በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

የሰው ልጅ ለአለማዊ ትምህርቱ ይደክማል፤ ለዱንያዊ እውቀቱ ይጠበባል፤ ይፅፋል ፣ ያነባል ፣ ይማራል ፣ ይመራመራል። ጀነት ለማያደርሰው ሲራጥንም ለማያሻግረው ከንቱ እውቀት ያለ እንቅልፍ ያድራል። ይህ ሁሉ ሲሆን አይደክምም አይሰለችም። እኔጋ ሲደርስ ግን የሆነ ነገር እጁን ይይዘዋል፤ ፍላጎቱን ያስረዋል። በብዙ ሙስሊሞች ቤት በሳጥናቸው ታሽጌ በግድግዳቸው ተንጠልጥሌ አለሁ።

ነገርግን በዕለት ተዕለት ኑሯቸው በማህበራዊ ጉዳዮቻቸው ውስጥ የለሁም። አብዛሃኛዎቹ አያውቁኝም የሚያውቁኝ አያነቡኝም የሚያነቡኝ አይተገብሩኝም። አሊፍ ባን ሳያውቁ ሁለት ፀጉር ያበቀሉ ብዙ ናቸው። ትርጉሜን ለማወቅ ሳይጣጣሩ ቀብር የገቡ በርካቶች ናቸው። ለሙዚቃ ፣ ለተራ ወሬና ለማይረባ ቀልድ ጆሮ የሚቆመው የሰው ልጅ ለእኔ ጆሮውን መንፈጉ ምላሱ መተሳሰሩ እጅግ ያሳዝነኛል። በእርግጥ ረመዷን ሲደርስ እታውቅ ይሆናል። ጭንቅና ችግር ሲበረታ እጠቆም ይሆናል ፈውስ ብርሃን መድህን መንገድና ህይወት መሆኔ በሁሉም ሰው ዘንድ ይታወቃል። ታዲያ ምነው የሰው ልጅ እኔን ለማንበብ ስለእኔ ለማወቅና ለመረዳት ጊዜ አጣ? የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ ይህን ቁርአን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት ብለው ከከሰሷቸው እንዳንሆን ያሰጋል።

                 =<({አል-ቁርአን 25:30})>=
{30} ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ ይህን ቁርአን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top