እህቴዋ መስፈርት አታብዥ በጊዜ ተዘወጅ

በአንድ ወቅት ወላጆች ለልጃቸው ሚስት ሲፈልጉ ቆይተው “የሸህ እገሌን ልጅ ልንድርህ ነውና ሂድ እያት” አሉት። ገና እንዳያት ወደዳት። በሌላ ቀን ፈቃደኝነቷን ሊጠይቅ ሄዶ ስለትዳር ሀሳባቸዉ እና ስለወደፊት ዓላማቸው አወሩ።

ጥቂት ጊዜ አንገታቸውን ደፍተው ከቆዩ በኋላ “ቁርኣን ምን ያህል ሐፍዘሃል?” ስትል ጠየቀችው። “አይ ብዙ አላፈዝኩም፤ ምናልባት ካሁን በኋላ አሃፍዝ ይሆናል። ግን መልካም የአላህ ባርያ የመሆን ጉጉት አለኝ።” አለ። ጉጉቱን በቀልቧ ያዘችለት። “አንቺስ ሐፍዘሻል?” ሲል ጠየቃት። “የአማን ጁዝ ሐፍዣለሁ።” አለችው።

እውነቱን የነገራት መሆኑን ባወቀች ጊዜ ቀልቧ ወደደው። አሳዝኗትም፤ ወዳዉም ጥያቄዉን ተቀበለችው።

ከተጋቡ በኋላ ቁርኣን እንዲሳሃፍዛት ጠይቃው ከሱረቱ “መርየም” አብረው ጀመሩ።

ሒፍዙን ሳያቆሙ ቀጠሉ። በመጨረሻም ሁለቱም ቁርኣንን በቃላቸው ሸምድደው የሒፍዝ ሰርተፊኬት አገኙ። አላረፈችም፤ አሁን ደግሞ “ሐዲሥ ለምን አንሐፍዝም?” ብላ ቡኻሪን አጥንተው ጨርሰዋል።

በዚህ መሃል አንድ ቀን ለዚያራ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄደው ሳለ ባልየው በኩራት ለአባቷ “አባ..አ..አንድ ያልነገርንዎት ነገር አለ። አልሐምዱሊላህ ልጅዎ ቁርኣን ሐፍዛለች።” አላቸው። አማቹ በአግራሞት አዩትና ወደ ጓዳ ገብተው የልጃቸዉን የምስክር ወረቀቶች አምጥተው አሳዩት። አማች ባየው ነገር ደነገጠ። ልጅቷ ሳታገባው በፊት አስቀድማ ሐፍዛለች ለካ። ከቁርአን አልፋ ኩቱቡ ሲታንም ጭምር የጨረሠች ስለመሆኑ ማስረጃ አላት። ባል ተገረመና ዝም አለ።

ያኔ እንዲያ ያደረገችው የባሏ ሞራል እንዳይነካ ፈርታ ነበር። ኢልም የለህም፤ ቁርኣን አላፈዝክም ብላ አላጣጣለችዉም፤ በእውቀቱ ደረጃ አልናቀችዉም። እሱ እውነቱን በነገራት ጊዜ ከልቧ አስገባችው፤ ፈቀደችዉም። እንደሷ ቁርአን እንዲሐፍዝም ስለፈለገች በዚያ መልኩ አስጀመረችው። ሱረቱ አማን ሐፍዣላሁ ያለችውም እውነቷን ነበር አልዋሸችም። ምክኒያቱም ሱረቱ አማ ከ30 የቁርኣን ጁዞች አንዱ ነዉና።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top