በአለም ዙሪያ ምን እየሆነ እንዳለ ታውቃላችሁ?

እስልምና ጫና እየተደረገበት ነው። በአለም ዙሪያ ከክርስቲያኖች ፣ ከአይሁዶች ፣ ከሂንዱዎች ፣ ከአለም ባንክ ፣ ከሬድዮ ፣ ከቴሌቪዥን ፣ ከህትመት ሚድያ ፣ ከጋዜጠኞች ፣ ከፓለቲከኞች ጥቃት እየተፈፀመበት ነው። ጥቃታቸው የሚባራ አይደለም። እንዲሁም ጥቃታቸው ሁሉን አቀፍ ነው። ማህበራዊ ፣ ተቋማዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ነው።

ማንኛውንም የአለም ችግር ብትወስድ የመጨረሻ ምክኒያት የሚያደርጉት እምነትን ነው።

አሁን ላይ እስልምናን በክፍ ያነሳሉ፤ ለስውር አጀንዳቸው እና ፍላጎታቸው መጠቀሚያ ያደርጋሉ። ፀረ-ኢስላም ዘመቻ በመጨመር ላይ ነው። ፀረ-ኢስላም ሃይሎች ሙስሊሞችን ለመዝለፍ ለማንቋሸሽ ያገኙትን አጋጣሚ ሁሉ ከመጠቀም ወደ ኋላ አይሉም። እስልምና እንዳይስፋፋ ፣ ሰዎች ሃይማኖቱን እንዳይረዱ ለማድረግ የማያደርጉት ነገር የለም። መስጅዶችን ያፈርሳሉ ፣ ቁርአን ያቃጥላሉ። የፀጥታ አካላትም ለዚሁ የዘላኖች ተግባር ተባባሪ የሚሆኑበት አጋጣሚ ሰፊ ነው።

ታዲያ ይህ ሁሉ ፀረ-ኢስላም ዘመቻ እና ጥላቻ ለምን ይመስላችኋል?

ምክኒያቱም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ እንደገና እስልምና በድጋሚ እያንሰራራና እያበበ በመምጣቱ ነው። የእስልምና ህዳሴ እና እድገት አሁንም በድጋሜ አለ።

ወደ ፊት እስልምና ግዛት ድል ከተመለሰ አሁን ያለው የካፒታሊስት ስርአት አለም ላይ ቦታ አይኖረውም። ለዛም ነው እስልምናን እያጠቁ ያሉት።

በነዚህ ተቃራኒና ተፃራሪ ሃሳቦች ምክኒያት ነው የጥፋት ዘመቻ ቅስቀሳ እና ጥቃት እየፈፀሙ ያሉት። የሙስሊሙ ኡማ አሁን ላይ ወሳኝ ጊዜ ላይ ይገኛል።

ይህን ሰይጣናዊ ዘመቻና ቅስቀሳ ለማክሸፍ እና ለእራሳችን አላማ ለመጠቀም እንዲሁም የሰዎችን የተሳሳተ አመለካከት እና ጭፍን እምነት ለማስተካከል በቻልነው ሁሉ በሶስት ግንባር ተሰልፈን መፋለም ይኖርብናል።

  1. ኛ እስላማዊ በራሪ ወረቀቶችን ፣ ብክሌቶችን በመፃፍና በመተርጎም ብዙ ሽህ ኮፒዎችን በማባዛት ለህዝብ ማሰራጨት እና በማህበራዊ ሚድያዎች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በግለሰብም ይሁን በቡድን ተደራጅቶ ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ ይጠበቅብናል። በራሪ ወረቀቶች መጣጥፎች በተለያዩ የሐገሪቱ ቋንቋዎች እንዲዘጋጁ ማድረግ በየክልሉ ፣ በየወረዳው ፣ በየቀበሌው እንዲዳረስ ማድረግ።
  2. ኛ የነብዩን(     ) ትክክለኛ ማንነት እና ስብዕና ለማያውቁ ሰዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት። በጽሑፎቻችን ፣ በብክሌቶች ፣ በማህበራዊ ሚድያ ፣ በንግግራችን እና ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ታላቅ ስብዕናቸው ከቅዱስ ቁርአን ጋር የተሳሰረ እንደሆነ ማሳየት።
  3. ኛ በክርስትና እና በመጽሐፍ ቅዱስ ዙሪያ ያሉ ድርሰቶችን እና ቅራኔዎች በመቃኘት በተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ። የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና ጭፍን እምነታቸውን ትተው ሚዛናዊ ሆነው እውነትን እንዲፈልጉ መርዳት። እንዲሁም የውይይትና የክርክር መድረኮችን መፍጠር ነው።
Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top