የሐዲስ ማስታወሻ 4

ሰኺህ አል-ቡኻሪ የሐ.ቁጥር 527

ኢብን ኡመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) : የአስር ሶላት ሆንብሎ (አውቆ) ያመለጠው ሰው ልክ ቤተሰቡንና ሃብት ንብረቱን እንዳጣ ሰው ነው ብለዋል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 169

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፡ ጫማ ሲለብሱ ፀጉራቸውን ሲያበጥሩ ሲያፅዳዱ ወይም ሲታጠቡና ማንኛውንም ነገር ሲያደርጉ በቀኝ ጎናቸው መጀመር ይወዱ ነበር።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 170

አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ) አይቻቸዋለሁ የአሰስር ሶላት በደረሰ ጊዜ ሰዎች ውዱዕ ለማድረግ ውሃ ፈለጉ ነገርግን ማግኘት አልቻሉም። የውዱዕ ውሃ ለአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) መጣላቸው፤ እጃቸውንም ማሰሮው ውስጥ አስገቡትና ሰዎች ከርሷም ውዱዕ እንዲያደርጉ አዘዙ። ሁሉም ውዱዕ እስኪያከናውኑ ድረስ ከጣታቸው ስር ውሃ ሲፈልቅ አይቻለሁ።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 172

አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን በተላጩ ጊዜ የተወሰነ ፀጉራቸውን ቀድሞ በመጀመሪያ የወሰደው አቡ ጦልሃ ነበር።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 177

አባስ ቢን ተሚም እንዳስተላለፈው አጎቴ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሰው ሶላቱን ትቶ መሄድ የለበትም ድምፅ እስካልሰማ ወይም የሆነ ነገር እስካልሸተተው ድረስ ብለዋል ብሏል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 207

ጃዕፈር ቢን ኡመያ እንዳስተላለፈው አባቴ እንዲህ ብሏል የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከትከሻው አካባቢ የሆነ የበሰለ የበግ ስጋ ሲበሉና ለሶላት ሲጠሩ ቢለዋቸውንም አስቀምጠውና ውዱዕ ደግመው ሳያደርጉ ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ ብሏል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 209

መይሙና (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከትከሻው አካባቢ የሆነ የበግ ስጋ በሉና ውዱ ደግመው ሳደርጉ ሰገዱ።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 211

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከእናነተ መካከል አንዳችሁ እየሰገደ የመጫጫን ስሜት ከተሰማው የመጫጫኑ ስሜት እስኪያበቃለት ወደ አልጋው ይሂድ (ይተኛ)። ምክኒያቱም እንቅልፍ ተጫጭኖት እያለ የሚሰግድ ሰው ለራሱ ምህረትን ወይም መጥፎ ነገር እየለመነ እንደሆነ አያውቅምና ብለዋል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 212

አነስ እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከናንተ መካከል አንዳችሁ እየሰገደ የመጫጫን ስሜት ከተሰማው የሚናገረውን (የሚቀራውን) ነገር እስኪረዳ ድረስ ይተኛ ብለዋል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 216

አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለተፈጥሮ ጥሪ መልስ ሊሰጡ (ሊፅዳዱ) በሄዱ ጊዜ ብልታቸውን የሚያፀዱበት ውሃ አመጣላቸው ነበር።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 218-219

አነስ ቢን ማሊክ እንዳስተላለፈው አንድ የአረብ ዘላን መስጅድ ውስጥ ሲሸና ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አዩትና ሰዎች እንዳይረብሹት (እንዳያቇርጡት) ነገሯቸው። በጨረሰ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ውሃ እንዲያመጡላቸው ጠየቁና ከሽንቱ ላይ አፈሰሱበት።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top