የሐዲስ ማስታወሻ 5

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 228

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ፋጢማ ቢንት አቢ ኹበይሽ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣችና እንዲህ አለች የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ቀጣይነት ያለው(ያልተቇረጠ) ደም ከማህፀኔ ይፈሰኛልና አልነፃ አልኩ ሶላቶቼን መተው አለብኝን? አለቻቸው። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አይሆንም(ልትተይ) አይገባም። ምክኒያቱም ከደም ቧንቧሽ እንጅ ሃይድ አይደለም። የወር አበባሽ ሲመጣብሽ ሶላትሽን ተይ እናም ሲጨርስ ደሙን ታጥበሽ ሶላትሽን ስገጅ አሏት።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 237

መይሙና እንዳስተላለፈችው አይጥ ያረፈችበትን (የወደቀችበትን) ቅቤ በተመለከተ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተጠይቀው አይጧንና በዙርያዋ ያለውን ቅቤ ጥላችሁ የቀረውን ተጠቀሙ ብለዋል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ማንኛውም ልጅ የሚወለደው ንፁህ ከሆነ የተፈጥሮ ባህሪ ጋር ነው። ወላጆቹ አይሁዳ ፣ ክርስቲያን ፣ ማዝዲስት እንዲሆን ሊቀይርት ይችላሉ ብለዋል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 238

አቡ ኹረይራ እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአሏህ መንገድ የቆሰለ ሙስሊም በግጭት ጊዜ ጉዳት እንደደረሰበት ሆኖ በዕለተ ትንሳኤ ይቀሰቀሳል፤ ደሙም ከቁስሉ ይፈሳል፤ ቀለሙም የደም ቀለም ይሆናል። ነገርግን ልክ እንደ ሚስክ ይሸታል ብለዋል።

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 241

አብዱሏህ ቢን መስዑድ እንዳስተላለፈው አንዴ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ካዕባ ውስጥ ሶላት እየሰገዱ እያለ አቡ-ጀህል ከባልደረባዎቹ ጋር ተቀምጦ ነበር። ከመካከላቸው አንደኛው ለሌሎቹ ከናንተ መካከል ማነው የግመል ፈርስ የሚያመጣና ሙሐመድ ሱጁድ ባደረገ ጊዜ ከጀርባው ላይ የሚደፋበት አለ። ከእነሱም መካከል እድለቢስ የሆነው ተነሳና ይዞ መጣ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱጁድ እስኪያደርጉ ድረስ ጠበቀና በትከሻዎቻቸው መካከል ደፋባቸው። እየተመለከትኩ ነበር ሆኖም ግን ምንም ነገር ማድረግ አልቻልኩም። ከኔጋ ሰዎች ቢኖሩና ብቇቇማቸው ተመኘሁ። እርስ በእርሳቸውም ላይ እየወደቁ መሳለቅ ጀመሩ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሱጁድ እያደረጉ ነበርና ፋጢማ (ረ.ዐ) መጥታ ፈርሱን ከጀርባቸው አንስታ እስክትጥለው ድረስ እራሳቸውን አላነሱም ነበር። እራሳቸውን ቀና አደረጉና ሶስቴ አሏህ ሆይ! ቁረይሽን ቅጣ አሉ። እናም ለአቡ-ጀህል እና ለአጋሮቹ ፈታኝ ነበር። ነቡዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሏህን በነሱ ላይ በለመኑ ጊዜ በዚህ ከተማ መካ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት እና ዱአ ተቀባይነት እንደሚያገኝ የፀና እምነት ስለነበራቸው ፈሩ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሏህ ሆይ! አቡጀህልን ፣ ኡትባ ቢን ራቢያ ፣ ሸይባ ቢን ራቢያ ፣ አልወሊድ ቢን ኡትባ ፣ ኡመያ ቢን ኸለፍ እና ኡቅባ አል-ሙይጥ እና ሌሎች ስማቸውን የማላስታውሳቸው ጨምሮ ነፍሴ በእጁ በሆነችው በአሏህ ይሁንብኝ! በአሏህ መልዕክተኛ ሲቆጠሩ የነበሩ ሰዎችን አስክሬን በቀሊብ አይቻለሁ(i.e ቃሊብ ከበድር ግድግዳዎች አንዱ ነው።)

ጥራዝ 1 መፅሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 243

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስካር የሚፈጥሩ መጠጦች ሁሉ ሐራም ናቸው ብለዋል።

ጥራዝ 1 መጽሐፍ 4 የሐ.ቁጥር 246

ኹዘይፋ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሌሊት በተነሱ ጊዜ አፋቸውን በሲዋክ ያፀዱ ነበር።

ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 255

ኢብን አብዱሏህ እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸው ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ያፈረሱ ነበር።

ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 262

አኢሻ (ረ.ዐ) እናዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ የጀናባ ትጥበት ባደረጉ ጊዜ እጃቸውን መጀመሪያ ይታጠቡ ነበር።

ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 284

አቡ ሰላማ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጁኑብ ሆነው እያለ ይተኛሉ? ስል አኢሻን ጠየኳት። አዎ! ነገርግን ወደ አልጋ ከመሄዳቸው በፊት ውዱዕ ያደርጋሉ ስትል መለሰችልኝ።

ጥራዝ 1 መጽሐፍ 5 የሐ.ቁጥር 285

ኡመር ቢን አል-ኸጧብ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ ከኛ መካከል አንዱ ጁኑብ ሆኖ ያለ መተኛት ይችላን? ስል ጠየኳቸው። ውዱእ ካደረገ አዎ! ጁኑብ እንኳ ቢሆን መተኛት ይችላል ሲሉ መለሱልኝ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል አንድን ሰው መልካም እንዲሰራ ያመላከተ ሰው መልካም እንደሰራው ሰው ተመሳሳይ ምንዳ ያገኛል ብለዋል።

በቡኻሪ እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው ብለዋል።

ሰሂህ አል-ቡኻሪ የሐ.ቁጥር 667

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሏህ ሰዎችን በሃይማኖታቸው ጉዳይ የሚጠቅምበት የሆነን እውቀት የሸሸገ (የደበቀ) ሰው በዕለተ ትንሳኤ አሏህ ከጀሃነም እሳት በሆነ ልጓም ይለጉመዋል ብለዋል።

ኢብን መስኡድ እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ መስመር አሰመሩና ይህ የአሏህ መንገድ ነው አሉ። እናም በግራና በቀኝ ሌሎች መስመሮችን ቅርንጫፍ አውጥተው አሰመሩና እነዚህ በመጨረሻው ሸይጧን ህዝቦችን የሚጣራባቸው መንገዶች ናቸው አሉ።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top