በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

በወጣቱ ተልዕኮ(አህመድ የሱፍ)

እናስተውል! ቁምነገር እንጅ ቀልድ የማይገባው ሞት ከፊታችን ይጠብቀናልና!

የቁምነገር ጫፍ የጠፋብን እስኪመስል ህይወታችን በቀልድ ብቻ የተሞላ ሆኗል፤ የወሪያችን አብዛሃኛው እጅ ፍሬ አልባ ቀልድና ዛዛታ ነው። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ለሶላት ሲቆሙ ከማን ፊት እንደሚቆሙ ያውቃሉና ከሶሃቦቻቸው ጋር እንኳ እንደማይተዋወቁ ይሆናሉ። እኛ ግን እየቀለድን ምናልባት ቀልዱንም እያጣጣምን ለሶላት እንቆማለን። የቀለድን በማስመሰል እንዋሻለን፤ ስንቀልድ ነው እያልን ሰውን በነገር እንወጋለን። አሏህ ለማን እንደተናገርን ወይም እንደቀለድን የውስጣችነን የሚያውቅ ስለመሆኑ ፈፅሞ መዘንጋት የሌለብን ጉዳይ ነው። የቀለድነው ነገር መጥፎ ይሁን ጥሩ ምንዳችነን እንደየስራችን ይሰጠናል።

በእርግጥ ቁምነገሮችን በቀልድ መልክ ማስተላለፋችን አይከፍም የሚከፋው ሲበዛና ቁምነገር ያጣ እንደሆነ ነው። ሰው በገዛ እጁ በራሱ ላይ አደጋ የሚጠራው በአሏህ ንግግር በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና እና በሃይማኖቱ መቀለድ ሲጀመር ነው። ይህ አይነቱ ቀልድ ቀልድ ሳይሆን ወደ ኩፍር የሚያድርስ ድፍረት ነው። አንዳንዴ ሰዎችን ወደ እስልምና ለመጣራት በምናደርገው ዳዕዋ ሙዱ ገብቶናል በሚሉ ሰዎች የሚቀለዱ ቀልዶች አሉ። ለምሳሌ አሏህ ጀነትን አህያ አያስርበት ነገር እና የመሳሰሉት ቀልዶች ከተለመዱ ይሰፉ ይሰፉና ሰዎች መንካት የሌለባቸውን ነገሮች ይነካሉ መዳፈር የሌለባቸውን ነገር ይደፍራሉ።

አሏህ በቁርአኑ በሱረቱ አተውባ አንቀፅ 65-66 ባለው እንዲህ ይላል፦

             =<({አል-ቁርአን 9:65-66})>=

{65} በእርግት! ብትጠይቃቸው እኛ እየተጫወትን እና እየቀለድን ነው ይላሉ። በአሏህና በአንቀፆቹ ፣ በመልዕክተኛውም ታላግጡ ነበራችሁን? በላቸው። {66} አታመካኙ ከአመናችሁ ብኋላ በእርግጥ ካዳችሁ።

የአጓጉል ቀልድ አደጋው ይህን ያህል የከፋ መሆኑን ካወቅን በአሏህ ፣ በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፣ በሃይማኖቱና በምልክቶቹ መቀለድ መታረም ያለበት ስህተት ነውና መቅረት አለበት። በፂም ፣ በሂጃብ ፣ በኒቃብ ፣ በሱሪ ፣ በጀለቢያ ፣ በኮፍያ ወ.ዘ.ተ መቀለድና መተረብ ይቁም። ስንቀልድና ስንተርብ በሰው ሳይሆን የሃይማኖቱ ምንጭ በሆነው አሏሁ አዘወጀል እያፌዝን መሆኑን እንረዳ።

የምላስ ወለምታ በቂቤ አይታሽም እንዲሉ ስንት ሰው አለ መሰላችሁ ሰውን ለማሳቅ ብሎ ጥቂት ቃላትን ብቻ ተናግሮ ጀሃነም እጣው የሚሆን። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው እንዲህ ብለዋል፦

“ከእናንተ ውስጥ አንዱ አሏህን የሚያስደስት አንድ ንግግር ይናገራል ወደ ላቀ ደረጃ ታደርሳለች ብሎ ሳያስብና ሳይገምት አሏህ ግን በእርሷ ሰበብ እስከ ዕለተ ቂያማ ድረስ ውዴታውን ይፅፍለታል። አንድ ሰው አሏህን የምታስቆጣ አንዲት ቃል ይናገራል ወደ አዘቅት ትጥለኛለች ብሎ ፈፅሞ ሳያስብና ሳይገምት በእርሷ ሰበብ ግን አሏህ እስከ እለተ ቂያማ ድረስ ቁጣውን ይፅፍበታል።”

ጎበዝ ቁምነገር እና ቀልዳችነን መለየት እስኪያቅተን ድረስ ቀልዳችን በዝቷል። በእንቅስቃሴያችን የሰፋ አደጋ በሚገጥመን ድረሱልን ብለን በምንጮህበት ጊዜ አረ እሱ እየቀለደ ነው ብለው ሰዎች እንዳይተውን ያሰጋል። ቁምነገር እንጅ ቀልድ የማይገባው ሞት ከፊታችን ይጠብቀናል እና እናስብበት!!!

For more free Islamic pamphlets, brochures and books delivery please subscribe to Youth Mission የወጣቱ ተልዕኮ

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top