የኮሮና ወረርሽኝ የማንቂያ ጥሪ!

Author picture
ስለ ኮሮና ወረርሽኝ የምናስበው ምንድን ነው? ቀርአን ምንይላል? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምን ብለዋል?
የኮሮና ወረርሽኝ የማንቂያ ጥሪ!

ስለ ኮሮና ወረርሽኝ የምናስበው ምንድን ነው? ቀርአን ምንይላል? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ምን ብለዋል? አስታውሱ! ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ ልክ እንደ ኮሮና ያለ በሽታ በተከሰተ ጊዜ ማለት ነው እንደ ሙስሊም ምን ማድረግ እንዳለብን መክረውናል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

“ወረርሽኑ በተከሰተበት ከተማ ፣ መንደር ፣ ቦታ ያለ ሰው አካባቢውን ለቆ አይውጣ፡፡ ወደ ተከሰተበት ቦታም አትሂዱ ብለዋል፡፡”

እንደ ሙስሊምነታችን ልናደርግ የሚገባው የመጀመሪያው ነገር ይህ ነው፡፡

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

አጋጣሚዎች

ጥያቄና መልስ፡ ወረርሽኝ እና ሙስሊም ሰው

ወረርሽኝ እና ሙስሊም ሰው የሚለው ርዕስ 7 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 7

Bookmark question icon

1 በወረርሽኝ ተጠቅቶ ሳለ ታግሶና አገግማለሁ ብሎ ተስፋ አድርጎ በመጠባበቅ ላይ እያለ የሞተ ሰው እንደ _____ ምንዳ ይፃፍለታል።

2 / 7

Bookmark question icon

2 እውነት ወይም ሐሰት፡ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ ሰበቦችን ሳያስቡ እና ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ጉዳዩን ለአሏህ ብቻ መስጠት በቂ ነው።

3 / 7

Bookmark question icon

3 በሽታን እና ወረርሽን መርገም ሸሪአዊ ብያኔው ምንድን ነው?

4 / 7

Bookmark question icon

4 እውነት ወይም ሐሰት፡ ወረርሽኝ በተከሰተ ጊዜ ከማህበረሰቡ ጥቅም ይልቅ የግለሰብ ጥቅም መብለጥ አለበት።

5 / 7

Bookmark question icon

5 አካላዊ ንፅህናን ለመጠበቅ የሚረዱ ግዴታዎችን እስልምና ደንግጓል። ከነዚህም ውስጥ

6 / 7

Bookmark question icon

6 አላማው ሆን ብሎ በሰዎች መሃል ወረርሽኙ እንዲስፋፋ ባደረገ ሰው ላይ ሸሪአዊ ብያኔው ምንድን ነው?

7 / 7

Bookmark question icon

7 የወረርሽኝ መስፋፋትን አስመልክቶ ማስረጃ የሌለው መረጃ በማህበራዊ ሚድያ ብታገኝ በእሱ ላይ ሊኖርህ የሚገባው ትክክለኛው አቋም ምንድን ነው

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ልክ እንደ ኮሮና ቫይረስ ያለ ወረርሽኝ በአለም ላይ እንዲከሰት የሚያደርገው አሏህ ነው፡፡ አንድም የአሏህ ቅጣት ፣ አንድም የአሏህ እዝነት ነው፡፡ የሰው ልጅ የቆሸሸች ነፍሱን የሚያጠራበት ነው፡፡

አሏሁ አክበር! አሏህን ለሚታዘዙ ሰዎች የኢማናቸው መፈተኛ እና ነፍሳቸውን የሚያጠሩበት በረካ ነው፡፡ አሏህን ለማይታዘዙ ፣ በትእዛዛቱ ላይ አመፀኞች ለሆኑ ደግሞ መቀጣጫ ነው፡፡

የማንቂያ ጥሪ ታውቃላችሁ አይደል፡፡ ሰው ከተኛበት የምትቀሰቅስ! በተዘዋዋሪ ይህ የአሏህ እዝነት ነው፡፡ አሂራን ማስታወሻ ነው፡፡

አሁን ቆም ብለን የምናስብበት ፣ የምናሰላስልበት ፣ እራሳችነን የምናደምጥበት እና የምንጠይቅበት ጊዜ ነው፡፡ ሰዎችን ስንሰርቅ ፣ ስናታልል ፣ ስናማ ፣ አሏህን ስናምፅ ፣ ብዙ ሐራም ነገሮችን ስንሰራ ቆይተናል፡፡

ለአሏህ ታዛዥ የሆነ ሰው የኢማኑ መፈተኛ ነው፡፡ አሏህን እያመፅን የኖርን ግን መቀጫችን ሊሆን ይችላል፡፡

ይሁን እንጅ አሁንም በተውበት ወደ አሏህ ለመመለስ እድሉ አለን፡፡ ይህ የማስጠንቀቂያ ጥሪ ነውና ወደ አሏህ በተውበት መመለስ እና በጎ ስራ መስራት አለብን፡፡

እንደምናውቀው ቻይና በግልፅ እስልምናን ማስተማር እና መተግበር ከማይቻልባቸው ሐገሮች ውስጥ አንዷ ናት፡፡ ባንዳንድ ቦታዎች ቁርአንን አቃጥለዋል ፣ መስጅዶችን አፍርሰዋል ፣ መስሊሞችን አሰቃይተዋል ፣ የኮሚኒስት ፓርቲ በሚፈልገው መልኩ ቁርአንን ለመከለስ እቅድ ነበረው፡፡

በእነሱ ላይ ምን ሆነ? አለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ምንድነው? አሜሪካ እንኳ ስኬቷን አድንቃለች፡፡ ምጣኔ ሃብታቸው በጣም አድጓል፡፡

ነገርግን አሏህ ሲሻ በስንት አመት ልፋት ያካበተችውን በሰከንድ ውስጥ እንድታጣው ያደርጋል፡፡ ውድ እህት ወንድሞቼ እኛ ከእዚህ ምን እንማራለን!

ዝምብሎ መቀመጥና ፎክስ ኒውስ ፣ ቢቢሲ ፣ ሲኤኔን ፣ ኢቢሲ ፣ ፋና ዜና ማድመጥ አይደለም፡፡ ከዚህ የአሏህ የማስጠንቀቂያ ጥሪ መማር አለብን፡፡ ሁሉንም ወደ እራሳችን ህይወት መልሰን እራሳችነን እንፈትሽ፡፡

እውቀት ፣ ገንዘብ ፣ ሃብት ፣ ጉልበት ፣ ጤና ቢኖረን አሏህ ሁሉንም በሰከንድ ውስጥ እንዳልነበር ያደርገዋል፡፡ ሁላችነም የእሱ ነን፡፡

አሁን ላይ ኮሮና በብዙ ሐገራት እየተስፋፋና እየተሰራጨ ነው፡፡ አሏህ ይህ እንዲሆን ከሻ አለም ላይ የትኛውም አካል ወይም ሃይል መመከት አይችልም፡፡ አሜሪካና ቻይና እንኳ እራሳቸውን መከላከል አልቻሉም፡፡

ውድ እህት ወንድሞቼ ስለቻይና ተውትና በቤታችን ፣ በንግዳችን ፣ በስራ ቦታችን ፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ትንሻን ቻይና የሆን ሰዎች ከዚህ ማስጠንቀቂያ መማርና ወደ አሏህ መመለስ አለብን፡፡

መልዕክቱን ከወደዱት ቢያንስ ለሶስት ሰው ሼር አድርጉት| Share

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

አጋጣሚዎች

ጥያቄና መልስ፡ የወረርሽኝ በሽታ

‹‹ወረርሽኝ በስብከቶች ውስጥ›› የሚለው ትምህርት ፈተና 13 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 10 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 13

1 የሙስሊም ሰው እምነቱ ከሌሎቹ የተለየ በመሆኑ ወረርሽኝን እና መከራን የሚጋፈጥበት መንገድ የተለየ ነው።

2 / 13

2 ‹‹ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይዋደቁም ኖሯል፤ ግን ልቦቻቸው ደረቁ።›› (ሱረቱ አንዐም 43) ከዚህ አያ (አንቀፅ) የምንረዳው

3 / 13

3 በአሏህ ላይ ስለ መመካት እውነታው

4 / 13

4 መከራ ከአሏህ ፍርድ አንድ _____ ነው።

5 / 13

5 ወረርሽኝ በተስፋፋ ጊዜ ሙስሊም ሰው ምን ያደርጋል

6 / 13

6 ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹አሏህ ለባሮቹ ርህሩህ (አዛኝ) ነው።›› (ሱረቱ አሹራ 19) በመከራ እና በችግር ጊዜ አሏህ ለባሮቹ አዛኝ ርህሩህ የመሆኑ ማሳያ የትኞቹ ናቸው

7 / 13

7 ከቁርአን እውነታዎች ውስጥ መከራ እና ችግር በሃጢያት ብዛት ይከሰታል የሚለው ነው።

8 / 13

8 እውነት ወይም ሐሰት፡ ቫይረሶች አሏህ ባሮቹን የሚያስፈራራበት አለማቀፋዊ ምልክቶች ናቸው።

9 / 13

9 እውነት ወይም ሐሰት፡ ሃያሉ አሏህ ወረርሽኝ እና መከራን ወደ ሰዎች አይልክም ሊቀጣቸው ቢሆን እንጅ።

10 / 13

10 እውነት ወይም ሐሰት፡ አሏህን መፍራት ኢባዳ ነው።

11 / 13

11 እውነት ወይም ሐሰት፡ ፍፁም በአሏህ ላይ የመመካት አካል የሆነው ለወረርሽኝ እና ለበሽታ ክትባት እና መድሃኒት አለመውሰድ ነው።

12 / 13

12 ወረርሽኝ በሚስፋፋ ጊዜ የሚሰጡ ትምህርት እና ስብከቶች ______ ነው።

13 / 13

13 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ብዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸው ሁለት በረካዎች አሉ።›› እነዚህ በሐዲስ ውስጥ የተጠቀሱት ምንድን ናቸው።

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »

Share