡራኖች ለዚህ ለመጨረሻ እስትንፋስ በመዘጋጀት ህይወታቸውን አያሳልፉም።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top