ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው። የተውባ የቃል በቃል ትርጉሙ መመለስ ማለት ሲሆን አሏህን ወደ ማስታዋስ እና ወደ መታዘዝ መምጣት ማለትም ነው።

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ለአለማት ጌታ ለሆነው ለአሏህ ይገባው። የአሏህ ሰላምና እዝነት በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ፣ በቤተሰቦቻቸው ፣ በሶሃቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ እስከ የውመልቂያማ ድረስ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

ተውባ በማድረግ ሐጢያተኞች ከሐጢያታቸው ይማራሉ። ምክኒያቱም አሏህ (ሱ.ወ.ተ) እጅግ በጠም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ መሃሪ ነውና።

አሏህ ከኛ ሙሉእነትን አይጠብቅም፤ ከኛ የሚጠብቀው ስተት በሰራን ወቅት ከአመፀኝነት ፣ ከወንጀለኝነት እና ካለመታዘዝ ወጥተን አሏህን ያዘዘንን ነገር ሁሉ ለመታዘዝ ፣ የከለከለንን ሁሉ ለመከልከል በተውባ ወደ እርሱ መመለስ ብቻ ነው።

ነገርግን ለብዙ ጊዜ ወንጀል እየሰራን፤ ከአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ምህረትና ከለላን ካልሻትን ምህረቱንም ካለመን ነፍሳችንም መወንጀሏን ትቀጥላለች፤ በወንጀላችነም ብዛትና ፅናት ትበሰብሳለች፤ መመለሻችንም የከፋ ይሆናልና ይህ ከመከሰቱ በፊት የአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ፍራቻ በልባችን ውስጥ ማኖር ይኖርብናል።

  • መወንጀልን ሆንብለን ማቆም አለብን
  • በወንጀላችን ላይ ልባዊ የሆነ ፀፀት ይኑረን
  • እራሳችነን ወንጀል ላይ ከሚጥሉ ነገሮች ሁሉ እናርቅ

ሁለት የበደል አይነቶች

  • በአሏህ(ሱ.ወ.ተ) እና በባሪያው መካከል ያለ
    ለምሳሌ:- ሽርክ ፣ ዚና ፣ ግድያ ፣ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ወ.ዘ.ተ
  • በሌሎች ሰዎች ላይ ያደረስነው መጥፎ ስራ ለምሳሌ፡- ሐሜት ፣ መስረቅ ፣ ዋሽቶ ማጣላት ወ.ዘ.ተ

በሌላ ሰው ላይ የሰራ ነው ወንጀል ካለ ያን ወንጀል ወይም ስህተት መጠገን አለብን። መጥፎ ነገሮች የተናገርነው ፣ ያማነው ፣ የሰረቅ ነው ወይም በሌላ መንገድ የጎዳነው ሰው ካለ አውፍ እንዲለን ደጋግመን መጠየቅ ወይም ሐቁን መመለስ ይኖርብናል።

በደል ወይም ወንጀል ከሰራን እና በሰራ ነው ነገር ላይ ከተፀፀትን ወንጀላችን ጉምን አልፎ ሰማይን የሚነካ ቢሆን እንኴ ከልባችን ከቶበትን አሏህ ይምረናል። ከዚህም በላይ አሏህ መጥፎ ስራዎቻችነን በመልካም ነገር ሊቀይርልን ቃል ገብቶልናል። ይህም በአሏህና በባሪያው መካከል ላለ በደል ወይም ወንጀል ነው።

“እነዚያ የተፀፀቱት ፣ ያመኑትና መልካም ስራን የሰሩት ሲቀሩ። ለነሱም አሏህ መጥፎ ስራዎቻቸውን ሃጢያታቸውን በመልካም ስራ ይቀይርላቸዋል። አላህም እጅግ መሃሪ አዛኝ ነው።”

{አል-ቁርአን 25 : 70}

በሌሎች ሰዎች ላይ ላደረስነው በደል አሏህ ይቅር አይለንም። የበደልናቸውን ሰዎች ከልባቸው አውፍ እንዲሉን መጠየቅ ወይም ሃቃቸውን መክፈል ይኖርብናል። ያሲሆን አሏህም ይቅር ይለናል። ሆኖም ስራችንን ፣ ንግግራችንን እና ልባችንን ለማፅዳትና አሏህን ወደ መታዘዝ ጎዳና ለመምጣት ተውባ እና እስቲግፋር ማዘውተር ይኖርብናል።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
Ahmed Yesuf

ፅናት

ፅናት ለተነሳንበት አላማ ተግባራዊነት የሚያስፈልገውን ዋጋ የመክፈል ችሎታ ነው፡፡ ፅናት ፈፅሞ እጅ ያለመስጠት ጥበብ በህይወት ውስጥ ሁላችነም አድካሚ እና አሰልች

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top