ጀነት ሃያሉ አሏህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀው ዘላለማዊ የደስታ ቤት ነው፡፡ ይህ ዘላለማዊ ደስታ አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ ነው፡፡ ነብዩ(ﷺ) ስለ ጀነት ሲናገሩ ‹‹አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት ፣ የሰው ልጅ ልብ አስቦት የማያውቅ ነገር አሏህ ለባሮቼ አዘጋጅቻለሁ አለ›› ብለዋል፡፡ ይህን ሐዲስ ያስተላለፉት አቡ ኹረይራ የሚከተለውን የቁርአን አያ አያይዘው ጠቀሱ

"ይሰሩት ለነበረው ምንዳ የአይን መርጊያ(መደሰቻ) የተደበቀላቸውን ፀጋ ማንኛዋም ነፍስ አታውቅም፡፡" {አል-ቁርአን 32፡17}

ጀነት የሚገቡ ሰዎች የፈለጉትን ፣ የተመኙትን ማንኛውንም ነገር ያገኛሉ፡፡ ጀነት ስምንት በሮች አሏት፡፡ አንደኛው ረያን ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህ በር ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ሲሆን ከእነሱ ውጭ ማንም ሰው በእሱ በኩል አይገባም፡፡ “በእሷ በገቡ ጊዜ ይቆለፋል፡፡ በእሷ በኩል ማንም አይገባም” {ቡኻሪ}

አብዛሃኛው የእሷ ህዝቦች ድሆች ናቸው፡፡ እቃዎቿም ከወርቅና ከብር የተሰሩ ናቸው፡፡ በእሷ የሚገቡ ሰዎች ከሃር የተሰሩና የተጠለፉ አረንጓዴ ልብሶች አላቸው፡፡ ከብር በተሰሩ አምባሮች ያጌጣሉ፡፡ ከተንቆጠቆጠ ማረፊያ ይተኛሉ፤ የሚያቃጥል ፀሐይ ወይም የሚቀዘቅዝ ብርድ አይነካቸውም፡፡ ከጥላዎች ፣ ከምንጮች እና ከፍራፍሬዎች መሃል እንዲሁም ከፈለጉት እና ከተመኙት ቦታ ይሆናሉ፡፡ ከጀነት መስህቦች ውስጥ አንዱ የከውሰር ወንዝ ነው፡፡ ውሃው ከወተት የነጣ ፣ ከማር በላይ የሚጣፍጥ እና ዳርቻው(ተረተሩ) ከሉል የተገነባ ነው፡፡

ጀነት የተለያዩ ደረጃዎች አሏት፡፡ በጣም ከፍተኛው ደረጃ ጀነተል ፊርደውስ ተብሎ ይጠራል፡፡ ነብዩ(ﷺ) በአንድ ወቅት ‹‹አሏህን ስጠይቁ፤ ፊርደውስን ጠይቁ›› ብለዋል፡፡ (መጅመእ አዝዋኢድ)

ስለ ጀነት ሰዎች አሏህ በቁርአኑ ሲናገር እንዲህ አለ፡ “እነዚያ የጌታቸውን ፊት(ውዴታ) ፈልገው የታገሱት ፣ ሶላታቸውን የሰገዱ ፣ ባስገኘናቸው ነገር በድብቅም በግልፅም ምፅዋት የሰጡ ፣ ክፋትን በመልካም የመለሱ እነሱ መልካም ፍፃሜ አላቸው፡፡ የአድን ጀነት(ዘላለማዊ የአትክልት ቦታ) ከወላጆቻቸው ፣ ከሚስቶቻቸው እና ከልጆቻቸው መሃል መልካምን የሰሩ ይገባሉ፡፡ መልአክቶችም ወደ እነሱ በእያንዳንዱ በር ይገባሉ፡፡ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን፤ (ይህ ምንዳ) በመታገሳችሁ ነው፡፡ በእርግጥ የመጨረሻዋ ቤት ምንኛ ታምር! ይሏቸዋል፡፡ (አል-ቁርአን 13፡22-24)

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top