ማን እንደ እናት

ማን እንደ እናት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

«ሰውንም ለወላጆቹ በጐ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው፤ በችግርም ላይ ሆና ወለደችው፤…»

{አል-ቁርአን 46 : 15}

“ጌታችሁም ከእሱ በቀር ያለን ነገር እንዳታመልኩ እና ለቤተሰቦቻችሁ ቅን ትሆኑ ዘንድ ደነገገ። በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው የእርጅና እድሜ በደረሱ ጊዜ ‘ኡፉ’ አትበላቸው ፤ አትገላምጣቸውም። መልካምን ቃል ተናገራቸው። በእዝነት የውርደትና የሽንፈት ክንፍህን ዝቅ አድርግላቸው። እናም ‘ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርህራሄ) እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትህን ስጣቸው’ በል።”

{አል-ቁርአን 17:23-24}

«የሰው ልጅ ለወላጆቹ መልካምና ታዛዥ ይሆን ዘንድ አዘዝነው። ነገርግን እውቀት በሌለህ ነገር በኔ ላይ እንድታሻርክ ቢጥሩ (ቢያስገድዱህ) አትታዘዛቸው፤..»

{አል-ቁርአን 29 :8}

በአህመድና በአነሳኢ እንደተዘገበው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)፡ ጀነት ከናታችሁ እግር ስር ናት ብለዋል።

አቡሑረይራ (ረ.ዐ) እንደተረከው አንድ ሰው ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ያረሱ ሉሏህ! በጣም ላገለግለው የሚገባ ማነው? ሲል ጠየቀ። ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እናትህ አሉት። ሰውየው ቀጣዩስ ማነው? ሲል ጠየቀ። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እናትህ አሉት። ቀጣዩስ ማነው? ሲል በድጋሚ ጠየቀ። ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) እናትህ አሉት። ለአራተኛ ጊዜ ቀጣዩስ ማነው? ሲል ጠየቃቸው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) አባትህ አሉት። {ቡሐሪ መጽሐፍ 73, ጥራዝ 8, የሐ.ቁጥር 2}

በአቡ ዳውድና በኢብን ማጃ እንደተዘገበው አቡ ኡሰይድ እንዳወራው አንዴ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ቁጭ ብለን ከሰላማህ ጐሳ የሆነ አንድ ሰው መጣና እንዲህ አላቸው፡ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ወላጆቼ ከሞቱ ብኻላ በኔ ላይ ሃቅ አላቸውን? ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ አዎ! አሏህ በምህረቱ እና በእዝነቱ ይባርካቸው ዘንድ ዱአ ልታደርግላቸው ይገባል! ለሰዎች የገቡትን ቃልቂዳን አሟላ፤ ጓደኞቻቸውንና ዝምድናቸውን አክብር ብለዋል።

ማን እንደ እናት

እናት የዛሬ ማንነታችን ስትሆን በመልካም ስብዕና ኮትኩታ ፣ ከመጥፎ ነገር ከልክላ አሳድጋናለች። የወደፊት ግባችን ምን መሆን እንዳለበት ሁሌም ትጨነቃለች ፣ ታልማለች። እሷ ሳትበላ እኛን ታጐርሳለች፤ የራሷን ስሜት ገድባ የኛን ታሟላለች።

ስናለቅስ ልቧ በፍርሃት ፣ በጭንቀትና በትካዜ ይዋጣል። እሩቅ ቦታ ስንሄድ ሃሳቧ ሁሉ ጥቅልል ብሎ ስለኛ ደህነነት ማሰብና መጨነቅ ይሆናል። በምን ሁኔታ ላይ እንደሆን ዘወትር ትጠበባለች።

ታዲያ እናትን መገላመጥ መሳደብ በሷ ላይ መፎከስ ቀርቶ ኡፍ እንኳ ፈፅሞ ልንላት አይገባም። አይደለም እንዴ? አዎ ይህን እንዳናደርግ ቁርአን ያስተምረናለ።

ይህን ሁሉ ፍቅር እዝነት ሰጥታን ልቧን መስበር ትልቅ ወንጀል ነው። እናም ውድ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ እናታችንን በቅን መንፈስ እናገልግላት፤ እንከባከባት።

የእናቱን ደስታ ፣ ፈገግታ ማየት የማይሻ ማን ይኖር ይሆን? ወንድሜ ከእሷ ሌላ አታገኝምና እድሉ ሳያመልጥህ ተጠቀምበት!!

በትንሹም ቢሆን አሏህ የእናታቸውን ሃቅ ከሚወጡት መካከል ያድርገን!!!

Share the Post:

Related Posts

መረጃ እና አስፈላጊነቱ

መረጃ ትርጉም ያለው መልዕክት ሆኖ ከአንድ ምንጭ ወደ ተጠቃሚ የሚተላለፍ ነው፡፡ ስለአንድ ነገር መግለፅ የሚያስችለን  ነው፡፡ ይህ መረጃ ከግለሰብ አስተሳሰብ

Read More
ተውባ
Ahmed Yesuf

ተውባ

ተውባ ማለት ሃጢያትን ወይም ወንጀልን ከሰራንና ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር አደጋ ላይ ከጣልን ብኻላ ወደ አሏህ በፀፀት መመለስ ማለት ነው።

Read More

Join Our Newsletter

Scroll to Top