ዛሬ የብዙወቻችን ችግር ኢልም አይደለም ተግባሩ እንጂ። ብዙወቻችን አንብበናል ፣ ሰምተናል ፣ አውቀናልም። ነገርግን ከአስተማሪውም ሆነ ከተማሪው የተግባር ሰው ጠፍቷል። መካሪው እና ተመካሪው እኩል ሆኗል።
በእርግጠኝነትና በቆራጥ ውሳኔ መንቃት የምንፈልግ ሁሉ በዚህ የቁርአን አንቀፅ እንንቃ!
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ።”
{አል-ቁርአን 61:2}
በሱረቱል በቀራ አንቀፅ 44 ላይ እንዲህ ይላል:-
“እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? የስራዎቻችሁን መጥፎነት አታውቁምን?”
{አል-ቁርአን 2:44}
አይሁዶች መጽሐፍ ተሰቷቸው ስላልሰሩበት በአህያ ተመሰሉ አሏህ በቁርአኑ በሱረቱል ጁምአ አንቀፅ 5 ላይ እንዲህ ይለላል:-
“የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያም ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ቢጤ ነው። የእነዚያ በአሏህ አንቀጾች ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ከፋ። አሏህም በዳዮችን ህዝቦች አይመራም።”
{አል-ቁርአን 62:5}