​ቅናት የትኩሳት በሽታ ቢሆን ኖሮ አለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በታመሙ ነበር!

 በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

ሐሰድ(ቅናት) አንድ ሰው መልካም ነገር ሲያገኝ ፣ ደስተኛ እና ጤናማ ሲሆን ፣ በትምህርቱም ሆነ በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ስኬታማ ሲሆን ፣ ሃብት ንብረት ሲያገኝ ፣ ቤተሰብ መስርቶ ልጆችን ወልዶ መኖር ሲጀምር ወይም ሌሎች በረካዎችን አሏህ ከሰፊ ችሮታው ሲለግሰው ምነው እነዚህ ነገሮች ከእሱ ጠፍተው ለእኔ በሆኑ ብሎ መመኘት ነው። ቅናት ብዙ ጊዜ ወደ ጥላቻና ወደ ጠላትነት የሚያመራ፤ የሚዋደዱ ሰዎችን በነገር አይን የሚያስተያይ እንዲሁም ብዙ ግዜ አሏህን ወዳለመታዘዝ የሚያመራ ትልቅ የልብ በሽታ ነው። በአቡዳውድ እና በትርሚዝይ በተዘገበው ሐዲስ አቡ ኹረይራ(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ልክ እሳት እንጨትን እንደሚበላው ሁሉ ቅናትም መልካም ስራን ይበላል ብለዋል።

ቅናት መጥፎ ባህሪን እና መጥፎ ስራን የሚያስከትል ሲሆን ብዙ ጊዜም ወደ ጥላቻ ፣ ክፍ አሳቢነት ፣ ሐሜት ፣ ውሸት ፣ ተንኮል ፣ ሌሎች ሙስሊሞችን አሳንሶ ወደ ማየት ፣ ስተት የሰሩ ሙስሊሞችን መልካም ስራቸውን በመደበቅ ስህተታቸውን አግዝፎ ወደ ማሳየት የሚያመራ ሲሆን ይህ በሽታ ስር ከሰደደ ደግሞ አሏህ ፍትሃዊ አይደለም ወደሚል የክህደት ጎዳና የሚያመራ መንፈሳዊ ህይወትንም ሆነ ዱንያዊ ህይወትን የሚያበላሽ ትልቅ የልብ ነቀርሳ ነው።

ያ ኢህወቲ ፊላህ! አሏሁ አዘወጀል የቀደምት ነብያትን ገድል በቀርአኑ ገልፆ እንዳስተማረን ሰማይ ላይ የመጀመሪያውን ወንጀል ወይም በደል የፈፀመው ኢብሊስ ከአደም(ዐ.ሰ) ፊትለፊት እንዳይሰግድ ያደረገውና ተረግሞ ከጀነት እንዲባረር ምክኒያት የሆነው፤ ሁለቱ የአደም(ዐ.ሰ) ልጆች ደም እንዲፋሰሱና እንዲገዳደሉ ያደረጋቸው እንዲሁም የዩሱፍ(ዐ.ሰ) ወንድሞች ዩሱፍን እራቅ ወዳለ ቦታ ወስደው ጉድጎድ ውስጥ እንዲጥሉት ያደረጋቸው ብቸኛው የቀልብ በሽታ ሒስድ(ቅናት) ነበር።

ልክእንደዚሁ ሁሉ ለዚህ ኡማም ትልቅ ፈተና ከሆኑ ነገሮች አንዱ ቅናት ነው። አንዱ ዳኢ ሌላኛውን ዳኢ አሳንሶ የሚያይበት ፣ ስራዎቹን የሚያጥላላበት ፣ ስም በመልጠፍ ከመስመር የሚያስወጣበት ፣ ሱንይ የሆነውን ወንድሙን ሱንይ አይደለህም ብሎ የሚሞግትበት ፣ አንዱ ኡለማ ሌላኛውን ኡለማ በነገር አይን የሚያይበት ፣ ልጅ አባትና እናቱን የሚገልበት ፣ ሚስት ባሏን የምትገልበት ፣ ልጅ ወላጆቹን ፍርድቤት ገትሮ የሚሞግትበት ፣ ዘመድ የዘመዱን ሰብል ወይም የዘመዱን ቤት በእሳት የሚያቃጥልበት ትልቁ የዚህ ኡማ በሽታ የሆነው ሒስድ ነው። እንደኔ እንደኔ ከጊዜ ወደጊዜ የጀመአዎች ሉይነት እየሰፋ የመጣውም በዚህ ምክኒያት ነው።

አሏሁ አዘወጀል በቁርአኑ በሱረቱ ኒሳዕ አንቀፅ 54 ላይ እንዲህ ይላል፦

               =<({አል-ቁርአን 4:54})>=

{54} አሏህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ሰዎችን ይመቀኛሉን?

=<({አል-ቁርአን 113:5})>=

{5} ምቀኛም በተመቀኘ ጊዜ (ከእርሱ) ክፋት እጠበቃለሁ በል!

ያ ኢህወቲ ፊላህ! እኛ ሙስሊሞች ከዚህ የልብ ነቀርሳ እራሳችንን ልናርቅ ይገባል። ሌሎች ሰዎች ያላቸው ነገር ወይም ስኬት ላይ የደረሱበት ነገር ካስደስተን አሏህ ለነሱም እንዲጨምርላቸው ለኛም እንዲሰጠን ዱአ እናድርግ እንጁ ሰዎችን በቅናት አይን አንመልከት ውጤቱ የከፋ ነውና።

  • አሏህ በቅዱስ ቃሉ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና ማለቱን አንዘንጋ!
  • በአንተ ላይ የሚቀኑ ሰዎችን ከምትጠላቸው ይልቅ ቅናታቸውን አክብርላቸው ምክኒያቱም አንተ ከነሱ የተሻልክ እንደሆንክ የሚያስቡ ናቸውና።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top