አህለሱና ወልጀመአ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮት እና ምሳሌ ፣ የሶሃባዎች እና ቀደምት ደጋግ የአሏህ ባሮች መንገድ አጥብቀው የያዙ ሰዎች ለማመላከት የምንጠቀመው መጠሪያ ስም ነው።
ይህ ማዕረግ ወይም መጠሪያ እውነትን አጥብቀው የሚከተሉ ሰዎችን በሃይማኖት ከሚፈላሰፉ እና ፈጠራቸውን ከሚከተሉ ሰዎች እንደመለያነት ያገለግላል።
አህለሱና ወልጀመአ እውነትን የሚከተሉ እና በመካከላቸውም በሃማኖት ቡድንተኝነት የማይከፋፈሉ፤ የዚህ ኡማ ቀደምት ሷሊሆች በተስማሙበት ነገር ብቻ የሚከተሉ ናቸው። በእምነት ጉዳይ በሃይማኖት ቡድኖች ጽንፍ መካከለኛ አቋምን የያዙ ናቸው።
በተመሳሳይ ሁኔታ በአምልኮት ተግባራት እና ባህሪያቶች በጽንፈኞች እና በቸልተኞች መካከል መካከለኛ አቋም የያዙ ናቸው። በዚህ አለም “አሸናፊዎች” በመጭው አለም ህይወት ደግሞ ነጃ የሚወጡ (ሚድኑት) ናቸው።
ሌላው አህለሱና ወልጀመአ ጋር በተያያዘ የሚጠቀሰው መጠሪያ ሰለፉነ ሷሊሂን ነው። የቃል በቃል ትርጉሙ “ቀደምት ሷሊሆች ፃድቃናት” የሚል ነው።
ይህ የሚያመለክተው የነብዩ ሶሃባዎች ፣ የእነሱ ፃድቅ (ሷሊህ) ወራሾ እና የአሏህን መጽሐፍት እና የመልእክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና የነብዩ ሶሃባዎች በተረዱበት መንገድ አጥብቀው የያዙትን ተከታይ መራሾች ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ቢድአና ሱና ተመልከቱ