ሰባቱ የአለማችን ድንቃድንቆች ምንድን ናቸው?

በአንድ ወቅት አንድ መምህር ተማሪዎች የአለማችን ድንቃድንቅ እንዲዘረዝሩና እና ታሪካቸውን እንዲያብራሩ ይጠይቃቸዋል።

“የአለማችን ድንቃድንቆች”

ምንም እንኳ አለመስማማት ቢኖርም የሚከተሉት ግን አብላጫ ድምፅ አግኝተዋል።

1 የግብፅ ፒራሚዶች
2 ታጅመሃል
3 ታላቁ ቦይ ካንየን
4 የፓናማ ቦይ
5 የአንፒየር ስቴት ህንፃ
6 ፔተር ባሳሊካ
7 የቻይና ትልቁ ግንብ

መምህሩ የተማሪዎቹን የክፍል ስራ እየሰበሰበ እያለ አንድ ተማሪ ግን የክፍል ስራዋን ያለጨረሰች መሆኑን ተመለከተ። መስራት ከበደሽ እንዴ? ብሎ ይጠይቃታል።

አዎ! በጣም ብዙ ስላሉ የትኛውን አንስቼ የትኛውን እንደምተው ከብዶኝ ነው” ስትል መለሰች።

“እስኪ የፃፍሽውን ብቻ ንገሪን። ከቻልን እናግዝሻለን አላት።”

ተማሪዋም እንደማመንታት እያለች እኔ እንደማስበው የአለማችን ሰባቱ ድንቃድንቅ ማየት ፣ መስማት ፣ መንካት ፣ መቅመስ ፣ ማሽተት ፣ መሳቅ እና መውደድ ናቸው አለች።

የመማሪያ ክፍሉ ፀጥ አለ። ኮሽታ እንኳ አልነበረም። እንደ ቀላል እና እንደተለመድ ነገር ልናስበው እንችላለን። ነገርግን እጅግ በጣም አስደናቂ ነገሮች ናቸው። እነዚህ ነገሮች በህይወታችን ውስጥ እፁብ ድንቅ የሆኑ የሰው ልጅ ሊሰራቸው ወይም የሰው ልጅ ሊገዛቸው የማይችላቸው ናቸው።

አስኪ አንድ ጊዜ አሏህ በኛ ላይ ያደረጋቸውን ውብ ፀጋዎች አስበን አልሃምዱ ሊላህ እንበል? እኔ አልኩ…. አልሃምዱ ሊላህ!

መልዕክቱን ከወደዱት ቢያንስ ለሶስት ሰዎች ሼር አድርጉት።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top