ክፍል አንድ

ቅንብር: አቡ አሚና ቢላል ፊሊፕስ
ተርጓሚ: ጀማል ሙኽታር

ኢስላም

ኢስላምን አስመልክቶ አንድ ሰው በቅድሚያ ሊያውቀውና በግልፅ ሊረዳው የሚገባው ነገር ኢስላም የሚለው ቃል ትርጉሙ ራሱ ምን ማለት እንደሆነ ነው። ክርስትና ከእየሱስ፤ ቡድሂዝም ከጉተማ ቡድሃ፤ ኮንፊሽያኒዝም ከኮንፊሽየስ እንዲሁም ማርክሲዝም ከካርል ማርክስ ስያሜያቸውን እንዳገኙ አይነት የእስልምና ሃይማኖት ስሙን ከግለሰብ ስም አልወሰደም። እንደ አይሁዳ ከይሁዳ ጐሳና እንደ ሕንዱይዝም ከህንዱ መጠሪያ ስሙን አላገኘም። ኢስላም የአሏህ ሃይማኖት ነው። በመሆኑም መጠሪያ ስሙ የአሏህን ሃይማኖት ማእከላዊ መርህ ለአሏህ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መገዛትንና ማደርን የሚወክል መጠሪያ ስም ነው። ኢስላም የሚለው የአረብኛ ቃል አምልኮት ለሚገባው ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ለአሏህ ራስን ማስገዛትና ለርሱ ፍቃድ ማደር ማለት ሲሆን ይህን የሚያደርግ ማንኛውም ሰው «ሙስሊም» ተብሎ ይጠራል። በተጨማሪም ቃሉ ሙሉ በሙሉ ለአሏህ ፈቃድ የመገዛት ውጤት የሆነውን “ሠላምን” ያመለክታል። ስለዚህ ዐረቢያ ውስጥ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አማካኝነት የመጣ አዲስ ሀይማኖት ሳይሆን በመጨረሻ ቅርፁ ዳግም የተገለፀ እውነተኛ ሀይማኖት ነው።

ኢስላም ለመጀመሪያው ሰውና ለመጀመሪያው የአላህ ነቢይ ለአደም የተሰጠና ወደ መላው የሰው ልጅ ከአሏህ የተላኩ ነቢዮች ሁሉ የጋራ ሃይማኖት ነዉ። የአሏህ ሃይማኖት የሆነው ኢስላም በዚህ እንዲሰየም የተወሰነው በኋለኞቹ የሰው ልጅ ትውልዶች አይደለም። ስሙ የተመረጠው በራሱ በአሏህ ሲሆን ይህም ወደ ሰው ልጅ ባስተላለፈው የማጠቃለያ መልእክት(ወሕይ) ውስጥ በግልፅ ተጠቅሷል። የመጨረሻው መለኮታዊ መፅሐፍ በሆነው ቁርአን ውስጥ አሏህ እንዲህ ይላል፦

"ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ ጸጋየንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ ለናንተም ኢስላምን ከሀይማኖት በኩል ወደድኩ።" {ሱራ አል-ማኢዳ 5:3}
"ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈፀጽሞ ከርሱ ተቀባይነት የለውም፤" {ሱራ አል-ዒምራን 3:65}
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበር፤ {ሱራ አል-ዒምራን 3:67}

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የትም ቦታ ላይ አሏህ ለነብዩ ሙሳ ሕዝብም ሆነ ለዝርዮቻቸው የነርሱ ሃይማኖት ይሁዳዊነት ነው ሲል ወይም ለክርስቶስ ተከታዮች ሃይማኖታቸው ክርስትና ነው ሲል አናገኝም። እውነቱን ለመነጋገር ሌላው ቀርቶ “ክራይስት” የሚለው ቃል “ክርስቶስ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ስም ሲሆን ትርጉሙ የተቀባው ማለት ነው። ይህም ክርስቶስ “መሲሕ” ለሚለለው የዕብራይስጥ የማእረግ ስም ትርጉም ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ኢየሱስ የሚለው ስም “ኢሳው(Esau)” ለሚለው የኢብራይስጥ ስም ላቲናዊ ቅላፄ ነው።

ይሁን እንጅ ነገሩን ቀላል ለማድረግ ስል ነብዩ ኢሳ(ዐ.ሰ) እየሱስ ብየ መጥራቴን እቀጥላለሁ። ሃይማኖታቸውን በተመለከተ ግን መጠፈሪያው ነብዩ ተከታዮቻቸውን ይጠሩበት የነበረው ስም ነው። ከሳቸው በፊት እንደነበሩት ነቢያት ሁሉ ሕዝቡ ፍላጐቱን ለአሏህ ፍላጐትና ለርሱ ፈቃድ እንዲያስገዛ ጥሪ አድርገዋል። የሰው ልጅ ምናብ ከፈጠራቸው የሐሰት አማልክት እንዲርቅም አስጠንቅቀዋል። በሐዲስ ኪዳን እንደተጠቀሰው ተከታዮቻቸው «ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁ በምድርም ትሁን» ብለው እንዲፀልዩ አስተምረዋል።

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top