ለሶላት ቅድሚያ እንስጥ

Author picture
ሶላት ልብን ብርሃን የምታድርግ ፣ የስኬት ሚስጥር ፣ የጀነት ቁልፍ እና ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር የምናጠነክርበት ፣ የአሏህን ውዴታ የምናገኝበት ፣ ለአሏህ ያለንን ታዛዥነት የምንገልፅባት ብቸኛዋ የኢባዳ ተግባር ናት።

አሏህ የሰው ልጆችን የፈጠረበትን አላማ ሲገልፅ በቁርአን እንዲህ ይላል፡ «የሰው ልጆችንም ሆነ ጅኖችን አልፈጠርኩዋቸውም እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጂ።»

እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርንበትን አላማ ረስተን አለማዊ በሆኑ ነገሮች ተጠምደን፤ አሂራን ረስተን ዱንያን ለማሳመር ከታች ከላይ ማለታችነን ቀጥለናል።

ይህ ምን ያህል ልቦቻችን በድንቁርና ፅልመት እንደተሸፈኑ የሚያመላክት ነው። እስኪ በነፍሶቻችን ውስጥ ያለውን እውነታ በጥያቄ መልክ እንመልከት።

  • ቁርአንን በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ የምንቀራ ምን ያህሎቻችነን?
  • ሶላታችነን በተደነገጉት የሶላት ሰዓት የምንሰግድ ፣ ኢስላማዊ እውቀትን ለመሻት የምንጣጣርስ ስንቶቻችን እንሆን?
  • ስለዲናችን ወቅታዊ ጉዳዮችስ ቁጭ ብለን የምንወያይ ስንቶቻችን እንሆን?
  • አይደለም ስለወቅታዊ ጉዳዮቻችን ቁጭ ብለን መወያየት ይቅርና ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ሰላምታን መለዋወጥ እረፍት እየሆነብን አይደለምን? እንደ ሙስሊምነታችን ከኛ የሚጠበቁብንን ነገሮች የምንሰራስ ስንቶቻችን እንሆን?
  • ወላጆቻችነን በቅን መንፈስ እያገለገልን ያለን ፣ ኢስላማዊ ባህሪያትን የተላበስን ፣ አሏህ ከከለከለው ነገር የተከለከልን ፣ የአሏህን ቅጣት ፈርተን ተውበት እያደረግን ስቅስቅ ብለን የምናለቅስ እና ህይወታችነን በቁርአን እና በረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እየመራን ያለን ስንቶቻችን እንሆን?

ሶላት

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንከቡት 29:45)

“ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች።”

ስግደት (ሶላት) ልብን ብርሃን የምታድርግ ፣ የስኬት ሚስጥር ፣ የጀነት ቁልፍ እና ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር የምናጠነክርበት ፣ የአሏህን ውዴታ የምናገኝበት ፣ ለአሏህ ትእዛዝ ያለንን ታዛዥነት ፣ ባርነታችንንና ለማኝነታችነን የምንገልፅባት ብቸኛዋ የኢባዳ ተግባር ናት።

ሶላት በጭንቀት ጊዜ እረፍትን ሰጭ ፣ ለችግሮች መፍትሄና የሃጥያቶች ማበሻ ናት።

ዛሬ ዛሬ ሶላትን መስገድ ፣ ቁርአን መቅራት ፣ ሂጃብ መልበስ የትርፍ ጊዜ ስራ እየሆነ መጥቷል። በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ይህንን እውነታ ለማረጋገጥ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፆች ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና በየሰፈሮቻችን ባሉ መስጅዶች ያለውን አህዋል መመልከት በቂ ነው።

ሶላት አንዱ የኢስላም ምሰሶ እንደሆነ ይታወቃል። ሶላትን አለመስገድ አንዱን የኢስላም ምሰሶን እንደ መናድ ነው። ለሶላታችን ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

አትኩሮት አይደለም ለሶላት በውዱእ ወቅት እንኴ ትኩረት ሰጥተን ተረከዛችነን በደንብ እንድናጥብ ፣ እያንዳንዷን ክፍል እንድናዳርስና ተረከዛችንንም ከጀሃነም እሳት እንድንጠብቅ ከሁሉም ነገር በላይ ተወዳጅ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አዘውናል።

አብዱሏህ ቢን አምር እንደተረከው አንዴ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጉዞ ወቅት ከኋላችን ቀርተው ነበር። ለሶላት ውዱእ እያደረግን እያለ ተቀላቀሉን። በእርጥብ እጃችነም እግሮቻችነን እያበስን ነበር። እናም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ሁለቴ እና ሶስቴ ተረከዛችሁን ከጀሃነም እሳት ጠብቁ አሉ። {ጥራዝ 1,መጽሐፍ 3,የሐ.ቁጥር 57}

ከሶላት እንድንርቅ የሚያደርጉ ነገሮች

  • ቸልተኝነት
  • ነገን እቶብታለሁ በማለት ሃጥያትን መዳፈር
  • ከቁርአን እና ከሐዲስ መራቅ
  • ትኩረትን አለማዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ ማድረግ
  • ማህበራዊ ድህረገፆችን አዘውትሮ መጠቀም
  • መጥፎ ጓደኛ
  • እውቀት አለመኖር
  • የአሏህ ፍራቻ በልባችን ውስጥ አለመኖር
  • የቀልብ መድረቅ
  • በኢስላማዊ ባህሪ ተኮትኩቶ አለማደግ
  • የአስተሳሰብ ዝንፈት
  • ጌሞችን አዘውትሮ መመልከት እና መጫዎት
  • የሰይጣንን መንገድ መከተል

በሰላታችን ጠንካራ ለመሆን ከሶላታችን እንድንርቅ ያደረጉንን ነገሮች ልናስወግድ ይገባል። በዙርያችን ከሶላት የራቀ ሰው ካለ የሚከተሉትን ነገሮች ልናደርግለት እንሞክር

  1. ዳእዋ ማድረግ
  2. ሰውየው በራሱ ከሶላት እንዲርቅ ያደረጉትን ነገሮች ነቅሶ እንዲያወጣ ማገዝ።
  3. ተውበት አድርጎ ወደ ሶላት እንዲመለስ ግፊት ማድረግ
    • አብሮን እንዲሰግድ ማበረታታት
    • ማስታወስ
    • ለዚህ ሰው ሁሌም ከጎኑ በመሆን የሚቸግሩት ነገሮች ካሉ ማገዝ
  1. የአሏህ ፍራቻ በልባችን ውስጥ እንዲኖር ማድረግ
    • የሶላትን ምንዳ ማስታወስ
    • ሶላትን የመተው ቅጣት ምን እንደሆነና የፍርዱን ቀን መከራ ማስተንተን
    • የዚች አለም ውስንነት በጥልቅ መረዳት
  1. እውቀትን መሻት
  2. ዱአንና ኢስቲግፋርን ማብዛት
  3. የመልካም ስብእና ባለቤት መሆን
  4. ከመጥፎ ጓደኛ መራቅ
  5. ታናናሽ ወንድሞቻችነን ፣ እህቶቻችንና ልጆቻችነን በኢስላማዊ ባህሪያት ኮትኩተን ማሳደግ
0%
3
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሶላት

ጥያቄና መልስ፡ የጀመአ ሶላት (የህብረት ስግደት)

‹‹ሶላቱል ጀመአ (የህብረት ስግደት)›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 የጀመአ ሶላት ሊባል የሚችለው በትንሹ ስንት ሰዎች ሲታደሙ ነው?

2 / 6

Bookmark question icon

2 ከኢማሙ ጋር አብሮ የሚሰግደው አንድ ሰው ብቻ ከሆነ የሰውየው አቋቋም ምን መሆን አለበት?

3 / 6

Bookmark question icon

3 እውነት ወይም ሐሰት፡ ኢማሙ በሩኩዕ ሁኔታ ላይ ሆኖ ሳላ ሰጋጁ ጀመአውን ከተቀላቀለ እንደ አንድ ሙሉ ረከአ ይቆጠራል፡፡

4 / 6

Bookmark question icon

4 እውነት ወይም ሐሰት፡ ኢማሙ (ጀመአውን የሚመራው) ሁልጊዜም በእድሜ ከፍ ያለ ነው፡፡

5 / 6

Bookmark question icon

5 ጀመአውን ዘግይየት ብሎ የተቀላቀለ ሰው ማድረግ ያለበት ምንድን ነው?

6 / 6

Bookmark question icon

6 ከኢማሙ ጀርባ የሚሰግድ ሰው ኢማሙን መከተል ያለበት በምን አግባብ ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 13%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ከማንኛውም ነገር በላይ ለሶላት ቅድሚያ እንስጥ!

Related posts

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡

Read More »
ሱጁድ

ሱጁድ

ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣

Read More »
ኢቃም

ኢቃም

ኢቃማ ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ

Read More »
ረከአ

ረከአ

እያንዳንዱ ሶላት የአንድ ወይም የሁለት ፣ የሶስት ወይም የአራት ረከአ ህብር ነው። እያንዳንዱ ረከአ አቋቋሞች ወይም ቅርፆች አሉት፤ መጀመሪያ መቆም ፣ ከዛም መዳፎችን ጉልበት ላይ

Read More »

Share