✍ በኢብን ረጀብ ኢብን ሐንበሊ

ትርጉም: በአህመድ የሱፍ

ክፍል 1

Iqra

 

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

አርዕስት

  1. የቢድአ ፍች በኢስላም
  2. ቢድአን ለመረዳት የሚያገለግሉ አጠቃላይ ህጐች
  3. የቢድአ አደጋዎች እና የሚያስከትላቸው ውጤቶች
  4. የቢድአ ሰዎች አሉን የሚሏቸው ማስረጃዎችና ማስተባበያቸው
  5. ቢድአን ለመስራት ምክኒያቶች
  6. የቢድአ ማጥፊያ መንገዶች
  7. ተያያዥነት ያላቸው የቁርአን አናቅጽፅቶች
  8. ተያያዥነት ያላቸው ሐዲሶች
  9. ተያያዥነት ያላቸው የሰለፎች ንግግር
  10. ተያያዥነት ያላቸው ታሪኮች
  1. የቢድአ ፍች በኢስላም
  • ኢማሙ ሻፊእይ(ረሂመሁሏህ) ከቁርአን ፣ ከሐዲስ ወይም ከሱሐቦቻቸው ንግግር መሰረት የሌለው ማንኛውም የኢባዳ ተግባር ቢድአ ነው ብለዋል።
  • ኢብን አልጀውዚ(ረሂመሁሏህ) ቢድአ ማለት በነብዩ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እና በሶሃቦቻቸው ዘመን ያልነበረ ከጊዜ በኋላ የተፈጠረ ማንኛውም የኢባዳ አይነት ቢድአ ነው ብለዋል።
  • ኢብኑ ረጀብ(ረሂመሁሏህ) ከሸሪአ መሠረት የሌለው ማንኛውም የኢባዳ አይነት ቢድአ ነው ብለዋል።

የቢድአን ፍች ለማጠቃለል ያህል ቢድአ ማለት ከቁርአን ፣ ከሐዲስ ፣ ከሸሪአ መሰረት የሌለው እና በረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እና በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን ያልነበረ ወይም ያላደረጉት የኢባዳ ተብየ አይነቶችን ሁሉ የሚያጠቃልል እና ከራሳችን ፍልስፍናና ስሜት በመነሳት ያልነበሩ ነገሮችን በዲነል ኢስላም ላይ መጨመር ነው።

  1. ቢድአን ለመረዳት የሚያገለግሉ አጠቃላይ ህጐች
  • የተፈበረከን (በፈጠራ የተገኘን) ሐዲስ መሠረት በማድረግ የሚደረግ የኢባዳ አይነት ቢድአ ነው። ለምሳሌ በረጀብ ወር የሚደረግ ስግደት
  • ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ያልሰሩት ያላከናወኑት ማንኛውም ኢባዳ ተብየ ተግባር ቢድአ ነው። ልክ ኒያን ሶላት ከመጀመራችን በፊት እንደ ማሰማትና ከአምስቱ ዋጅብ ሶላቶች ውጭ ላሉ ሱና ሶላቶች አዛን እንደ ማድረግ ማለት ነው።
  • ኢስላም እንደ ኢባዳ የማይቀበላቸውን ድርጊቶች አሏህን ለማስደሰት በሚል ሰበብ ወይም ኒያ የሚደረጉ ማንኛቸውም የልማድ ድርጊቶች ቢድ አናቸው። ለምሳሌ ያህል ቀጣይነት ያለው ዝምታ ፣ አለመብላት አመጠጣት ፣ አለማግባት ወ.ዘ.ተ
  1. አሏህን ለማስደሰት በሚል ሰበብ የተከለከሉ ነገሮችን መስራት ቢድአ ነው።

ባጠቃላይ ሁሉም የኢባዳ ተግባሮች ሊሰሩ የሚገባቸው ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በሰሩባቸው መንገዶች ብቻና ብቻ ነው። ይህም የሚከተሉትን ስድስት ሁኔታዎች ያሟላ መሆን ይኖርበታል



  • የኢባዳ ስራው ከሸሪአ ድንጋጌዎችጋ ሊስማማ ይገባል።

ያለበለዚያ ስራችን ውድቅና በራሳችን ጊዜ የምንጠምበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው። ስለዚህ መወሊድን ማክበር በራሱ ቢድአ ፣ ጥመት ነው። ምክኒያቱም በሸሪአ አልተደነገገም ፣ ሶሃቦች እንዲያከብሩ አልታዘዙምና።

  • የኢባዳ ድርጊቱ ከሸሪአ ክፍሎች (ዝርዝር ነገሮች) ጋር ሊስማማ ይገባል።

ስለዚህ አንድ ሰው ከሐጅ ቡኋላ በግመል ወይም በፍየል ፈንታ እንደ መሦዋዕት አድርጐ ፈረስ ቢያርድ ተቀባይነት አይኖረውም።

  • ኢባዳው በሸሪአ ከተደነገጉ ነገሮች ጋር በመጠን ሊስማማ ይገባል።

ስለዚህ አንድ ሰው በዙሁር ሶላት አራት ረከአ በመስገድ ፈንታ ሁለት ረከአ ጨምሮ ባጠቃላይ ስድስት ረከአ ቢሰግድ ተቀባይነት አይኖረውም። ድርጊቱም ጠማማ ተግባር ነው።

  • የኢባዳ ተግባሩ በምን አይነት መንገድ እንደሚከወን ከሸሪአ ጋር ሊስማማ ይገባል።

ስለዚህ አንድ ሰው ውዱእ ሲያደርግ እጁን በመታጠብ ፈንታ እግሩን በማጠብ ቢጀምር ተቀባይነት አይኖረውም።

  • ኢባዳው የሚደረግበት ሰዓት ከሸሪአ ጋር ሊስማማ ይገባል።

ስለዚህ ፀሀይ ስትጠልቅ የዙሁር ሶላትን መስገድ ተቀባይነት አይኖረውም።

  • ኢባዳው የሚደረግበት ቦታ ከሸሪአ ድንጋጌ ጋር ሊስማማ ይገባል።

ማጠቃለያ

አንድን ኢባዳ በረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም መንገድ ለመስራት ኢባዳው በዝርዝር ነገሮች ፣ በመጠን ፣ በቦታ ፣ በሰአትና በምን አይነት መንገድ መከወን እንዳለበት ከሸሪአ ድንጋጌዎች ጋር ሊስማማ ይገባል።

  1. የቢድአ አደጋዎችና የሚያስከትላቸው ውጤቶች
  • ቢድአ ለጥመትና ለክፍርና ቀዳሚ የሚያደርግ ወይም ጥመትን የሚያበስር ነው።
  • በአሏህ ስም መሠረት የለሽ ንግግር ማድረግን
  • ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለምን ማስተካከል ወይም እንከን አሉባቸው ብሎ ማመን
  • ሱና የሆኑ ነገሮችን መተውን
  • በሙስሊሞች መሃል ግጭት ማቀጣጠልን
  • ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የኢስላምን መልእክት ሙሉ በሙሉ አላደረሱም ብሎ መውቀስ (መተቸት)ን ያስከትላል።
  1. ቢድአን ለመስራት ምክኒያቶች
  • ድንቁርና
  • የራስን ስሜት መከተል
  • ጥርጣሬን አጥብቆ መያዝ
  • አሊሞች የሚጠበቅባቸውን ሚና እየተጫወቱ አለመሆ ናቸው።
  • በደካማ ወይም በተፈበረኩ ሐዲሶች ላይ ጥገኛ መሆን
  • ለሌሎች ሰዎች ስህትተ ድንበር ያለፈ ስሜታዊ ምላሽ መስጠት
  • የረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሶሐቦች ኢስላማዊ መልእክቶችን ወይም ፅሁፎችን በተረዱባቸው መንገዶች መረዳት አለመቻል
  • በጭፍን ከቢድአ ሰዎች ጋር መመሳሰል
  1. የቢድአ ማጥፊያ መንገዶች
  • ከቢድአ አደጋዎችና ውጤቶቹ ማስጠንቀቅ
  • ሰዎች ቁርአንና ሱናን ሰለፎቹ በተረዱበት መንገድ እንዲረዱና አጥብቀው እንዲይዙ ጥሪ ማድረግ
  • ደካማ(ዶኢፍ) እና ትክክለኛ(ሰሂህ) የሆኑ ሐዲሶችን ለይቶ ማወቅ
  • የዲን ትምህርት ቤቶችን ከቢድአ ነገሮች ማፅዳት
  • እውቀትን ማስፋፋት
  • ሰዎች በእምነታቸው ፣ በአቂዳቸው ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት ማስተካከል
  • የቢድአ ሰዎችን ማስጠንቀቅና ማሸነፍ
  • እውቀትን ከትክክለኛ ምንጭ መሻት

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top