የቀን እና የሌሊት ጊዜያችነን እንዴት ማሳለፍ አለብን?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

ማንኛውም ሰው ህይወቱን በተለያየ መንገድ ያሳልፋል። ነገር ግን ወሳኙ ጥያቄ የህይወቱን ሃቅ የሞላ ወይም የፈፀመ ማነው? የሚለው ነው። እንስሳቶች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ እንዲሁ ያሳልፋሉ። ነገርግን ጊዜውን በጥበብ የተሰጠው የሰው ልጅ የተለያዩ ነገሮችን በመፈፀም ያሳልፋል።

ሆኖም ኩፋሮች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ ፅልመት በወረሰው ጠማማ መንገድ ላይ ሆነው ከቀጥተኛዋ የህይወት ጎዳና እንዳፈነገጡ ይንከራተታሉ። ነገርግን የህይወት መመሪያቸውን በአሏህ መለኮታዊ መመሪያ ላይ ያደረጉ አማኞች ደህንነቱ በተጠበቀ ፣ ሰላምና መረጋጋት በሰፈነበት የህይወት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። ከሃዲያኖች ቀንና ሌሊታቸውን የሚያሳልፉት በመንፈሳዊ ፅልመት ሲሆን ሙእሚኖች ግን የቀንና የሌሊት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በመንፈሳዊ ብርሃን ነው። ይህ ከሆነ አሁንም ሊነሳ የሚገባው ወሳኙ ጥያቄ ሙስሊሞች ከከሃዲያኖች ለመለየት እንዴት ነው የቀንና የሌሊት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ብሎ መጠየቁ አስፈላጊ ነው።

እኛ ሙስሊሞች ጊዜያችነን ከታች በተዘረዘረው መልኩ ማሳለፍ ይኖርብናል።

  1. ከማንኛውም የወንጀል አይነት በመቆጠብ

  2. ወንጀል ሲሰሩ ወዳው በመቶበት

  3. የአሏህን ሐቅ በመጠበቅ

  4. የወላጆቻችነንና በዙርያችን ያሉ ሰዎችን ሃቅ በመጠበቅ

  5. መጥፎ ንግግርን በማስወገድ

  6. ስምና ዝናን ባለመፈለግ

  7. ሰዎች የሰራነውን ስህተት ሲነግሩን እራሳችነን ትክክለኛ አድርገን ለማቅረብ ከመሞከር ይልቅ ስህተታችነን ተቀብለን ተውበት በማድረግ

  8. እንቶ ፈንቶ ወሬዎችን ባለማውራት

  9. ማንኛውንም አይነት ስራ ስንሰራ የሸሪአ ድንጋጌያቸውን በማስታወስ

  10. ማንኛውንም የኢባዳ አይነቶች ስንፈፅም ደከመኝ ሰለቸኝ ባለማለት

  11. ከሌሎች ሰዎች ጋር ስንገናኝ ወይም ስንወያይ እራሳችነን ዝቅ በማድረግ ወይም በመተናነስ ወይም ደግሞ እኔ እበልጣለሁ የሚል ስሜት በማስወገድ

  12. ከከሃዲያኖች በመራቅ

  13. የሰዎችን ስህተት ባለመፈለግና ለሰዎች መጥፎ ነገር ባለማሰብ

  14. የራሳችነን ስህተት በመመርመር ነፍሳችነን ወደ ኸይር ነገር በማመላከት

  15. ሶላታችነን በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና መንገድ በወቅቱ ከተመስጦ(ከኹሹ) ጋር በመስገድ፤ የሱና ፆሞችን በመፆምና ቂያመለይል በመቆም

  16. በምላሳችነም ይሁን በቀልባችን አሏህን አብዝተን በማውሳት

  17. በትህትና በመናገር ወይም በመመለስ

  18. በዱንያ ጉዳይ ፣ በዱንያ ትርፍና ኪሳራ ሁልጊዜ ከመጨነቅ ይልቅ የአሏህን ሰፊ ችሮታ በማስተንተን

  19. የወንድሞቻችነን እና የህቶቻችነን ስህተት ባየን ወቅት በመደበቅ

  20. ምግብ አብዝተንም ሆነ በትንሹ አለመመገብ

  21. አሏህ ለዋለለን ውለታ አመስጋኞች በመሆን

  22. እንግዶችን ፣ ምንገደኞችንና ኡለማዎችን በማገልገል

  23. ሁሌም በምንሰራው ስራ ላይ አሏህን በመፍራት

  24. ሞትን በማስታወስ

  25. ውሸት ባለመናገር

  26. ሸርአዊ ድንጋጌን በሚጣሱበት ቦታና ስብሰባዎች ላይ ባለመካፈል

  27. እራስን በመልካም ስብዕና በማነፅና ሃያዕን በመላበስ

  28. አሏህ ፍፃሜያችነን እንዲያሳምርልን በመለመን

  29. ዱአና ስቲግፋር በማብዛት

  30. ቁርአን አዘውትረን በመቅራት

  31. ያወቅነውን ነገር ለሌሎች እህት ወንድሞቻችን በማካፈል

  32. በቻልነው አቅም የምንሰራቸውን ስራዎች በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና መሰረት በማድረግና በኢህላስ በመስራት

  33. ዝምድናን በመቀጠል

  34. ከመተኛታችን በፊት ስንሰራ የዋልናቸውንና ስንሰራ ያመሸናቸውን ነገሮች አስበን ለሰራናቸው መልካም ነገሮች አሏህን ማመስገንና ለሰራናቸው ስህተቶች ደግሞ የአሏህን መሃርታ መለመን ይኖርብናል።

     

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top