ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 172
አነስ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን በተላጩ ጊዜ የተወሰነ ፀጉራቸውን ቀድሞ በመጀመሪያ የወሰደው አቡ ጦልሃ ነበር።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 177
አባስ ቢን ተሚም እንዳስተላለፈው አጎቴ የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ሶላቱን ትቶ መሄድ የለበትም ድምፅ እስካልሰማ ወይም የሆነ ነገር እስካልሸተተው ድረስ ብለዋል ብሏል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 207
ጃዕፈር ቢን ኡመያ እንዳስተላለፈው አባቴ እንዲህ ብሏል የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከትከሻው አካባቢ የሆነ የበሰለ የበግ ስጋ ሲበሉና ለሶላት ሲጠሩ ቢለዋቸውንም አስቀምጠውና ውዱዕ ደግመው ሳያደርጉ ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ ብሏል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 209
መይሙና(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከትከሻው አካባቢ የሆነ የበግ ስጋ በሉና ውዱ ደግመው ሳደርጉ ሰገዱ።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 211
አኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ከእናነተ መካከል አንዳችሁ እየሰገደ የመጫጫን ስሜት ከተሰማው የመጫጫኑ ስሜት እስኪያበቃለት ወደ አልጋው ይሂድ(ይተኛ)። ምክኒያቱም እንቅልፍ ተጫጭኖት እያለ የሚሰግድ ሰው ለራሱ ምህረትን ወይም መጥፎ ነገር እየለመነ እንደሆነ አያውቅምና ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 212
አነስ እንዳስተላለፈው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ከናንተ መካከል አንዳችሁ እየሰገደ የመጫጫን ስሜት ከተሰማው የሚናገረውን(የሚቀራውን) ነገር እስኪረዳ ድረስ ይተኛ ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 216
አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ለተፈጥሮ ጥሪ መልስ ሊሰጡ(ሊፅዳዱ) በሄዱ ጊዜ ብልታቸውን የሚያፀዱበት ውሃ አመጣላቸው ነበር።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 218-219
አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው አንድ የአረብ ዘላን መስጅድ ውስጥ ሲሸና ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አዩትና ሰዎች እንዳይረብሹት (እንዳያቇርጡት) ነገሯቸው። በጨረሰ ጊዜ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ውሃ እንዲያመጡላቸው ጠየቁና ከሽንቱ ላይ አፈሰሱበት።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 228
አኢሻ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ፋጢማ ቢንት አቢ ኹበይሽ ወደ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) መጣችና እንዲህ አለች የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ቀጣይነት ያለው(ያልተቇረጠ) ደም ከማህፀኔ ይፈሰኛልና አልነፃ አልኩ ሶላቶቼን መተው አለብኝን? አለቻቸው። የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) አይሆንም(ልትተይ) አይገባም። ምክኒያቱም ከደም ቧንቧሽ እንጅ ሃይድ አይደለም። የወር አበባሽ ሲመጣብሽ ሶላትሽን ተይ እናም ሲጨርስ ደሙን ታጥበሽ ሶላትሽን ስገጅ አሏት።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 237
መይሙና እንዳስተላለፈችው አይጥ ያረፈችበትን(የወደቀችበትን) ቅቤ በተመለከተ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ተጠይቀው አይጧንና በዙርያዋ ያለውን ቅቤ ጥላችሁ የቀረውን ተጠቀሙ ብለዋል።
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ማንኛውም ልጅ የሚወለደው ንፁህ ከሆነ የተፈጥሮ ባህሪ ጋር ነው። ወላጆቹ አይሁዳ ፣ ክርስቲያን ፣ ማዝዲስት እንዲሆን ሊቀይርት ይችላሉ ብለዋል።
ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 238
አቡ ኹረይራ እንዳስተላለፈው ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) በአሏህ መንገድ የቆሰለ ሙስሊም በግጭት ጊዜ ጉዳት እንደደረሰበት ሆኖ በዕለተ ትንሳኤ ይቀሰቀሳል፤ ደሙም ከቁስሉ ይፈሳል፤ ቀለሙም የደም ቀለም ይሆናል። ነገርግን ልክ እንደ ሚስክ ይሸታል ብለዋል።