ዩሱፍ (ዐ.ሰ)

ዩሱፍ ወይም ይወሴፍ(   ) የያዕቁብ(   ) ልጅ ሲሆኑ አስራ አንድ የአባት ልጅ ወንድሞች ነበሩት። በጣም ጥሩ እና መልከ መልካም ልጅ በመሆኑ የእቁብ(   ) በጣም አብዝተው ይወዱታል። በሚያሳዝን ሁኔታ አስራ አንድ ወንድሞቹ በእሱ ቀኑ። አስራ አንድ ከዋክብት ፣ ፀሐይ እና ጨረቃ፤ ለእኔ ሲሰግዱ ህልም አየሁ ብሎ ለአባቱ በነገረ ጊዜ በእሱ ላይ ያሴሩበታል ብሎ በማሰብ ለወንድሞችህ ይህን ህልም እንዳትናገር አለው።

በአንድ ወቅት ቅናታቸው ገፋፋቸውና እኛ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳልፋል ፍቀድልን እኛ ጋር አብረን እንውሰደው ሲሉ ከብዙ ማመንታት በኋላ አባታቸውን አሳምነው ይዘውት ሄዱ። ወስደውም ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወረወሩት።

ልብሳቸውን በበግ ደም ለውሰው ወደ አባታቸው በመውሰድ እያለቀሱ በተኩላው ተበላብን ሲሉ ሊያታልሉ ሞከሩ። ያዕቁብ(   ) ተወዳጅ ልጃቸው አሁንም በህሕወት ያለ መሆኑን ልባቸውን አሳመኑ። በደም የተጨማለቀውን ጨርቃቸውን እየዘረጉ እንዴት ያለ አዛኝ ተኩላ ነው! የተወዳጁን ልጄን ልብስ ሳይቀድ የበላው! አሉ። ጉዳያቸውን ለአሏህ ሰጡ፤ እርዳታውንም ለመኑ።

ዩሱፍ (ዐ.ሰ) መገኘት

ወደ ግብፅ የሚጓዙ መንገደኞች ውሃ ለመጠጣት የውሃ ጉድግዱ ያለበት ቦታ ላይ አረፉ። አንድ ሰው ባልዲውን ወደ ጉድጓዱ ለቀቀ፤ ዩሱፍ (    ) ባልዲው ውሃው ላይ ከመድረሱ በፊት ከባልዲው ላይ ወጡ። ሰውየው ባልተለመደ መልኩ የሚጎትተው ነገር ከበደው፤ ጓደኞቹ ተሯሩጠው አገዙት። ሲያወጡት መልከ መልካም ፣ ጤነኛ ልጅ ተቀምጧል።

ጉዳያቸው ገንዘብ ብቻ ነበርና ሊሸጡት እግሮቹን በሰንሰለት አስረው ወደ ግብፅ ወሰዱት፡። ግብፅ እንደደረሱ የባሪያ ገበያ ላይ አወጡት። ከመቶ የሚበልጡ ሰዎች ተሰባሰቡ።

ተመልካቹም ፣ ባለጠጋውም ፣ የማህበረሰቡ መሪዎች ተሰባስበዋል። ጨረታው ቀኑን ሙሉ ሲካሄድ ዋለ። በመጨረሻ አዚዝ የተባለ የግብፅ የፍርድቤት ሹመኛ ሁሉንም ተጫራቾች በመብለጥ ዩሱፍን ወደ ቤቱ ይዞ ሄደ።

የዙለይካ ፍቅር እና መዘዙ

የአዚዝ ሚስት ዙለይካ ከቀን ቀን ብታየው ፣ ከእሱ ጋር ብትቀመጥ ፣ ብታወራው ፣ ብታዳምጠው አይታው ሰምታው የማትጠግበው ሆነባት፤ በጊዜ ሂደት ፍቅሯ እሳት ሆነ። የመልከ መልካሙን ዩሱፍን ፍቅር መቋቋም አቃታት። በሃሳቧ ያኖረችው ዩሱፍ ብዙ ሌሊቶችን እንቅልፍ ነሳት። ወደደችው። ልታማልለው ሞከረች፤ ችክ ብሎ እምቢ አላት። በዚህም ምክኒያት ወደ እስርቤት ያወረደውን ታሪክ ፈጠረች።

ዩሱፍ ሊያገባኝ ፈልገ ስትል ለባሏ ስሞታ አቀረበች። እስርቤት ውስጥ እውነትን ያስተምር ነበር። በደግነቱም ይታወቃል። ዩሱፍ (  ) በእስርቤት ህይወታቸው ህልም የመፍታት ችሎታ ተሰጥቷቸው ነበር። በአንድ ወቅት ከእስርቤት ሰዎች ለአንዱ ህልሙን እንዲፈቱለት ይጠይቃቸዋል። ህልሙን ፈቱለት፤ ዩሱፍ (   ) እንዳሉትም ሆነ። ሰውየው ከእስር ተፈቶ ወጣ። የንጉሱ ሲኒ (ዋንጫ) ያዝ ሆነ።

የዩሱፍ (   ) ህልም የመፍታት ችሎታ

ከአመታት በኋላ ዩሱፍ እዛው እስርቤት ውስጥ ነው። የግብፅ ንጉስ በጣም የሚያስጨንቅ ህልም አየ። ከንጉሱ ምክርቤት ውስጥ ህልም ሊፈታ የሚችል አንድም ሰው ባለመኖሩ የተለያ ሰዎች ህልሙን እንዲፈቱለት ጠየቀ። ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ ቅዥት ነው አሉ። ንጉሱ ከበድ ያለ እራት በልቶ ነበር የተኛው ማለት ነው። ንጉሱ ማርጀት ጀመረ ህልሙ ራሱ ግራ ተጋባ ሲሉ ቀለዱ።

የንጉሱ ዋንጫ ያዥ ዩሱፍ ( ) እውነተኛ ሰው መሆናቸውን እና ህልም በመፍታት የተካነ መሆኑን ስለሚያውቅ ፈቃድ ወስዶ ዩሱፍ ( ) ሊጠይቃቸው ሄደ። የንጉሱ ዋንጫ ያዥ የዩሱፍን የህልም ፍች ለንጉሱ በነገረው ጊዜ በአካል ሊያያቸው ፈለገ።

ምክኒያቱም ዩሱፍ (   ) የተናገሩት ወደ ፊት የሚከሰተውን ድርቅና ረሃብ ብቻ ሳይሆን ድርቁን እና ረሃቡን ለመጋፈጥ መወሰድ ያለበትን እርምጃ ጭምር ነበር። ዩሱፍ (    ) ይህን አጋጣሚ ያ በእሳቸው ላይ የተነሳውን እና ወደ እስር ቤት የተወረወሩበትን አሳፋሪ የሆነ የሃሜት ወሬ ለማጥራት ተጠቀሙበት።

እናም ያሉት ሆነ። የንጉሱ ግምጃ ቤት ገንዘብ ያዥ እና ተቆጣጣሪ ሃላፊ ሆኖ በንጉሱ ተሸመ። ድርቁን ለመቋቋም ይቻል ዘንድ እርዳታውን ጠይቀው። ዩሱፍ( ) ጥያቄውን ተቀበለ።

ረሃቡ በመላ ሐገሪቱ ብቻ ሳይሆን ዩሱፍ ተወልዶ ባደገበት ሐገር ድረስ የሰፋ ነበር። የየሱፍ ዝግጅት የተሟላ ነው። ለመጠባበቂያ ያኖሩት የችግሩን ጥፋት ለመጋፈጥ በቂ ነበር። ዩሱፍና ወንድሞች ፊት ለፊት ተገጣጠሙ። ሞቷል ብለው ስላሰቡ አላወቁትም ነበር።

በኋላ ላይ ወንድማቸው ዩሱፍ (  ) እንደሆነ ሲረዱ በእሱ ላይ ባደረጉት ነገር አፈሩ። ምህረቱን (ይቅርታውን) ለመኑ፤ ይቅርታም አደረገላቸው። አባታቸው ያእቁብ (   ) የዩሱፍን በህይወት መኖር ባወቁ ጊዜ የአይን ብርሃናቸው ተመለሰላቸው።

ከዚያ ቡኋላ የዩሱፍ አባትና ወንድሞቹ ዩሱፍን ግብፅ ውስጥ አገኙት። ለረዥም ጊዜ ተለያይተው ከቆዩ በኋላ ደስ የሚል ጥምረት ፈጠሩ።

ታላቅ የአሏህ ነብይ እና ታዛዥ የአሏህ ባሪያ ዩሱፍ (    ) አሏህ በሳቸው ላይ ያደረገውን ችሮታ በማሰብ እንዲህ ሲሉ ፀለዩ፡ ጌታየ ሆይ! በእርግጥ ሃይልን ሰጠኸኝ፤ የህልሞችን ፍች አስተማተርከኝ። የሰማያት እና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በዱንያ እና በመጭው አለም ረዳቴ ነህ። ሙስሊም ሆኜ ግደለኝ። ከመልካሞቹም አስጠጋኝ። (አል-ቁርአን 12፡101)

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top