አደብ | ኢስላማዊ ባህሪ |
አቂዳ | እምነት |
አድል | ፍትህ/መልካም ባህሪ |
አህካም | ህግ/ትዕዛዝ የኢስላምን ህግ መሠረት በማድረግ 5 ትዕዛዞች አሉ 1) ዋጅብግዴታ 2) ሙስተሃብየተወደደ 3) ሐራምየተከለከለ 4) መክሩህየተጠላ 5) ሀላል__የተፈቀደ/ህጋዊ |
አሂራ | መጭው አለም |
ቢድአ | ከቁርአን ፣ ከሐዲስ እና ከሸሪአ መሠረት የሌለው እንዲሁም በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እና በነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ዘመን ያልነበረ ማንኛውም የኢባዳ ተብየ አይነቶችን ከራሳችን ስሜትና ፍልስፍና በመነሳት በዲነል ኢስላም ላይ ያልነበሩ ነገሮችን መጨመር ወይም መቀነስ ነው። |
ዶኢፍ | ደካማ የአንድ ሐዲስ የተላለፈበትን ሰንሰለት እና በእምነቱና በተግባሩ ሙሉ ስምምነት የሌለው ሐዲስ መገለጫ ነው። |
ፊትና | ፈተና |
ፊጥራ | ተፈጥሯዊ/ተፈጥሮ/የተፈጥሮ |
ሐዲያ | ስጦታ |
ሀጅ | አንዱ የእስልምና ምሰሶ ነው። |
ሐሰድ | ምቀኝነት |
ሐያእ | ይሉኝታ |
ሂጅራ | ስደት |
ሂክማ | ጥበብ |
ሁክም/አህካም | ድንጋጌ/ፍርድ |
ኢባዳ | አሏህን የመገዛት ተግባር/የአምልኮት ተግባር የኢባዳ (የአምልኮት ተግባር) ሁለት ሁኔታዎች አሉት 1) ለአሏህ ቅን መሆን 2) ለአሏህ መልእክተኛ መታዘዝ(ሱናውን መከተል) ከኢባዳዎች መካከል ሶላት ፣ ዘካት ፣ ፆም ወ.ዘ.ተ የአሏህ ፍራቻ በልብ ውስጥ መኖር እርዳታውንና ምህረቱን መሻት |
ኢህሳን | የአንድ ኢባዳ (ስራ) ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ አንድን ኢባዳ ስትሰራ ወይም አሏህን ስትገዛ አሏህን እንደምታየው ሁነህ መገዛት ይህን ማድረግ ከቻልክ አሏህ እንደሚያይህ ሆነህ መገዛት ወይም መስራት ማለት ነው። |
ኢጅቲሃድ | የሙስሊም ሊቃውንቶች መንፈሳዊ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ የሚያደርጉት አእምሯዊ ጥረት |
ኢኽላስ | ጥርት ያለ ቅንነት |
ኢልም | እውቀት |
ኢሻራት | የመጨረሻው ቀን ምልክቶች |
ጃሚእ | ሰፋ ያለና ሁሉን አቀፍ የሐዲስ ማጣቀሻ መፅሐፍ |
ጂሃድ | በአሏህ (ሱ.ወ) መንገድ ጥረት ወይም ትግል ማድረግ |
ከራም | ለጋስነት/ቸርነት |
ኪበር/ኪብር | የተሳሳተ(የውሸት) ኩራት |
ኪታብ | መፅሐፍ |
ሁጥባ | ስብከት |
ኩፍር | የአሏህን አምላክነት መካድ |
ሙጃሂድ | በአሏህ መንገድ ጥረት ወይም ትግል የሚያደርግ |
መውዱእ | የተፈበረከ በተለይ ለሐዲስ |
ሙተፈቁን አለይህ | ስምምነት የተደረሰበት/በቡሐሪይ እና በሙስሊም የተላለፈ ማንኛውም ሐዲስ |
ሙወጢር | ቀጣይነት ያለው/በተለያየ ጊዜ በብዙ ሰዎች የተዘገበ ሐዲስ |
ቀደር | መጥፎም ሆነ ጥሩ የሚከሰተው አሏህ የደነገገው ነው ብሎ ማመን |
ረህማ | ምህረት/እዝነት |
ሪፋቅ | መልካምነት/ደግነት |
ሶብር | ራስን መቆጣጠር/ታጋሽነት |
ሶሂህ | ትክክለኛና ምንም እንከን ወይም ደካማ ላልሆነ ሐዲስ የተሰጠ ስም ነው |
ሰውም | ፆም |
ሸሂድ | ራሱን በአሏህ መንገድ የሰዋ |
ሽርክ | ለአሏህ አጋር ወይም ባላንጣን ማበጀት/ማጋራት ሽርክ(ማጋራት) ሶስት ክፍሎች አሉት 1) አሽርኩል አክበርትልቁ ማጋራት 2) አሽርኩል አስገርትንሹ ማጋራት 3) አሽርኩል ኸፊይ__ድብቁ ማጋራት |
ሽርኩል አክበር | ከአሏህ ውጭ ባለ ነገር ላይ ማመን(ማምለክ) አሏህ በሽርክ ላይ የሞተን ሰው አይምርም መልካም ስራውንም አይቀበለውም እናም ከኢስላም ውጭ ይሆናል |
ሽርኩል አስገር | ትንሹ ማጋራት አሏህን ለማስደሰት ተብሎ ሳይሆን ዝናን ክብርን እና ምስጋናን ከሰዎች ዘንድ ለማግኘት ተብሎ የሚሰራ የአምልኮት ተግባር ነው። የዚህ አይነቱ ማጋራት አንድን ሰው ከኢስላም ውጭ አያደርገውም |
ሽርኩልኸፊይ | ይህ ማጋራት አሏህ በደነገጋቸው ሁኔታዎች ላይ አለመርካት ወይም ቅርመሰኘት ነው። |
መረጃ እና አስፈላጊነቱ
መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ