ኡስማን ኢብን አፋን

ኡስማን ኢብን አፋን (   ) ሶስተኛው ኸሊፋ ነው። የተወለደው ነብዩ ሙሐመድ (   ) ከተወለዱ ከሰባት አመት በኋላ ነው። በጣም የተማረ እና መካ ውስጥ አሉ ከሚባሉ ሃብታሞች አንዱ ነው።

እስልምናን በተቀበለ ጊዜ አጎቱ ለከፋ ግርፋት ዳርጎታል። እስልምናን እንዳይቀበልም ትልቅ ግፊት አድርጎበት ነበር። ነገርግን ኡስማን (   ) በአላማው ፀና።

ኡስማን ( ) ዙል ኑረይን (የሁለት ብርሃን ባለቤት) ተብሎ ይታወቃል። ምክኒያቱም ኡስማን ኢብን አፋን ( ) ሁለቱን የነብዩ ( ) ልጆች ማለትም ሩቅያ እና እሷ ስትሞት ደግሞ ኡሙ ኩልሱምን አግብቶ የነበረ በመሆኑ ነው።

እንዲሁም ኡስማን ( ) ስስት የለሽ በሆነው ልግስናው በደንብ ይታወቃል። የተቸገሩትን ያለቁጥር የረዳ፤ ትልቁን የሃብቱን ክፍል ለሙስሊሞች ደህንነት ያዋለ ነው።

በተቡክ ዘመቻ ወቅት ድሃ ወታደሮችን ለመርዳት ነብዩ( ) አስተዋፅኦ በጠየቁ ጊዜ ኡስማን ( ) ሶስት መቶ ግመሎች ከነ ስንቁ በመስጠት በጣም ትልቁን የአስተዋፅኦ ድርሻ ተወጥቷል።

በድጋሚ መዲና ውስጥ ያለውን መስጅድ ነብዩ ( ) ማስፋት በፈለጉ ጊዜ ኡስማን ( ) ለዚሁ አላማ የሚውል ተጨማሪ መሬት ገዝቷል። እንዲሁም በኸሊፋው አቡበክር ዘመን ሙስሊሞች በርሃብ በተጠቁ ጊዜ በሃያ አምስት ሽህ ዲርሃም እህል አስመጥቷል።

ያኔ በጣም ብዙ ገንዘብ ነበር። ለተቸገሩትም ተከፋፈለ። እነዚህ ኡስማን ( ) ለእስልምና እና ለሙስሊሞች ሲል ካደረገው ውስጥ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው።

ኡስማን ኢብን አፋን ( ) በትህትናው እና በቅድስናው በደንብ ይታወቃል። በአንድ ወቅት ነብዩ (  ) ለአኢሻ (  ) መልዕክቶች እንኳ ለኡስማን ሃያዕን ያሳያሉ ሲሉ ተናገረዋል።

ብዙ ጊዜ የሌሊቱን ክፍል በሶላት ያሳልፋሉ። እያንዳንዱን ሁለተኛውን ወይም ሶስተኛውን ቀን የይፆማሉ ፣ በየአመቱም ሐጅ ያደርጉነበር።

ሃብት ቢኖረውም እንኳ የሚኖረው ግን ቀለል ያለ ህይወት ነው። በህይወት እያሉ የጀነትን ብስራት ከተሰጣቸው አስር ሶሃባዎችም አንዱ ነው።

ኡስማን ኢብን አፋን አበርክቶ

በእሳቸው አስተዳደር ጊዜ የእስልምና ግዛት በምዕራብ እስከ ሞሮኮ ፣ በምስራቅ እስከ አፍጋኒስታን ፣ በሰሜን እስከ አርሜንያ እና አዘርባይጃን ይደርሳል። የባህር ሃይል ተቋቁሟል ፣ የግዛት የአስተዳደር ወሰን እንዳዲስ ተከልሷል…፣ ብዙ የህዝብ ፕሮጀክቶች ተሸሽለውና ተለጥጠው ተጠናቀዋል።

በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የተለያየ የቁርአን አነባበብ ዘየ ነበራቸው። ሆኖም ይህ የተለያየ የአነባበብ ዘየ ለእስልምና ጥሩ አለመሆኑን በመረዳት ሁሉም የቁርአን ቅጅዎች እንዲሰበሰቡ አድርጎ በመካ የአረብኛ ዘየ የተዘጋጀውን ትክክለኛውን ቅጅ ኮሚቴዎች እንዲያወጡ አድርጓል።

ትክክለኛውም ቅጅ የነብዩ (  ) ሚስት በሆነችው ሐፍሷ እንክብካቤ ስር እንዲሆን ተደርጓል። ከብዜ ጥንቃቄ የተሞላበት ፍተሻ ፣ ውይይት እና ጥረት ቡኋላ በትክክለኛው የመካ አረብኛ ዘየ የቁርአን ቅጅ እንዲዘጋጅ እና ሌሎች ከመደበኛው ዘየ ጋር የማይገጥሙ ቅጅዎች ወደ ፊት ውዝግብ (መደናገር) ለማስቀረት ሲባል ሁሉም ተቃጥለዋል።

የአብዱሏህ ኢብን ሳባ ተንኮል እና የኡስማን መገደል

ኡስማን (   ) የእስልምና ግዛት ለአስራ ሁለት አመታት አስተዳድረዋል። በመጀመሪያው ስድስት አመታት ሙስሊሞች ውስጣዊ ሰላም እና መረጋጋት የነበራቸው ቢሆንም በሁለተኛው የኸሊፋው አስተዳደር ዘመን በሰዎች መካከል ቅሬታ እየጨመረ መጣ።

እያደር ሁኔታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደረሰ። እስልምናን ከውስጥ በኩል ለማዳከም አንድ አብዱሏህ ኢብን ሳባ ተብሎ የሚጠራ የመናዊ አይሁድ ለዚህ መጥፎ አላማ ሲል እስልምናን ተቀበለ።

በማስከተልም በሙስሊሞች መካከል አለመስማማትን ለመፍጠር የተንኮል ዘመቻውን ጀመረ።

አይሁዳዎች እና መሰሎቻቸው በሰዎች መካከል ያለውን ቅሬታ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም በኡስማን (   ) ላይ አሴሩ። ኡስማን ኢብን አፋን (   ) አመፁን በእንጭጩ መቅጨት ይችል ነበር።

ነገርግን ርህሩህ በመሆኑ ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት እና ችግሩን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ወሰነ።  በእርግጥ የሙስሊሞች ደም ለማፍሰስ የመጀመሪያው መሆን አልፈለገም። አማፂያኖቹ ስልጣኑን በፈቃድ እንዲለቅ በፈለጉ ጊዜ ይህን አላደረገም።

ምክኒያቱም በአንድ ወቅት ነብዩ ሐመድ (   ) ኡስማን! ምናልባት አሏህ ልብስ ያለብስሃል፤ እናም ሰዎች እንድታወልቀው ከፈለጉ ለእነሱ ስትል አታውልቀው። ብለው የሰጡት ቃልኪዳን ላይ ወሰን ማለፍ አልፈለገም።

ከግዛቱ ከተለያየ ቦታ የተሰባሰቡ አማፂያን ወደ መዲና በቡድን በቡድን ሆነው ጎረፉ። ከረዥም ጊዜ ከበባና አፈና ቡኋላ ኡስማን ቁርአን እየቀራበት ወደ ነበረው ክፍል ዘለው በመግባት ገደሉት።

ኡስማን (  ) ከመገደሉ በፊት እያነበበ የነበረው የቁርአን አንቀፅ ልክ እናንተ ባመናችሁበት ነገር እነሱ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ። ነገርግን ከዞሩ እነሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው። በእነሱ ላይ አሏህ ይበቃሃል። እሱ ሁሉን ሰሚ ሁሉን አዋቂ ነው። (አል-ቁርአን 2፡137) የሚል ነበር።

ኡስማን ኢብን አፋን (   ) ወደ ፊት የሚገጥመውን መከራ በተመለከተ ነብዩ (   ) የተናገሩት ትንቢት ተፈፅሟል። ኢማሙ ሙስሊም እንደ ዘገበው ነብዩ (  ) የጀነት ብስራት በሰጡት ጊዜ ወደ ፊት የሚገጥመውን ፈተናም አብረው ነገረውት ነበር።

ኡስማን (  ) ብስራቱን በተቀበለ ጊዜ አሏህ ሆይ! ፅናትን ስጠኝ። እርዳታው የሚሻ አንድ አሏህ ብቻ ነው ሲሉ ዱአ አደረጉ። (ሙስሊም)

ኡስማን ኢብን አፋን (   ) የሞተው በዙሎሂጃ 18ዓ.ሂ ጁምአ ከሰአት በኋላ ሲሆን የሞተውም በሰማኒያ ሁለት አመቱ ነው።

አስሃቢ ፣ አል-መዲና እና ኹለፋኡ ራሽዱን ተመልከቱ

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top