ኒወርክ ከተማ ውስጥ የነበረው የአለም ንግድ ማዕከል መንትያ ህንፃ ተቆራርጦ አመድ የሆነው በፈረንጆቹ የቀን አቆጣጠር መስከረም 11/2001G.C ነው። ያኔ አለምን አስደንግጧል።
ቀኑ 11
ወሩ 9
ህንፃው የያዘው የወለል ብዛት 110 ነው።

ይህን ቁጥር አስታውሱ 11_9_110
አሁን ቅዱስ ቁርአንን ክፈቱና
ጁዝዕ 11
ምዕራፍ 9
አንቀፅ 110 ተመልከቱ

የዚህ አንቀፅ የአማርኛ ትርጉም: “የገነቡት ግንባታ በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅናና የጥርጣሬ ምንጭ ከመሆን ፈፅሞ አይወገድም፤ ልቦቻቸው (በሞት) ካልተቆራረጠ በቀር። አሏህ ሁሉን አዋቂ ጥበበኛ ነው።” (አል-ቁርአን 9:110)

ከዚህ አንቀፅ ቀደም ብሎ ያለው አያ እንዲህ ይላል: “የግንቡን መሰረት አሏህን በመፍራትና ውዴታውን በመፈለግ ላይ ያደረገ ሰው ይበልጣል ወይስ ጎርፍ በሸረሸረው ለመናድ በተቃረበ የገደል አፋፍ ላይ ግንቡን የመሰረተና በእርሱ (ይዞት) በገሃነም እሳት ውስጥ የወደቀ ሰው (ይበልጣል)? አሏህ በደለኛ ህዝቦችን አይመራም።” (አል-ቁርአን 9:109)

እነዚህ አንቀፆች የተገለፁት ከ1439 አመታት በፊት ነው። በእርግጥ ቅዱስ ቁርአን ለምትረዳ ልብ በር ከፋች ነው።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top