ሲራጥ | ማለት በመሠረቱ መንገድ ማለት ሲሆን ሰዎች በፍርዱ ቀን የሚያልፉበት በጀሃነም እሳት አግድም የሚቀመጥ ድልድይ ማለት ነው። ይህም እንደጐራዴ የሰላ እና ከፀጉር በላይም የቀጠነ መሆኑ ተገልፃል። |
ሱፍህ | በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መስጅድ ውስጥ የተመሠረተ የመጀመሪያው ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ |
ጣጉኡት | ከአሏህ ውጭ ያለ ማንኛውም የሚመለክ ነገር ሁሉ ጣጉኡት(ጣኦት) ነው |
ተስፊያህ | ማፅዳት |
ተውሂድ | አሏህ በራሱ የገለፃቸውን ባህሪያቶቹን እና ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የገለፇቸውን የአሏህ ባህሪያቶች ማረጋገጥና አሏህ ሊመለክ የሚገባው ብቸኛ አምላክ መሆኑን ማወጅ ማለት ነው። ተውሂድ ሶስት ክፍሎች አሉት 1) ተውሂድ አሩቡብያህ 2) ተውሂዱ አል-ኡሉሂያ 3) ተውሂድ አል-አስማኡ ወሲፋት |
ተቅሊድ | ጭፍን እምነት/በጭፍን መከተል |
ተዋዱእ | ራስን ዝቅ ማድረግ/መተናነስ |
ተወኩል | በአሏህ መመካት/መወከል |
ኡለማ | አሊም |
ኡለማህ | አሊሞች |
ኡማ | ሙስሊም ማህበረሰብ |
ዘካህ | አንዱ የኢስላም ምሰሶ ሲሆን ፍቹም ለድሆች ምፅዋት መስጠት ማለት ነው |
ሪባ | አራጣ/ወለድ |
አጅር | ምንዳ/ሽልማት |
አሰላሙ አለይኩም | ሙስሊሞች እርስ በርሳቸው ሲገናኙ የሚለዋወጡት ሰላምታ ሲሆን ትርጉሙም «ሰላም ባንተ ላይ ይሁን» ማለት ነው። |
አሲዲቅ | እውነተኛ/ሃቀኛው ይህ መጠሪያ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ለአቡበክር የተሰጡት ነው። |
አሹራ | የሙሐረም ወር አስረኛ ቀን ነው። ይህ ቀን አሏህ ሙሳንና የኢስራኤል ልጆችን ከፊርአውን የጠበቀበት ቀን ነው። |
አኡዙ ቢላሂ ሚነሸይጧኒ ረጂም | አንድ ሙስሊም ቁርአን ከማንበብ በፊት ፣ ከመናገሩ ፣ ዱአ ከማድረጉ በፊት ፣ ወደ መፅዳጃ ቤት ከመግባቱ በፊት እና ማንኛውንም ነገር ከማከናወኑ በፊት የሚለው አረፍተ ነገር ሲሆን ትርጉሙም «ከተረገመው ሸይጧን በአሏህ እጠበቃለሁ» ማለት ነው። |
አውልያ | ጓደኛ/ረዳት/ደጋፊ |
አውራህ | ሐፍረተ ገላ |
አያህ | ታአምር/ምልክት |
አያት | ታአምራት |
አያቱል ኩርሲይ | ሱራ አል-በቀራ አያህ 256 አያቱል ኩርሲይ ተብሎ ይጠራል |
አዝዋጅ | ጥንዶች(ባልና ሚስት) |
ባበልሪያን | አንደኛው የጀነት መግቢያ በር ስም ነው። |
በድር | በሙስሊሞችና በአሏህ ጠላቶች መካከል የተካሄደ የመጀመሪያው ሙሉ ወታደራዊ ዘመቻ(ጦርነት) ነው። ይህ ጦርነት የተካሄደው በሁለተኛው ዓመተ ሂጅራ በሙስሊሞችና በመካ ቁረይሾች መካከል ነበር። በድር የምትገኘው ከሚዲነቱል ሙነወራ በስተደቡብ 150 ርቃ ነው። የሙስሊም ወታደሮች ቁጥር 313 ሲሆን የቁረይሽ ወታደሮች ደግሞ 1000 ነበሩ። |
በይቱሏህ | የአሏህ ቤት |
በይቱል ሃምድ | የምስጋና ቤት |
በካ | የመካ ሌላኛ መጠሪያ ስም ነው። |
በኒ ኢስራኢል | የእስራኤል ጐሳ |
ባረከ ሏህ | የአሏህ በረካ ባንተ ላይ ይሁን አንድ ሙስሊም አንድን ሰው ሲያመሰግንና ውለታን ሲመልስ ይህን አባባል ይጠቀማል። ሰው የውየውም «ባረከ ሏህ ፊኩም» ብሎ ይመልስለታል። |
በርዘህ | በምድር ህይወትና በአሂራ ሂወት መካከል ያለ ክፍል |
ባቲጢል | ውሸት/ውሸታም |
ቢንት | ሴት ልጅ |
ቢስሚላህ | በአሏህ ስም |
ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም | በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። |
ቡህታን | ሃሜት |
ቡራቅ | ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ወደ ሚእራጅ የተጓዙበት እንሰሳ |
መረጃ እና አስፈላጊነቱ
መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ