እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ

እህትነት እና ልባዊ የእህትነት ውዴታ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

እውነተኛ የእህትነት ፍቅር ከኢስላም የመመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ሲሆን ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር በሆነ ጥቅም ያልተመረዘ ነው።

አንዲትን ሙስሊም ሴት ጁኦግሪፊያዊ መነሻ ፣ ጐሳ ፣ የቆዳ ቀለም ፣ የአይን ቀለም ወይም የፀጉር ቴክስቸር እና ቋንቋ ሳይገድባት ከእህቶቿ ጋር ልብ ለ ልብ የሚያስተሳስር ብቸኛ ሰንሰለት ነው። ሰንሰለቱም መሰረት ያደረገው የአሏህን (ሱ.ወ.ተ) የእምነት ገመድ ላይ ነው።

አማኞች ወንድማማቾች ናቸው። በመካከላቸውም እርቅን ፍጠሩ። እናም ምህረትን ታገኙ ዘንድ አሏህን ፍሩ።”

{አል-ቁርአን 49:10}

ይህ ፍቅር አንዱ የእምነት ጥፍጥና መገለጫ ነው።

አነስ (ረዐ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) የሚከተሉት ሶስት ባህሪያቶች ያሉት ሰው የእምነት ጥፍጥና ይኖረዋል ብለዋል። {አል-ቡኻሪ ጥራዝ 1 መጽሃፍ 1 የሐዲስ ቁጥር 15}
  • አሏህ እና መልእክተኛው ከማንኛውም ነገር በላይ ውድ የሆኑለት
  • ሰውን የሚወድና ውዴታውም ለአሏህ ብሎ የሆነ
  • ወደ ጀሃነም እሳት መወርወር እንዲሚጠላ ሁሉ መክፍርን (መጥመምን) የሚጠላ የሆነ

እናም ይህ ፍቅር እውቅናን ፣ ስልጣንን ፣ ዝናን እና ክብርን ለማግኘት ተብሎ ያልሆነ ሲሆን ንፁህ እና ብርሃን የሆነ ቀልብን የሚፈልግ ውዴታ ነው። ከሰው ልብ ጥላቻን ፣ ቅናትን እና ባላንጣነትን ለማጥፈት ብቸኛው መንገድ ለአሏህ ብሎ መዋደድ ነው።

እናም ውድ ሙስሊም እህቶቼ አሏህ በእሱ መንገድ ከተዋደዱት፤ በእሱም መንገድ ተባብረው ከሚሰሩትና አርሽ ጥላ ስር ከሚቀመጡት፤ አብረው ከሚቀሰቀሱትም ያድርገን። አሏህ ኢማን እና ተቅዋን ያጎናፅፈን። አሚን!! እኔ ለአሏህ ብየ እወዳችኋለሁ!!!

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top