የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ዳዕዋ (ትምህርት)

Author picture
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ዳዕዋ (ትምህርት) የሰጡት በዘጠንኛው ዙልሂጃ በ10ኛው አመተ ሂጅራ በአረፋ ተራራ መካከል በሚገኘው የኡርናህ ሸለቆ ውስጥ ነበር።
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ዳዕዋ (ትምህርት)

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ዳዕዋ (ትምህርት) የሰጡት በዘጠንኛው ዙልሂጃ በ10ኛው አመተ ሂጅራ በአረፋ ተራራ መካከል በሚገኘው የኡርናህ ሸለቆ ውስጥ ነበር።

ሰዎች ሆይ! ከዚህ አመት ቡኋላ በድጋሚ ከናንተ መካከል መሆኔን አላውቅምና ጆሮዋችሁን አውሱኝ። ስለዚህ የምነግራችሁን ነገር በደምብ አድምጡ፤ ንግግሬንም ዛሬ እዚህ ቦታ ላይ ለሌሉ ሰዎች አድርሱ።

ሰዎች ሆይ! እንደምታውቁት ይህ ወር ፣ ይህ ቀን እና ይች ከተማ የተቀደሱ ናቸው። እናም የእያንዳንዱ ሙስሊም ህይወት እና ሃብት ንብረት የተቀደሰ አደራ እንደሆነ እወቁ። በአደራ መልክ የተሰጣችሁን ሸቀጦች (ንብረቶች) ለባለቤቶቻቸው መልሱ።

ማንንም አትጉዱ፤ ማንም አይጎዳችሁምና። በእርግጥም ጌታችሁን እንደምትገናኙ እና ስራዎቻችሁን እንደምትተሰሳቡ እወቁ። አሏህ አራጣ መብላትንም ከልክሏችኋል፤ ስለዚህ ሁሉም አራጣ ከእንግዲህ ሊቀር ይገባል።

ለሃይማኖታችሁ ደህንነት ሸይጧንን ተጠንቀቁ። ሊያጠማችሁ በሚችልባቸው ትልልቅ ነገሮች ላይ ተስፋ አጥቷልና በትንንሽ ነገሮች እሱን ከመከተል ተጠንቀቁ።

ሰዎች ሆይ! ሴቶቻችሁን በተመለከተ በእነሱ ላይ መብቶች ያላችሁ መሆኑ እውነት ነው። ነገር ግን እነሱም በናንተ ላይ መብቶች አሏቸው። መብታችሁን ከጠበቁ በደግነት የመመገብና የመልበስ መብት ይገባቸዋል።

አጋሮቻችሁ እና እረዳቶቻችሁ ናቸውና በደምብ ተንከባከቧቸው፤ መልካም (ደግ) ሁኑላቸው። ካልፈቀዳችሁላቸው ጋር ጓደኛ ላያበጁና ዝሙትን ላይፈፅሙ ይህ የእናንተ መብት ነው።

ሰዎች ሆይ! በቅንነት አዳምጡኝ። አሏህን ተገዙ ፣ አምስት አውቃ ሶላት ስገዱ ፣ በረመዷን ወርም ፁሙ ፣ ንብረታችሁንም በዘካ መልክ ስጡ ፣ የቻላችሁም ሐጅ አድርጉ።

እያንዳንዱ ሙስሊም ለሌላኛው ወንድም እንደሆነ ታውቀላችሁ። ሁላችሁም እኩል ናችሁ። ማናችሁም በሌላው ላይ በላጭነት የለውም በተቅዋውና በመልካም ስራው ብቻ ቢሆን እንጅ።

አስታውሱ! አንድ ቀን ከአሏህ ፊት ቀርባችሁ ለስራዎቻችሁ መልስ ትሰጣላችሁ። እናም ካረፍኩ (ከሞትኩ) በኋላ ከቀጥተኛው መንገድ መጥመምን ተጠንቀቁ።

ሰዎች ሆይ! ከእኔ በኋላ ነብይ አይመጣም፤ አዲስ እምነትም አይፈጠርም። በደንብ አስቡ! ሰዎች ሆይ! ያስተላለፍኩላችሁን ንግግሬን ተረዱ።

ከኋላየ ሁለት ነገሮችን ትቸላችኋለሁ (ቁርአን እና ሱናን) እነሱን አጥብቃችሁ እስከያዛችሁ ድረስ አትጠሙም።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

እኔን ያደመጡ ሁሉ ንግግሬን ያስተላልፉ፤ እንዲሁም ሌሎች ለሌሎችም። የመጨረሻዎቹ ሰዎችም ንግግሬን በቀጥታ ካደመጡ ሰዎች በላይ በተሻለ የተረዱ(የተገነዘቡ) ሰዎች ይሁኑ። አሏህ ሆይ! ምስክሬ ሁን ለህዝቦችህ መልዕክትህን አድርሻለሁ። {በማለት ነበር የመጨረሻ ዳዕዋቸውን ያደረጉት}

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት

የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት የሚለው ትምህርት ፈተና 12 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 10 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 12

Bookmark question icon

1 ትክክለኛው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች ስንት ናቸው?

2 / 12

Bookmark question icon

2 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ሚስታቸው ማናት?

3 / 12

Bookmark question icon

3 ከነብዩ ሙሐመድ ተአምራቶች ውስጥ የሆነው የትኛው ነው?

4 / 12

Bookmark question icon

4 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጡት የጠቡባቸው ሴቶች የትኞቹ ናቸው?

5 / 12

Bookmark question icon

5 የነብያት እና የመልዕክተኞች ሁሉ ቁንጮ (የበላይ) ማን ነው?

6 / 12

Bookmark question icon

6 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረግ ከ _____ ይመዘዛል።

7 / 12

Bookmark question icon

7 ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተላኩት ለማን ነው?

8 / 12

Bookmark question icon

8 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በልጅነታቸው እና በወጣትነታቸው ዘመን _____ ሆነው ሰርተዋል።

9 / 12

Bookmark question icon

9 አንድ ሙስሊም ሰው ከሌሎች ሰዎች ውዴታ ሁሉ ማስቀደም (ማስበለጥ) ያለበት ለማን ነው?

10 / 12

Bookmark question icon

10 ከእስልምና ሃማኖት ውጭ ሌላ ሃይማኖት መከተል የተፈቀደ ነው።

11 / 12

Bookmark question icon

11 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሩትን ማመን ፣ ያዘዙትን መታዘዝ እና የከለከሉትን መከልከል እና መራቅ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

12 / 12

Bookmark question icon

12 የነብያት እና የመልዕክተኞች መደምደሚያ (ማብቂያ) የሆነው ነብይ የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ነብዩ ሙሐመድ

ነብዩ ሙሐመድ

ሙስሊም ሰው ከነብዩ ሙሐመድ ዝርዝር ታሪኮች ጋር እራሱን ማስተዋወቅ አለበት። ያ ሲሆን በሁሉም የህይወት ጉዳዮች ምሳሌነታቸውን መከተል ይችላል። ምክኒያቱም የህይወት ታሪካቸው ተጨባጭ የእስልምና እና የህግጋቱ

Read More »
የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት

አሏህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት እና ስብዕናዎች ከሁሉ የተለዩ አድርጓቸዋል። ይህ የነብዩ ሙሐመድ ባህሪያት ልቦች በፍቅራቸው እና በውዳሴያቸው እንዲነጉዱ ያደርጋል። በዚህ ጽሁፉ ውስጥ ከእነዚህ ባህሪያት የተወሰኑትን

Read More »

የነብዩ ሙሐመድ መልዕክት

ሃያሉ አሏህ መልዕክተኞችን ከላቀ ጥበብ ጋር የላካቸው ሲሆን ነብዩ ሙሐመድ ከሁሉም በላይ አልቆ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ (ማብቂያ) አድርጓቸዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ እነዚህንም ጥበቦች እና ነብዩ

Read More »

Share