እንደሚታወቀው ጋብቻ አሏህ ለኛ ልሰው ልጆች ከሰጠን ኒእማዎች መካከል አንዱ ነው። ትዳር የሰው ልጅ ከመጀመሪያው ሲፈጠር በትዳር የተረጋጋና ደስተኛ ህይወትን ይመራበት ዘንድ አሏህ ያስቀመጠው የስነ-ፍጥረት ህግጋት ሲሆን ኢስላም እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ ማህበረሰብ ባጠቃላይ የሰው ልጅ የትዳርን ጥቅም እንዲያገኙ ሁሌም ወደ ትዳር አለም ጥሪ ያደርጋል።
ትዳር የህይወታችን ወሳኝ ክፍል እንደመሆኑ በኢስላም ልዩ ስፋራ አለው። የኢማናችን ግማሽ እንደሆነ ተገፃል።
የትዳር ጥቅሞች
- ኢማንን ሙሉ ያደርጋል
- ደስተኛና ፅኑ የቤተሰብ ፍቅር መስርቶ ለመኖር ያስችላል
- የማህበራዊ ህይወት ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርጋል
- ፍቅርን እና አጋርነትን ያስገኛል
- የሰው ልጅ የዘር ሃረግ እንዳይቋረጥ ልዩ ሚና ይጫወታል
- የአሏህን ውዴታ ያስገኛል
- የአሏህ ባሪያ ፣ ሷሊህ የሆኑና ኢስላምን የሚያገለግሉ ልጆችን በኢስላማዊ አደብ ኮትኩቶ ለማሳደግ ይረዳል
- የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ኡመት ከሌሎች ነብያቶች ኡመት በላይ ከፍ ያደርጋል
- ከሃራም ነገር ይጠብቃል
- የአሏህን ህግጋት ከመጣስ ያድናል
- ዘርን ያስገኛል
- የአእምሮ ሰላምን ፣ ደስታና ምቾትን ያጎናፅፋል
- ቀልብ የሰከነች እንድትሆን ሲያደርግ ወደ ስኬትም ያመራል
- ከሸይጧን ተንኮል ይጠብቃል
- ቀላል የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖረን ያደርጋል