የሐዲስ ማስታወሻ 1

ጥራዝ 1, መጽሐፍ 1 የሐዲስ ቁጥር 1 እና መጽሐፍ 2,ቀጥር 51

ኡመር ኢብኑ አል-ኸጧብ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ: የስራዎች ምንዳ በኒያ ይወሰናል። እያንዳንዱም ሰው ባሰበው ነገር ይመነዳል። እናም ለዓለማዊ ጥቅም ወይም ሴት ለማግባት ብሎ የተሰደደ ስደቱ ለተሰደደበት ነገር ነው» ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ።

ጥራዝ 1,መጽሐፍ 2,ቁጥር 7

ኢብኑ ኡመር እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ: ኢስላም በሚከተሉት አምስት መርሆዎች መሠረት ነው ብለዋል፡

  • ከአሏህ ውጭ ሊመለክ የሚገባው ነገር አለመኖሩንና ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር
  • ሶላት መስገድ
  • ዘካ መስጠት
  • ሐጅ ማድረግ
  • የረመዷንን ወር መፆም

ጥራዝ 1, መፅሐፍ 2, የሐዲስ ቁጥር 8

አቡሑረይራ እንደተረከው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ): «ኢማን ከ60 ቅርንጫፎች በላይ አሉት። ይሉኝታም አንዱ የኢማን ክፍል ነው» ብለዋል።

ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 9

አብዱሏህ ቢን አምር እንደተረከውነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: «ሙስሊም ማለት ሙስሊሞችን በምላሱና በእጁ የማይጎዳ የሆነ ነው። ስደተኛ ማለት ደግሞ አሏህ ከከለከለው ነገር የተከለከለ ነው» ብለዋል።

ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር

አቡ ሙሳ እንደተረከው የተወሰኑ ሰዎች የአሏህ መልእክተኛን እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው:- የማን ኢስላም ነው ከሁሉም በላጩ? (i.e ያም ማለት በጣም ጥሩ የሆነው ሙስሊም ማነው?) እሳቸውም ሙስሊሞችን በምላሱና በእጁ ከመጉዳት የራቀ (ያስወገደ) ነው ሲሉ መለሱ።

ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 12

አነስ እንደተረከው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:- አንዳችሁም አላመናችሁም ከናንተ መካከል ለራሱ የወደደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ።

ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቁጥር 13

አቡሑረይራ እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል: ሂወቴ በእጁ በሆነችው አንዳችሁም እምነት የላችሁም (አላመናችሁም) ከናንተ መካከል ከአባቱና ከልጁ አብልጦ እስካል ወደደኝ ድረስ።

ጥራዝ 1, መጽሐፍ 2, የሐ.ቀጥር 15

አነስ እንደተረከው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: የሚከተሉት ባህሪያት ያሉት የእምነት ጥፍጥና ይኖረዋል ብለዋል

1) አሏህና መልእክተኛው ከማነኛውም ነገር በላይ ውድ የሆኑለት

2) ሰውን የሚወድና ውዴታውም ለአሏህ ብሎ የሆነ

3) ወደ ጀሃነም እሳት መወርወርን እንደሚጠላ ሁሉ መጥመምን (መክፈርን) የሚጠላ የሆነ

ጥራዝ 1 መጽሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 169

አኢሻ (ረ.ዐ) እንደተረከችው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጫማ ሲለብሱ ፣ ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ ፣ ሲያፀዱ ወይም ሲታጠብና ማንኛውንም ነገር ሲያደርጉ በቀኝ ጎናቸው መጀመር ይወዱ ነበር።

ሰሒህ አል-ቡሐሪ የሐ.ቁጥር 527

ኢብን ኡመር (ረ.ዐ) እንደተረከው የአሏህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ): “የአስር ሶላትን ሆንብሎ (አውቆ) ያመለጠው ሰው ቤተሰቡንና ንብረቱን እንዳጣ ሰው ነው።” ብለዋል።

ኢማሙ አህመድ ኢብን ሐምበል ጥራዝ የሐ.ቁጥር አቡቀትዳህ (ረ.ዐ) እንደተረከው ነብዩ እንድህ ብለዋል “ክፉ ሌባ ከሶላቱ የሚሰርቅ ነው። ያረሱ ሉሏህ! የሶላት ሌባ ማነው? ሲሉ በትህትና ጠየቋቸው። ሩኩኡን ወይም ሱጁዱን በትክክል የማያከናውን ነው።” ሲሉ መለሱ።

ሰኺህ አል-ቡኻሪ የሐ.ቁጥር 527

ኢብን ኡመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ): የአስር ሶላት ሆንብሎ (አውቆ) ያመለጠው ሰው ልክ ቤተሰቡንና ሃብት ንብረቱን እንዳጣ ሰው ነው ብለዋል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 169

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ): ጫማ ሲለብሱ ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ ሲያፅዳዱ ወይም ሲታጠቡና ማንኛውንም ነገር ሲያደርጉ በቀኝ ጎናቸው መጀመር ይወዱ ነበር።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 170

አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) አይቻቸዋለሁ የአሰስር ሶላት በደረሰ ጊዜ ሰዎች ውዱዕ ለማድረግ ውሃ ፈለጉ ነገርግን ማግኘት አልቻሉም። ብኋላ ላይ የውዱዕ ውሃ ለአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጣላቸው፤ እጃቸውንም ማሰሮው ውስጥ አስገቡትና ሰዎች ከርሷም ውዱዕ እንዲያደርጉ አዘዙ። ሁሉም ውዱዕ እስኪያከናውኑ ድረስ ከጣታቸው ስር ውሃ ሲፈልቅ አይቻለሁ።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top